Tuesday, October 15, 2013

This is not Ethiopia

እንደሃገር እንነጋገር!

http://ecadforum.com/Amharic/archives/9976/

እንደሃገር እንነጋገር!

October 15, 2013
ታደለ መኩሪያ
ኑር ከሰው ኑር ከሃገር ይል ነበር፡ የሃገሬ ሰው፤ ሰው ለሰው መፈጠሩን የሚገልጽ አባባል ነው። በአጠገብህ ካለው መሰልህ ሰው አብረህ መኖር ከቻልክ በመላው ሃገርህ ካለው ሰው መኖር አያቅትህም ለማለት ነው።
የሰው ልጅ ለራሱ መልካሙን እንደሚያስብና እንደሚሰራ ሁሉ ራሱን ለማጥፋትም የዛኑ ያህል ይሠራል። ጥያቄው ባብላጫው ለየትኛው ይሠራል ነው? ሕዝብ እንደ አንድ የሃገር ዜጋ ተሰባስቦ ሲኖር ማሟላት ያለበት በተፈጥሮ የተቀበለው ግዴታ አለበት። መሠረታዊ የሆኑ ፍላጎቶቹን ማሟላት፣ ስብዕናውን ያለማስደፈር፣የሌላውንም ያለመድፈር፣በሌላው ላይ ፍትህ ሲጓደል የእርሱም እንደተጣሰ መቁጠር፤ ትውልድ እንዲተካው ሲያስብም ቅርስ ማስተላለፍም  ግድ እንሚለው ማወቅ  ከብዙቹ ጥቂቶቹ ናቸው። ያ ሣይሆን ቀርቶ ዜጎች በረሃብ፣ በጦርነት፣በስደት፣ በፍትህ እጦት የሚጎሣቆሉ ከሆነ ሰው አውቆም ሆነ ሣያውቅ ለመልካሙ ሣይሆን ለጥፋቱ እየሰራ ነው። በግብተኝነት መሪዎች ናቸው ለዚህ ሁለ ጥፋት ተጠያቂዎች በማለት የሚያቀርበው ከሃላፊነት የማምለጫ ምክንያት ውኃ አያነሳም፤ ለምን ቢባል መሪ ከሕዝብ ነውና የሚወጣው፤ ሆኖም ወደዝርዝር ሐታታ ከመግባቴ በፊት ለአንባቢዬ ጥያቄ ላቅርብ፤ በኢትዮጵያ ሃገራችን የመልካሙ ሥራ ወይስ የጥፋቱ ሥራ አይሎ ይገኛል? መልሱን ለእናንተ ለተወው።
ከኖርኩት ዘመን ልጀምር፣ ከአርባ ዓመት በፊት የሕብረተሰባችን አመለካከት፣ የተፈጥሮ ሐብታችን  አጠባበቅ አሁን ካለንበት  በጥልቀት ሲመረመር፣ ሰው ራሱን የሚያጠፋ እንጂ የሚያለማ ተግባሩ ጎልቶ አይታይም ። በሰዎች መካከል የነበረው መከባበር፣ የሃይማኖት ዕምነት፣የቃልኪደን ጽናት እየተሟጠጠ መምጣቱን ያሣያል። የተፈጥሮ ሐብታችንም በቁማር እንደተገኘ ሐብት በአስረሽ ሚቺው የመሰለ የዜግነት ሃላፊነት በጎደለው መንገድ መውደሙ ይታያል። ሰው ራሱ በሰራው ጥፋት  ምን ማድረግ እንዳለበት ግራ ተጋብቷል። በቅርቡ ዶክተር በረሃኑ ነጋ ‘ዴሞክራሲና ሁለንታዊ ልማት በኢትዮጵያ’ በሚል ርዕስ ባሳተሙት መጽሐፋቸው ውስጥ ሃገራችን ያለችበትን አስጊ ሁኔታ ገልጸዋል። በጥናት የተገኙ መረጃዎችን ዋቢ በማድረግ ለናሙና ያህል ያሉትን ኩነቶች በመጽሐፉ ውስጥ አስፍረዋል። የሰው ልጅ ራሱን ከሚያጠፋው ተግባሩ ይልቅ ከሚያለማው ሥራ ላይ ልቆ ቢገኝ እሰየው ነበር፤ ግን አልሆነም። እንዲሆን ምን መደረግ አለበት? ለሚለው መልሱ  እንደሃገር ከመነጋገር  ሌላ አማራጭ የለውም። ሰው ለሃገሩ ልማትም ሆነ ጥፋት ሃላፊነት አለበት። እያነዳንዱ ሰው ትውልድ እተካባታለሁ የሚላትን ሃገሩን ካልተከባከበ ለተፈጥሮ ሐብቷ መከበር ዘብ ካልቆመ ከዚያ ውጭ የሚሠራው ለጥፋት ነው። በዴሞክራሲ የተመረጡ የሕዝብ ተወካዮች የማይመሩት አስተዳደር የሚሠራው ለጥፋት ነው። በዘፈቀደ  በነዝህላልነት በልምድ የሚሠሩ ሥራዎች የሚመሩት ወደ ጥፋት ነው።
ባለፉት ዘመናት ወደ ሥልጣን የመጡት የንገሡና የደርግ ገዥዎች በሩን ገርበብ አድርገው ዘግተው እኛ ነን ሰለሃገር የምንነጋገር እናንተ ያለናችሁን አድርጉ የሚሉ ነበሩ። አሁን በትረ መንግሥቱን የያዘው የትግራይ ሕዝብ ነፃነት ግንባር (ሕወሃት)  እንደሃገር  ሳይሆን እንደመንደር እንነጋገር የሚል ነው። ከናካቴው  በሩን በደህንነት፣ በፌደራል ፖሊስ፣ በአጋዚ ጦር ክርችም አድርጎ  ባለሃገሩን አላውቅህም የሚል የቅኝ ገዥዎችን መሰል አገዛዝ የሚያራምድ ነው። ይህን በቅኝ ገዠ ቁልፍ የተዘጋውን  በር ማስከፈት የምንችለው እንደሃገር ስንነጋገር ነው። ለገዥዎቻችን በር ጠባቂዎች ቀለብ ሰፋሪዎቹ እኛ ነን እነርሱም በአካል እኛን ናቸው። ሕዝብ ካልፈቀደ መሪዎች  ነን ባዮች አንዲት ቀን በመንበራቸው ላይ ለቆዩ አይችሉም። ይህ እንዲሆን መፍቀዱ በራሱ ትልቅ ጥፍት ነው። በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ራሳችንን ለዘመናት በማጥፋት ሥራ ላይ እንደተሰማራን  የሚያሳይ ነው። ስለዚህ ለጥፋቶች ሁሉ ጥፋት ዜጎች ትልቁን ድርሻ እንወስዳለን።ምክንያቱም ጥቂቶች ሃገር እንዲያጠፉ ብዙሃኑ ፈቅደናልና! ሰው ራሱን ለማጥፋት ይሰራል ስል፤ የዜግነተን ግዴታ ካለማወቅ፣ከግዴለሽነት፣ ከፍረሃት፣ራስ ወዳድነት፣አቆራጭ አማራጭ ለራስ መኖር ከመሻትና አርቆ አስተዋይነትን በማጓደሉ ተቀራርበን ያለመነጋገራችን የሃገራችንን ችግሮች በጋራ ለማስወገድ  አለመቆማችን ለጥፋት መስራታችንን ፍትው አድርጎ የሚያሳይ ነው።
በአሁኑ ወቅት ከምንጊዜውም  ጊዜ ይልቅ በተሻለ መንገድ ተቀራርብን እንደሃገር ለመነጋገር አመቺ ሁኔታ የተፈጠረ ይመስላል። የቀድሞ ገዥዎቻችን በሓለፈነታቸው ከጥፋት ነፃ ናቸው አንልም። ወያኔ ግን አሣውን ለማጥፋት ውኃውን አድርቀው የሚል ፓሊሲ የሚከተል ነው። ይህን ማን ፈቀደለት እኛው ነን።
የትግራይ ሕዝብ ነፃነት ግንባር (ሕወሃት) የተለያዩ የጎሣ አባላትን ለቃቅሞ ሃገሪቱ የምትተዳደርበትን ሕገ መንሥት ቀረፆ  ኢህአዴግ የሚባል ድርጅት ነው ሃገር የሚመራው አለን። ሐቁ ግን ሕገ መንግሥቱም ኢህአዴግም የፈረስ ዕቃ ናቸው። ጋላቢው የትግራይ ሕዝብ ነፃነት ግንባር (ሕወሃት) ትግራይን  ለመገንጠል ፣ ኤርትራን ለማስገንጠል 1967 ዓ ም የቀረጸው ፕሮግራሙ ዛሬ በመላው ሃገራችን እየተገበረ ነው። ይህ ፕሮግራም ፋሺሽት ኢጣሊያ 1928 ዓ ም  ኢትዮጵያን  በቅኝ ለመያዝ ያለ የሌለውን ኃይሏን ተጠቀማ ሳይሆንላት ሲቀር የነደፈችው የዘርና የጎሣ ሰነድ ነው።  በዘርና በጎሣ ከፋፍሎ ማዳከሙ ለጊዜውም ቢሆን ስርቶላት ነበር።ከሰባ ዓመት በኋላ ወያኔ በጎሣና በዘር መከፋፈሉን መሰሎኒ የጀመረውን ለፍፃሜ ለማድረስ ሃያ ሁለት ዓመት ተቀሳቅሷል ሆኖም ይህ ሰው በሰው የሚደረገው ጥፋት መቆም እንዳለበት እንደሃገር የምንነጋገርበት ወቅት የተቃረበ ይመስላል። ኢትዮጵያውያን እንደሃገር እንዳንነጋገር ያደረገን ፤የወያኔ አብዮታዊ ዲሞክረሲ ርዕዮተዓለም አስተሳሰብና ፖሊሲ የፈጠረው ችግር አይደለም። በሌላ መልኩ የትግራይ ሕዝብ ሕወሃትን ጠላው ወይም ሌሎች ፓርቲዎችን ተጠራጠረ ብሎ ችግሮች በአንድ ሕብረተስብ ክፍል ብቻ ማድበልበሉ ምናልባት አቅጣጫ ማስለወጥ ካልሆነ ፤ ችግሩ አንድና አንድ ብቻ ነው። ያም መላው ሕዝብ የሚጋረው ቸግር ነው። ወያኔ በሥራ ላይ ለማዋል የነደፈው የቅኝ ገዥዎች ሰነድ ነው።
እንደሃገር ስንነጋገር ይህን የትግራይ ሕዝብ ነፃነት ግንበር (ሕወሃት) የዘር ፖለቲካ  የሚያጸባረቀው ሰነድ  ወደቁሻሻ መጣል አለበት። ከዚያ ባለፈ በሕር ቀለም ቢሆን ሰማይ ብራና ሆኖ ብንለቀልቀው ወጤት የለውም። ግለሰቦችን ማውገዙ መግለጫ ማውጠቱ፤ግለሰቦች በሕዝብ ላይ ላደረሱት በደል በሒደት ፍርዱን ይቀበላሉ ። የማናገኘው የተፈፕሮ ሐብታችንና የሚተኩን ልጆቻችን አዕምሮ አጉልፋቶ እየሆነ ነው።ይህ ደግሞ ለባርነት የሚያዘጋጃቸው ነው። እዚህ ላይ የማይቀረውን የሞት ጽዋ ሁላችንም ቀማሾች ነን። ለቀሪው ወገናችን ምን አንተውለት? የሚከፋፍለውን ሠነድ?  ምድረበዳ ሃገር? መልሱን ለእናንተ ልተው!
ታደለ መኩሪያ
tadele@shaw.ca

ስንቱን አጣን! (ከፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም) | Zehabesha Amharic

ስንቱን አጣን! (ከፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም) | Zehabesha Amharic

የደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ተቃውሞ አሰሙ

ጥቅምት (አራት)ቀን ፳፻፮ / ኢሳት ዜና :-አዲሱን የትምህርት አመት ለመጀመር ምዝገባ ያጠናቀቁት ተማሪዎች ፣ ከአለባበስ ጋር በተያያዘ ባነሱት ተቃውሞ የግቢው መስታውቶችና አንዳንድ አገልግሎት መስጪያ እቃዎች መሰባበራቸው ታውቋል፡፤ ይህንንም ተከትሎ ፖሊስ ግቢውን መቆጣጠሩን ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ ተማሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል።
የተቃውሞው መነሻ የዩነቨርስቲው ባለስልጣናት ከቤተከርስቲያን መልስ ነጠላ ለብሰው ወደ መመገቢያ ክፍል የገቡትን ተማሪዎች ፣ ነጠላ ለብሳችሁ መግባት አትችሉም በማለት በመከልከላቸው ነው ።
ተማሪዎቹ “መብታችንን ልትገፉን አትችሉም” በሚል ጩሀት ሲያሰሙ እንደነበረም ታውቋል።
በአሁኑ ጊዜ ሁኔታው መረጋጋቱን የገለጹት ተማሪዎች፣ አጋጣሚው ተማሪው በውስጡ አፍኖ ያዘውን ነገር በአደባባይ እንዲተነፍስ እድል ሰጥቶታል ብለዋል።

ሙስሊም ኢትዮጵያውያን በነገው ኢድ-አል አድሃ ላይ ተቃውሞ እንደሚያሰሙ ታወቀ

ጥቅምት (አራት)ቀን ፳፻፮ / ኢሳት ዜና :-ለወራት ተቋርጦ የነበረው የድምጻችን ይሰማ ተቃውሞ ነገ በመንግስት ባለስልጣናትና በመጅሊስ መሪዎች ንግግር ላይ ተግባራዊ እንደሚሆን ከወጣው መርሀግብር ለማወቅ ተችሎአል።
በአዲስ አበባ ስታዲየም በሚካሄደው ዝግጅት የመንግስት ባለስልጣናትም ሆኑ የመጅሊስ አመራሮች ንግግር የሚያደርጉ ከሆነ ንግግሩ እስኪቆም ድረስ ተቃውሞው ይቀጥላል።
ተቃውሞው በመላ አገሪቱ እንደሚከናወን ድምጻችን ይሰማ ያወጣው መረጃ ያመለክታል።
ፖሊስ ጸጥታ ለማስከበር ዝግጅት ማድረጉን የፌደራል ፖሊስ ባወጣው መግለጫ ጠቅሷል። ላለፉት ሁለት አመታት መንግስትን ከፍተኛ ስጋት ላይ ጥሎት የነበረው የድምጻችን ይሰማ እንቅስቃሴ፣ የጸጥታ ሀይሎች እርምጃ ከወሰዱ በሁዋላ ለተወሰኑ ጊዜያት ጋብ ብሎ መቆየቱ ይታወሳል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በዛሬው እለት በወልድያ መስጊዶች ላይ በተንጠለጠሉ ማይክራፎኖች የመንግስት ባለስልጣናት የመልካም ምኞች መግለጫ ሲያስተላልፉ ውለዋል። በኢትዮጵያ የእስልምና ታሪክ ታይቶ አይታወቅም ያሉት ነዋሪዎች፣ ማይክራፎኖቹ የአዛን ወይም የጥሪ ማስተላለፊያ እንጅ የመንግስት ባለስልጣናት የመልካም ምኞት መግለጫዎች አይደሉም ብለዋል። በሀሉም መስጊዶች ” የወልድያ ምክር ቤት እንኳን ለኢድ አል አድሀ በአል በሰላም አደረሳችሁ” ብሎአል እየተባለ መልእክት ሲተላለፍ መዋሉን ግራ የተጋቡ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

Monday, October 14, 2013

ሸህ መሀመድ ሁሴን አል ዓሙዲ ቤቶችን ተነጠቁ



ጥቅምት (አንድ)ቀን ፳፻፮ / ኢሳት ዜና :-ከመንግስት ጋር ባላቸው ከመጠን ያለፈ ወዳጅነትና ቅርበት የሚታወቁት ሼህ መሀመድ ሁሴን አል-አሙዲ ለእግዶች ማረፊያ የተከራዩዋቸውን  ቤቶች እንደተነጠቁ የኢሳት ምንጮች ገለጹ።
ሼሁ፤ ከውጪ አገራት ለሚመጡባቸው እንግዶች በአያት ሲ.ኤም. ሲ   25 መኖሪያ ቤቶችን ለውጪ አገር ጎብኝዎች በተሰላ ሂሳብ ተከራይተው +በዶላር ምንዛሬ እየከፈሉ ሲገለገሉባቸው መቆየታቸውን የጠቀሱት እነዚሁ ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ  ምንጮች፤ መንግስት ባልተገለጸ ምክንያትና የኪራይ ውሉን በማፍረስ  25ቱንም   ቤቶች ሰሞኑን እንደነጠቃቸው አመልክተዋል።
ባለሀብቱ አገር ውስጥ በሌሉበትና ባላወቁበት ሁኔታ የተወሰደው እርምጃ ጉዳዩን በቅርብ የሚያውቁ የሚድሮክ ሠራተኞችንና የባለሀብቱን ወዳጆች ማስደንገጡ ታውቋል።  አል-አሙዲ በኪሳራ ምክንያት የተዘጋውን የካራቱሪን እርሻ ጠቅልለው ሳይገዙት አይቀርም የሚል ወሬ በስፋት እየተሰራጨ ባለበት ጊዜ  መንግስት በድንገት ይህን እርምጃ መውሰዱ ከመለስ ሞት በሁዋላ የባለህብቱና-የመንግስት ግንኙነት እየሻከረ መምጣቱን ጠቋሚ ነው ብለዋል-ዜናውን ያደረሱን ወገኖች።

የጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ እህት ይቅርታ እንድትጠይቅ ተጠየቀች

ጥቅምት (አንድ)ቀን ፳፻፮ / ኢሳት ዜና :-በእስር ላይ የምትገኘው የጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ እህት እስከዳር ዓለሙ የቃሊቲ ማረሚያ ቤትን ይቅርታ ካልጠየቀች እህቷን መጎብኘት እንደማትችል ተገለጸላት።
እስከዳር”  አስቂኝም፤አስገራሚም ነገር”በሚል ርዕስ  በፌስ ቡክ ገጿ ላይ እንዳሰፈረችው፦ማረሚያ ቤቱ በደብዳቤ ይቅርታ ካልጠየቅሽ ሁለተኛ እህትሽን አታያትም እንዳላት ገልጻለች።
“ሰብዐዊ ጥሰት የተፈፀመብን ፣ የተጉላላን ፣ የተሰደብን ፣ የተዛተንብ፣የተደበደብን . . . እኛ፡፡ ይሄ ሆኖ ሳለ ነዉ እንግዲህ በእህትሽ ጉዳይ የማረሚያ ቤቱን ስም በየመፅሔቱ አጥፍተሻል  የተባልኩት። ስም ማጥፋት የተባለውም ስለርዕዮት የረሃብ አድማንና ስለ ተፈፀመባት የሰብአዊ መብት ጥሰት መግለጼ ነው”ብላለች-እስከዳር ዓለሙ።
” ስለዚህ ነው ይቅርታ ጠይቂ የተባልኩት” ያለችው እስከዳር፤  “እኔ የምለዉ እነዚህ ሰዎች ይህንን ይቅርታ እንዴት ነዉ የሚወዱት?!!”በማለት  ጠይቃለች።

ከ15 ሺ በላይ የኢህአዴግ አባላት መልቀቂያ አስገቡ

ጥቅምት (አንድ)ቀን ፳፻፮ / ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ እያካሄደ ባለው የአባላት ግምገማ ወቅት ከ15 ሺ በላይ አባላት በአንድ ጊዜ መልቀቂያ ማስገባታቸው ይፋ ተደርጓል።
ስራቸውን ከሚለቁበት ምክንያቶች መካከል  በድርጅቱ አመኔታ ማጣት ፣ ተገቢውን አገልግሎት ክፍያ አለማግኘት፣ ለድርጅቱ የሚከፍሉት ገንዘብ ከፍተኛ መሆን እና የድርጅቱ አባላት ሹመት በወገን መሆኑ የሚሉት ተጠቅሰዋል።
ከፍተኛ የአባላት መልቀቂአ ቁጥር ከተመዘገበባቸው ክልሎች መካከል ኦሮሚያ በ9 ሺ 4 መቶ 56 አንደኛ ሲሆን ፣ አማራ፣ ደቡብ ክልል እና ትግራይ በተከታታይ ያሉትን ደረጃዎች ይዘዋል። በትግራይ በ2005 ዓ/ም 1 ሺ 1 መቶ 13 ሰዎች የህወሀት አባላት መልቀቂያ አስገብተዋል።
ኢህአዴግ 5 ሚሊዮን አባላት እንዳሉት ቢነገርም ፣ በንቃት የሚሳተፉት 2 ሚሊዮነቹ ብቻ ናቸው ተንብሎአል። ከእነዚህ መካከል 20 ሺ የሚሆኑት በስም ብቻ አባላት ተብለው ቢመዘገቡም፣ በአካል የሌሉ መሆናቸውም ተገልጿል።
በስብሰባው አብዛኞቹ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ለደሞዝና ለስራ ሲሉ አባል እንደሚሆኑ የተገለጸ ቢሆንም በአለፉት አመታት ድርጅቱን ከተቀላቀሉት ተማሪዎች መካከል ስራ አገኙት ሩብ አይሆንም ተብሎአል።
በክልል ዋና ዋና ከተሞች በአዋሳ፣ ባህርዳር፣ እና መቀሌ ውጤት ያላቸው ተመራቂዎች ስራ ሳይዙ፣ ውጤት የሌላቸው የድርጅቱ ነባር አባላት በተቃራኒው ስራ መቀጠራቸው በአባላቱ ላይ ቅርታ እንዲፈጠር አድርጎአል ተብሏልም ።
ዛሬ ስራ ማግኘት የህልም እንጀራ ነው ያሉት አባሎች፣ ዲግሪ ይዘው ስራ ለማግኘት ከሶስት እስከ 4 አመታት የሚጠብቁ ተመራቂዎች መኖራቸውን ተናግረዋል።
ኢህአዴግ መልቀቂያ ያቀረቡ አባላቱን ጥገኞች ሲል ሰይሞአቸዋል። የድርጅቱ አባላት ለኢሳት እንደገለጹት አብዛኞቹ የብአዴን ከፍተኛ አመራሮች በሙስና የተዘፈቁ ናቸው። ኢሳት በሚቀጥለው ሳምንት <<የድርጅት አባላት እንዲያውቁት>> በሚል የብአዴን የአመራር አባላት ሙስናን በተመለከተ የላኩትን ደብዳቤ ይፋ እንደሚያደርግ ለመግለጽ ይወዳል።
በተመሳሳይ ዜናም አክራሪነትና ጽንፈኝነትን አስመልክቶ ስልጠና ለመስጥት የፈዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ከሐረማያ ዩንቨርስቲ ጋር በመተባበር ትናንት ያደረገዉ ስብሰባ ያለዉጤት ተበትኗል።
መንግስት ንጹሀንን ያለምንም መረጋገጫ አክራሪ አሸባሪ ብሎ መፈረጁ ግዜ ያለፈበት ነው”ያሉት የስብሰባው ተሳታፊዎች፤”በመንግስት እየተባለ ያለውን ነገር+ እንኳን  የዩንቨርስቲዉ ማህበረሰብ ፤ሳይማሩ እያስተማሩ ያሉት እናት አባቶቻችንም አይቀበሉትም “ብለዋል።
ተማሪዎችና መምህራን  በማከልም፦”የመረጃ ምንጫችን ኢቲቪ ብቻ ነው ብላችሁ የምታስቡ ከሆነ ተሳስታችሗል” በማለት  የመንግስት ባለስልጣናትን ሞግተዋቸዋል።
“ጽንፈኛ” የሚለዉ ቃል በባርያ ፍንገላ ግዜ በባሪያ አሳዳሪዎች ላይ ያምጹ ለነበሩ ግለሰቦች የተሰጠ ስያሜ ነው በማለት የተናገሩት  አንድ ክርስቲያን የሆኑ የስብሰባው ታዳሚ፤ “መንግስት የእስልምና ሐማኖት ተከታዮች  በክርስቲያኑ ላይ ጦርነት ሊያዉጁ ነው ብሎ ቢናገር ፤ህዝበ ክርስቲያኑ አይቀበለውም”ብለዋል።
ግለሰቡ አስተያየታቸውን ሲያጠቃልሉም፦ኢትዮጵያ ዉስጥ አክራሪ አለ ማለቱ አለማቀፋዊ እዉቅናን ያላገንኘና ተዓማኒት የሌለዉ መሆኑን ገልጸዋል።
እንደ ቢ.ቢ.ኤን ዘገባ፤በስብሰባው ላይ በዩንቨርሲቲዉ ሶላትና ሂጃብን አስመልክቶ እገዳ ለማድረግ እቅድ እንዳለ የቀረበው ሃሳብ በሁሉም ተሳታፊዎች ከፍ ያለ ተቃውሞ ገጥሞታል።
“ኢትዮጵያን ልክ እንደ አፍጋኒስታንንና ፓኪስታን ችግር ያለባት ማስመሰሉ ተገቢ አይደለም፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ተቻችሎ ያለ በመሆኑ ያንዱ ወገን ሐይማኖት መከበር ለሌላዉ ስጋት አይደለም፤”ያሉት ተሳታፊዎቹ፤ ሰዎችአለባበሳቸዉን ከቀየሩ አመለካከታቸዉን ይቀይራሉ ማለቱ  ስህተት ስለሆነ “ሀይማኖታዊ አለባበስ ከዩኒቨርሲቲ በር መልስ”የሚለው ሃሳብና እቅድ ተቀባይነት የለውም”ብለዋል።
የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር  በሐረማያ ዩኒቨርስቲ” አክራሪነትንና አሸባሪነትን” አስመልክቶ ባዘጋጀዉ በዚህ  ስልጠና ላይ እስከ አስራ ሁለት ሺ የሚጠጉ ተማሪዎች ተሳትፈዋል።
ይሁንና በርካታ ተማሪዎች የመንግስት ባለስልጣናት የሚያቀርቡትን ሐሳብ ፊት ለፊት በንግግር ከመቃወማቸውም በላይ   ስብሰባዉን ረግጦ ወጥተዋል።

ቅዳሜ ዕለት የታሰሩት የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና አመራሮች ዛሬ ከሰአት ፍርድ ቤት ይቀርባሉ፡፡

ቅዳሜ ዕለት የታሰሩት የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና አመራሮች ዛሬ ከሰአት ፍርድ ቤት ይቀርባሉ፡፡
ቅዳሜ እለት በጃንሜዳ ፖሊስ ማዘዣ ጣቢያ ታስረው የነበሩ የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና አመራሮች ችሎት አካባቢ ወደሚገኘው ወረዳ 9 ፖሊሰ ጣቢያ ተወስደው 2 ቀን እንዲያድሩ ከተደረጉ በኋላ ዛሬ ጠዋት ወደ ጃንሜዳ ፖሊስ ጣበያ ተመልሰው የተወሰዱ ሲሆን አሁንም በጃንሜዳ ፖሊስ ጣቢያ ይገኛሉ፡፡ በወረዳ 9 የ2 ቀን ቆይታቸውም የፖሊስ አባላት በግዴታ የወንዶቹን ፀጉር የቆረጧቸው መሆኑ ተረጋግጧል፡፡አባላቱ ዛሬ በ8 ሰአት ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ የተነገራቸው ሲሆን በጃንሜዳ ፖሊስ ጣቢያ የፓርቲው አባላትና ከፍተኛ አመራሮች እየጠየቋቸው ይገኛሉ፡፡

የኢህአዴግ አፈና አሁንም እንደቀጠለ ነው!! (ጥቅምት 2 ቀን 2006 ዓ.ም ከምሽቱ 1 ሰዓት)

ሰማያዊ ፓርቲ ለጽ/ቤት መጠቀሚያ ተከራይቶ ነበረውን ቢሮ በግድ ካልወጣችሁ ሲሉ ከነበሩት የጉለሌ ክ/ከተማና ወረዳ 03 ካድሬዎች መካከል በተነሳው ውዝግብ መፍትሄ ለማፈላለግ መሀከል የገባው የመነን አካባቢ ፖሊስ በውይይት ለመፍታት ሁለቱም አካላት ከቤቱ እንዲወጡና ፖሊስ ቤቱን እንዲጠብቅ፤ በቀጣዩ ቀን ለመነጋገር ስምምነት ተይዞ የፓርቲው አባላት ወደቤታቸው ለመሄድ ከጽ/ቤቱ ለቀው ቢሄዱም ከመንገድ ላይ
1.ወ/ት ሀና ዋለልኝ (የሴቶች ጉዳይ ኃላፊ)
2.አቶ ዮናስ ከድር (የምክር ቤት አባል)
3.ወ/ት እየሩስ ተስፋው
4.አቶ ዮናታን ተስፋዬ
5.አቶ አቤል ኤፍሬም
6.አቶ አህመድ መሀመድ
7አቶ እያስፔድ ተስፋዬ
የአራዳ ክ/ከተማ ፖሊስና የደህንነት አካላት ወደ ጃልሜዳ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ወስደው በቁጥጥር ስር እንዳዋሏቸው አሁን በደረሰን መረጃ ማወቅ ተችሏል፡፡ ከዚህ በፊት እንደሚታወሰው የጃልሜዳ አካባቢ ፖሊስ የፓርቲውን አባላት እያሰረ ይደበድብ እንደነበረ ፤ አሁንም ከአንድ ሰአት በላይ አባሎቹን ምን እያደረጋቸው እንደሆነ ማወቅ አለመቻሉ እየተደበደቡ ይሁን? የሚለውን ስጋት በከፍተኛ ሁኔታ አጭሯል፡፡

በ1ኪሎ ቁርጥ ሥጋ እና በ12 ድራፍት ብርጭቆ – እውነትና ከሕደት…

http://ecadforum.com/Amharic/archives/9967/

በ1ኪሎ ቁርጥ ሥጋ እና በ12 ድራፍት ብርጭቆ – እውነትና ከሕደት…

October 14, 2013
በይድነቃቸው ከበደ
(የሰማያዊ ፓርቲ የህግ ጉዳይ ሀላፊ)
ኪነ-ጥበብ ምኞታችን፣ደስታችን፣አዘናችንን እና ክፋታችን የምናይበት እና የምናዳምጥበት የህይወታችን ነፀብራቅ ነው፡፡ ኪነ-ጥበብ ህይወትን ቀለል አድርጎ ከማዝናናት ባለፈ በገለሰብ አስተሳሰብ ላይ የራሱ የሆነ በጎ ወይም በጎ ያልወነ አስታውጾ የሚያበረከት ጥበባዊ ሃይል ነው፡፡ይህ ሃይል በመልካም አስተሳሰብ ላይ ተመስርቶ ወደ ህብረተሰቡ ውስጥ ሲገባ የሚኖረው አገራዊ ፋይዳ እጅግ በጣም የበዛ ነው፤፤ በመሆኑም ኪነ-ጥበብ እንዲህ አይነቱ ጠቀሜታ እንዲኖረው የሚያደርጉት በጥበብ ሙያ ውስጥ የሚገኙ ባለሙያዎች ናቸው ፤እነኚህ ባለሙያዎች ሙያቸው ከመሬት የፈለቀ ሣይሆኖ በልምድና በት/ት የዳበረ ጥበባዊ ተስጥኦ ነው፡፡
ከኪነ-ጥበብ ዘርፎች ውስጥ ከሚመደቡት አንዱ ቴአትር ነው፤ ቴአትር በአገራችን ያለው ተቀባይነት ቀላል የሚባል አይደለም ፤ቴአትር አሁን ያለበት ደረጃ ለመድረስ የቴአትር ባለሙያዎች የከፈሉት ዋጋ ከዕድሜቻው፣ ከገንዘባቸው እና ከዕለት ተዕለት ማህበራዊ ህይወታቸው ላይ ጎምዶ ያስቀረባቸውን የሚያውቁት ዋጋውን የከፈሉት እነሱ ብቻ ናቸው፡፡ ቢሆንም በቴአያትር ጥበብ የዝወትር እንቅስቃሴችን መጥፎዉንና የተሸለውን በመለየት ጥበባዊ በሆነ መንገድ እየተዝናናን እንድንማርበት ለሚያደርጉ የቴአትር ባለሙያዎች ስራዎቻቸውን ስንመለከትና ስናደምጥ እውነትም ለሙያው እድገት የተከፈለ ነገር እንዳለ ያስገነዝበናል፡፡
ስለሆነም ለቴአትር ባለሙያዎቻችን ከትላንት ዛሬ የምንሰጣቸው ከበሬታና አድናቆት የሚበረታታና የሚያስደነቅ ነው፤ይህ ደግሞ ለቴአትሩም እድገት የሚጠቅም ነው፡፡ይሁን እንጂ በቀርብ በብሔራዊ ቴአትር ቀደምት ባለሙያዎች ላበረከቱት አስታዋጽኦ በማስታወስ የሽልማት ፕሮግራም የተዘጋጀ ቢሆንም ዝግጅቱ እውነትና ከሕደት የተቀላቀለበት ነበር፡፡
‹‹……. ቀደምት ባለሙያዎች እንዲገናኙና ባለፈው ላደረጉትም አስታውጽኦ ሽልማት መሰጠቱ ተገቢነት ያለው ድርጊት ነው፡፡ባለሙያዎቹ ሲገናኙና በመነፋፈቅ ፈቅራዊ ሰላምታቸውን ሲለዋወጡ ስመለከት እጅጉን ደስ ብሎኝ ነበር የምከታተለው፡፡ እየቆየሁ ሲሄድ በውስጤ ቅሬታ ተሰማኝ በብሔራዊ ቴአትር በተከናወነው ስርአት ላይ በሞት የተለዩትን ተነሱ፤ በነፍስ ያሉት ግን ተገኝተው የሚመሰገነው ተመሰገነ፤ የሚሸለመው ተሸለመ እዚህ ላይ ነው ቅድም የጀመረኝ ቅርታዬ የበረታብኝ፡፡………. ››
በማለት በብሔራዊ ቴአትር ቤት የተካሄደውን ሽልማት ስነስርአት በኢቲቪ ፕሮግራሙን ሲከታተል የነበረ ሰው ትዝብቱን እና ቁጭቱን በሎሜ መፅሔት በባለፈው ሳምንት ዕትም ላይ ያስነበበን፡፡
እኔም የሰውዬውን ትዝበት እና ቁጭት አብዝቼ የምጋራው ነው፤ አርቲስት ደበበ እሸቱ በሙያው ከበሬታን ያተረፈ ለብሔራዊ ቴአትር ቤት እድገት የተቻለውን አስታውጾኦ ያበረከተ እና በህይወተ ከቀሩልን አንጋፋ አርቲስቶች መካከል አንዱ ስለመሆኑ ማንኛውም ሰው የሚሰጠው ምስክር ነው፡፡እውቁ አርቲስት ደበበ እሸቱ  ተዋናይ፣ኮሜዲያን፣ አዘጋጅ ሆነ ለረዥም ዓመታት አገልግሏል፡፡ በመድረክ ፣ በሬዲዩ፣ በቴሌቪዥን፣ በፊልም ስራ እና በጋዜጠኝነት ሙያ ሠርቷል፡፡ ቤተ መንግስት ተገኝቶ አፄ ኃይለሥላሴን  ከሥልጣን ሲወርዱ ያነጋገራቸው ጋዜጠኛ ደበበ እሸቱ ነው፡፡ የተለያዩ ሃላፊነቶችን ይዞ ሠርቷል ፤ በአፍሪካ የመድረክ ሙያተኞች ማህበር በሊቀመንበርነት መርቷል እንዲሁም በአትላንታ አንድ ቀን በስሙ ተሰይሞለታል፡፡ የአርቲስት ደበበ እሸቱ የጥበብ  እረዥሙ የህይወት ጉዞ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ኪነጥበባት ወ ቴአትር ተጀምሩ በብሔራዊ ቴአትር የቀጠለ ሲሆን  በአገር ፍቅር ቴአትር ቤት ያበቃ ነው፡፡
ስለ አርቲስቱ ካነበብኩት እና ከማቀው ይህን ብልም ከእኔ እውቀት ማነስ ያስቀረውበት መልካም የሆኑ ስራዎቹ እንደሚኖሩት ተስፋ አደርጋለው፡፡ በመሆኑም በብሔራዊ ቴአትር ቤት በተካሄደው የማስታወስ እና የሽልማት ስነስርአት ላይ አርቲስት ደበበ እሸቱን ለማስታወስም ሆነ ለመሸለም አለመቻሉ ከምን እንደመነጨ አንድ ለበዓሉ ዝግጅት ቅርብ የሆነ ለሆዱ ያደራ አርቲስት በ1ኪሎ ቁርጥ ሥጋ እና በ12 ድራፍት ብርጭቆ በፈጀ ወጪ እውነትና ክሕደትን ዘርዝሩ የተናገረው፡፡ ይህን ሰው ሆድ አደር ያልኩበት ምክንያት የሚያውቀውን እውነት በፍራቻ ምክንያት በአደባባይ አለመግለፁ እንዲሁም የዝግጅቱ አስተባባሪ ከሆኑት ውስጥ አንዱ እንደመሆኑ መጠን የራሱን እምነት ወይም አቋም በዝግጅቱ ሂደት ላይ ምንም ሳይገልፅ ሌሎችን ለመኮነን የሄደበት መንገድ ነው፡፡
ይህ ለበዓሉ ዝግጅት ቅርብ የሆነው አርቲስት የቀረበለትን ምግብ እና መጠጥ እየጠጣ አርቲስት ደበበ እሸቱ በሙያው አንቱታን ያተረፈ ለቴአትር ሙያ እድገት አስታውጾኦ ያበረከተ መሆኑ እና በቀድሞ የሙያ አጋሮቹ ፍቅርና ከበሬታ ያለው መሆኑን ምግብና መጠጥ ለጋበዘው ሰው ገልጾአል፡፡ ንግግሩን ሲቀጥል ‹‹ ደቢሾ የተቃዋሚ ፓርቲ አባል  ስለሆነ በፕሮግራሙ ላይ እንዲሳተፍ አልተፈለገም ፤ በሱ ጉዳይ ላይ ስንቱ አፈ ልጉም ሁሉ ልወደድ በሚል አፉን ፈታ መሰለህ፡፡ የሚገርመው ግን ደቢሾ ወደ ቴአትር ቤት አንድ ሁለት ጊዜ መጥቶ በነበረ ጊዜ ሁሉም እንዴት እየተንደረደሩና እላዩ ላይ እየተጠመጠሙ እንደሚስሙት አይ ነበር እነዚያው ሰዎች አሁንም እንዳይጠራ ብለው ሲሞግቱ  በጣም ነው የተገረምኩት ፡፡ ዋናው ደግሞ ስራ አስኪያጁ እንዴት እንደተቃወመና በጭራሽ ሊጠራ አይገባም ፤ እሱ የሚጠራ ከሆነ እኔ በበዓሉ አልገኝም ስራዬንም እለቃለው አለ ! በቃ ያንን ስንሰማ ሁላችንም ፈራን………..  ስማ  እንግዲህ ይህ  በእኔና ባንተ የሚቀር የግል ጨዋታ ነው፤ የኔን ስም በጽሁፍም ሆነ በግልም ለደቢሾም ቢሆን እንዳታነሳ፤ አደራህን ነገ የሚሆነውን ማን ያውቃል ? ›› በማለት የነገሩን ሂደት ሰፋ አድርጎ የገለፀው፡፡
ውድ አንባቢያን 1ኪሎ ቁርጥ ሥጋ እና 12 ድራፍት ብርጭቆ የፈጀ ወጪ በመሸፈን በብሔራዊ ቴአትር ቤት የተካሄደውን የሙያ ክሕደት እውነቱ እንዲወጣ ያደረገው አርቲስት እና ምግብና መጠጥ አሸንፎት እውነቱን የተናገረው ሌላኛው አርቲስቲ ሙሉውን ታሪክ መስከረም 18 ቀን 2006 ዓ.ም በወጣው ሎሚ መፅሔት ላይ ማግኘት ይቻላል፡፡
ወደ መነሻዬ ልመለስ እና አርቲስት ደበበ እሸቱ እድሜ ልኩን በሙያው ያገለገለ እውቅ አርቲስት ነው ፡፡ በዚያው መጠን አሁን ባለው በገዢው ስርዓት ለታየው ብልሹ አስተዳደር ግንባር ቀደም በመሆን ሲተች እና ሲታገል ነበር በዚህም ምክንያት ለተደጋጋሚ እስር እና ለተደጋጋሚ ይቅርታ ጥያቄ ተዳርጓል፡፡ ይህ ግለሰባዊ የፖለቲካ አስተሳሰብ  በኪነ-ጥበብ ውስጥ ላበረከተው በጎ አስታውጾ በየትኛውም በኩል መመዘኛ ሊሆን አይገባም !!! እርግጥ ነው ገዢው መንግስታችን ለልማታዊ አርቲስቶች ያለው ድጋፍ ቀላል የሚባል አይደለም ፤ ልማታዊ አርቲስቶችም ለኢህአዴግ መንግስት ያላቸው ድጋፍ ወደር አይገኝለትም፡፡
አርቲስቶቻችን ሰው እንደመሆናቸው መጠን የራሳቸው የሆነ የሃሳብ ነፃነት ያላቸው ሲሆን በዚህ መብታቸው በመጠቀም የሚፈልጉትን የፖለቲካ አስተሳሰብ የመደገፍ ሳይመስላቸው ሲቀር የመተቸትና የመቃወም መብታቸው የተጠበቀ ነው፡፡ ነገር ግን ይህን ተፈጥራዊ የሃሳብ ነፃነት መብት በሃይል ወይም በጥቀማጥቅም በመደለል እና በማስገደድ የአንድ የፖለቲካ ስርአት ብቻ ደጋፊና አቀንቃኝ ማድረግ የሞራል ጥያቄ ያስነሳል፡፡
በመሆኑም እንዲህ አይነቱ አካሄድ ለአርቲስቱም ሆነ ለሙያው እድገት ጉዳት እንጂ ጠቀሜታ የለውም፡፡ በአገራችን የፖለቲካው ስርአት ሲለወጥ የአገር መከላኪያ ሠራዊት ( ጦሩ) እየተለወጠ በአዲስ መልክ እየተቋቋመ ተቸግረናል ፡፡ አሁን ደግም  የመከላኪያ ሠራዊት ( ጦሩ) ብቻ ሳይሆን አርቲስቶቻችንም ከፖለቲካ ስርአታችን ጋር እየተቀየሩ በአዲስ መልክ ልናያቸው ይሆን ? ፡፡ እንዲህ አይነቱ አደገኛ ከስረት ውስጥ ከመግባታችን በፊት የነገሩን አካሄድ ሊመረመር ይገባል ፡፡
በመሆኑም በአርቲስት ደበበ እሸቱ ላይ የተፈጸመው የሙያ ከሕደት እጅግ በጣም የሚያሳዝን እንዲሁም የሚያሳፍር ነው፡፡ ከምንም በላይ ደግሞ አገርን አስተዳድራለው ከሚል መንግስት እንደሰፈር ጉልበተኛ ጎረምሳ እልህ በመጋባት በአርቲስቱ ላይ የሙያ ከሕደት እንዲፈፀም ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ያልሆነ አስታውጾኦ በመንግስት ካድሬዎች በመፈጸሙ ሌላኛው አሳፋሪ እንዲሁም አስቂኝ ነገር ነው፡፡
ስለዚህም ለእውነት ያደሩ ሙያተኞች እንዲህ አይነቱን አሳፋሪ ተግብር ለህዝብ ከማጋለጥ ባለፍ ለሙያቸው እና ለእራሰቸው እድገት የሚበጀውን ቀና መንገድ ለማምጣት ውጫዊ እና ውስጣዊ ሙያዊ ትግል ሊያካሂዱ ይገባል፡፡ በተጨማሪ በቀብር ስነስርአት ላይ ጥቁር ለብሶ እና በእመም ጊዜ ለመታከሚያ ገንዘብ ለመሰብሰብ ከመታየት በለፈ በሙያቸው እውቅ የወኑትን አርቲስቶች በህይወት እያሉ በማሰብ እና በማበረታታት ሙያዊ አጋርነታቸውን ለእውነት የቆሙ አርቲስቶች ሊያሳዩን ይገባል፡፡

Hiber Radio: “ተስፋዬ የወያኔን ዓላማ ለማሳካት ኢትዮጵያውያንን ለማጋጨትና በተወሰኑ የኦነግ ሰዎች ሞገስ ለማግኘት ሆን ብሎ እየሰራ ነው” ዳኛ ወ/ሚካኤል ቃለምልልስ | Zehabesha Amharic

Hiber Radio: “ተስፋዬ የወያኔን ዓላማ ለማሳካት ኢትዮጵያውያንን ለማጋጨትና በተወሰኑ የኦነግ ሰዎች ሞገስ ለማግኘት ሆን ብሎ እየሰራ ነው” ዳኛ ወ/ሚካኤል ቃለምልልስ | Zehabesha Amharic

Sunday, October 13, 2013

ስብሃት ነጋን አጅበው አክቲቪስት መስፍን ላይ ድብደባ የፈጸሙት ግለሰቦች ማንነት ታወቀ | Zehabesha Amharic

ስብሃት ነጋን አጅበው አክቲቪስት መስፍን ላይ ድብደባ የፈጸሙት ግለሰቦች ማንነት ታወቀ | Zehabesha Amharic

ስብሃት ነጋ ወንጀል ፈፀሙ፤ በአሁን ሰአት በፖሊስ እየታደኑ ነው

http://ecadforum.com/Amharic/archives/9965/

ስብሃት ነጋ ወንጀል ፈፀሙ፤ በአሁን ሰአት በፖሊስ እየታደኑ ነው

October 13, 2013
ከኢየሩሳሌም አርአያ
በአሌክሳንደሪያ ቨርጂኒያ ከአንድ ሰአት በፊት ስብሃት ነጋና አብሯቸው የነበረ ግለሰብ በአንድ ኢትዮጲያዊ ላይ ከፍተኛ ድብደባ ፈፅመው ማምለጣቸውን ማረጋገጥ ተችሏል። መስፍንsebehat nega one of the founders of TPLF የተባለው ኢትዮጲያዊ በአሁኑ ሰአት በሆስፒታል የሚገኝ ሲሆን የሲቪሊቲ ሩም ፓልቶክ አዘጋጅ አባ መላ በስልክ አግኝቶት ስለሁኔታው ያነጋገረው ሲሆን፤ መስፍን እንደገለፀው በድብደባው ጅርባው እንደተጎዳና ብዙ ደም እንደፈሰሰው ገፆዋል። እነስብሃት ድብደባውን ሲፈፅሙ በቅርብ ርቀት ቪዲዮ እየተቀረፁ እንደነበረና ይህኑን ማስረጃ ለፖሊስ መስጠታቸው ታውቋል። ድርጊቱ ከተፈፀመ በኋላ ፖሊስ በአካባቢው ፈጥኖ የደረሰ ሲሆን፣ በአሁን ሰአት እነስብሃትን ለመያዝ ፖሊስ መሰማራቱ ታውቋል።

ይቺ ባንዲራ! – ከተመስገን ደሳለኝ (ጋዜጠኛ) | Zehabesha Amharic

ይቺ ባንዲራ! – ከተመስገን ደሳለኝ (ጋዜጠኛ) | Zehabesha Amharic

Thursday, October 10, 2013

The most successful Ginbot 7 popular Force fund raising event in oslo se...

የአማራ ክልል የድንበር ከተሞች ለአጎራባች ክልሎች ሊሰጡ ነው፡፡


http://freedom4ethiopian.wordpress.com/2013/10/09/699/

የአማራ ክልል የድንበር ከተሞች ለአጎራባች ክልሎች ሊሰጡ ነው፡፡

የአማራ ክልል የድንበር ከተሞች ለአጎራባች ክልሎች ሊሰጡ ነው፡፡

ኢሳት ከአማራ ክልል ባለስልጣናት ባገኘው መረጃ የጃን አሞራ፣ የማይጸብሪ አዋሳኝ፣ ራስዳሸንን ጨምሮ የአዲአርቃይን አካባቢዎች ወደ ትግራይ፣ በመተማ በኩል ደግሞ የተወሰነውን ክፍል ለቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለመስጠት ድርድር በመካሄድ ላይ ነው።
ባለስልጣናቱ ቀደም ብለው የህዝቡን የልብ ትርታ ለማዳመጥ ጥረት ሲያደርጉ እንደነበር የደረሰን መረጃ የሚያመለክት ሲሆን፣ አንዳንድ የወረዳ ባላስልጣናት ጉዳዩን ወደ መድረክ እንድናወጣላቸው ተማጽነዋል።
መንግስት ከአሁን በፊት በአማራ ክልል ስር የነበረውን የመተከል ዞን ለቢኒሻንጉል ጉምዝ ፤ራያና ቆቦ ፤ዳንሻ እና ሁመራ ፤በመተማ በኩል ለሱዳን ፤የመተማ ቀሪው ክፍል ለቤንሻንጉል ፣ በሰሜን ሺዋ በኩል ለኦሮምያ የልማት እገዛ በሚል መሰጠቱን በማውሳት ፣ አሁንም ተጨማሪ መሬት እየተቆረሰ ክልሎችን ለማስደሰት እየዋለ ነው በማለት ቅሬታቸውን ገልጸዋል።
የአንቀጽ 39 ቱርፈቶች የሰጡን ገፀ በረከቶች ናቸው ሲሉ የአማረሩት የድንበር ከተማ ነዋሪዎች፣ ”ጨለምተኛ አባት መሬት እየሸጠ ልጆቹን ከእርስት ይነቅላል፡፡ ጨለምተኛ መንግስት አገርን በመሸጥ ዜጎችን ያስደፍራል፡፤ ምንነታቸውን ያሳጣል መንግስትም ማንነታችን እየነጠቀን ነው ሲሉ” ገልጸዋል።
ሁኔታው ያበሳጫቸው ነዋሪዎች በአገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ ድርጅቶች ጉዳዩን አጽንዎት ሰጥተው ሊያዩት ይገባል ብለዋል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ የትግርኛን ቋንቋ በአማራ ክልል ተማሪዎች እንዲማሩት ለማድረግ ታስቦ በጎንደር በተካሄደው የፓይለት ጥናት ህዝባዊ ተቃውሞ በማስነሳቱ እንዲቆም ተደርጓል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የቋንቋ ጥናት ባለሙያ የሆኑት ፕሮፌሰር ባየ ይማም በቅርቡ በአቀረቡት ጥናት የመንግስት ቋንቋ አጠቃቀም ‘የህዝብን ጉዳይ በህዝብ ቋንቋ’ የሚለውን መርህ የተከተለ ባለመሆኑ ህዝቡ ማግኘት ያለበትን መልእክት በትክክል እያገኘ፤ ለለውጥም እየተነሳሳ አይደለም ብለዋል፡፡ ባጭር ቃል በዚህ አይነት ቋንቋ የሕዝብን አእምሮ መቀየር እንደማይቻል የገለጹት ፕሮፌሰሩ፣ባለስልጣናቱ የአማረኛ ቋንቋ እንዲጠፋ የበኩላቸውን እየተወጡ ነው ብለዋል፡፡
“ሀገራችን የቋንቋ ፖሊሲና የአጠቃቀም ደንብ ወይም ስርዓት እስካሁን የላትም፡፤ እስካሁን ድረስ ከህገመንግስታዊ የመብት ማረጋገጫ አንቀጾች ያለፈ፣ ቋንቋን እንደ ማንኛውም የሀገር ሀብት በእቅድ የሚያሳድግ፣ የሚቆጣጠር፣ አጠቃቀሙን ስርዓት የሚያሲዝ ፖሊሲና ዝርዝር ደንብ የለንም፡፡ ባለመኖሩም ሁሉም እንደፈለገ የሚተረጉምበት፣ የሚጽፍበት፣ የሚያሰራጭበት ሁኔታ ውስጥ ገብተናል፡፡ ይህ ሊቆምና ቋንቋዎቻችን በዕቅድ ሊያድጉና ጥቅም ላይ ሊውሉ ይገባል” ሲሉ ፕሮፌሰሩ ተናግረዋል።
ፕሮፊሰር ባየ ይማም ለቋንቋው ድክመት የመንግስት ባለስላጣናት ተጠያቂ መሆናቸውንም ገልጸዋል።
አማርኛ ቋንቋ የሀገሪቱ የስራ ቋንቋ መሆኑ እየታወቀ ክልሎች በፍፁም ጥላቻ እንዲያድርባቸው እንዲሁም ክፍል ውስጥ ገብተው የመማርን መብት ለተወላጆች ብቻ ትቻለሁ በማለት የአማርኛ ትምህርት ክፍለ ጊዜዎች ፤ በትግራይ ፤ ኦሮምያ፤እና ደቡብ ልልኦች ክፍት ይሆናሉ።
ተማሪዎች በቋንቋ ትምህርት በሚመዱበበት ወቅትም በአማርኛ ቋንቋ የሚሰጡ ደጋፊ ትምህርቶችን ላለመማር አሰጣ አገባ እንደሚገቡ ታውቁዋል፡፡
በኦሮሚያ፣ በትግራይ፣ በቤንሻንጉል እና ሶማሊ ክልሎች የክልሎቹን ቋንቋ የማይናገሩ ተማሪዎች ተመርቀው ስራ ለማግኘት አይችሉም። በመሆኑም ከአማራ ክልል የሚመጡ ተማሪዎች ከክልላቸው፣ ከአዲስ አበባ እና ከደቡብ ክልል ውጭ በሌሎች ክልሎች ተቀጥረው ለመስራት እየተቸገሩ ነው።
አንዳንድ ልዩ ችሎታ ያላቸው ወይም መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ውስጥ ተቀጥረው ለመስራት ካልሆነ በስተቀር የአማራ ክልል ተማሪዎች ስራ ለመያዝ እንደሚቸገሩ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ሰዎች ገልጸዋል።
በሌላ በኩል ግን አማርኛ የሚችል የማንኛውም ክልል ተወላጅ በአማራ ክልል ተወዳድሮ ስራ የመያዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አስተያየት ሰጪዎች እንደሚሉት በኢትዮጵያ ውስጥ እንደልብ ተዘዋውሮ የመስራት እና የመኖር መብት በእጅጉ ተገድቧል።
posted by Aseged Tamene

Hailemariam Defends Anti-Terror Law, Condemns Critics (Video)


http://www.awrambatimes.com/?p=10680

Hailemariam DesalegnAwramba Times – Ethiopian Prime Minister Hailemariam Desalegn defended the controversial anti terrorism law.
Answering questions at his office last week, Mr. Hailemariam claimed that enacting such legislation was necessary to keep the nation safe from terrorist attacks.
Amnesty International, Human Rights Watch and the Committee to Protect Journalists have been vocal critics of the anti-terrorism law. The law’s critics call it an effective tool for silencing dissent saying some of the provisions would violate the right to freedom of expression and association.
One of the controversial provisions of the anti terrorism proclamation states that “whosoever writes, edits, prints, publishes, publicizes, disseminates, shows, makes to be heard any promotional statements encouraging, supporting or advancing terrorist acts stipulated under this Proclamation is punishable with rigorous imprisonment.”
In June 2011, Ethiopian parliament has officially proscribed Ginbot 7, OLF & ONLF as terrorist organizations.


3 Responses to “Hailemariam Defends Anti-Terror Law, Condemns Critics (Video)”


አቶ ዓባይ ፀሐዬ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፖሊሲና ምርምር አማካሪ ሚኒስትር፣ ሆነው ሊሰሩ እንደሆነ ተጠቆመ፡፡

http://freedom4ethiopian.wordpress.com/2013/10/09/89234/

አቶ ዓባይ ፀሐዬ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፖሊሲና ምርምር አማካሪ ሚኒስትር፣ ሆነው ሊሰሩ እንደሆነ ተጠቆመ፡፡

መነሻ ገጽ - ዜና - የአራት ከፍተኛ ባለሥልጣናት የሥልጣን ዝውውር ሊደረግ ነው
 
የአራት ከፍተኛ ባለሥልጣናት የሥልጣን ዝውውር ሊደረግ ነው
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የአራት ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትን የሥራ ዝውውር በዚህ ሳምንት ውስጥ ሊያደርግ መሆኑ ተጠቆመ፡፡
ጽሕፈት ቤቱ ዝውውሩን የሚያደርገው በሚኒስትር ማዕረግ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር በሆኑት አቶ ዓባይ ፀሐዬ፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የተፋሰስ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ሽፈራው ጃርሶ፣ የአውሮፓ ኅብረትና ቤኔሉክስ (ቤልጂየም፣ ኔዘርላንድና ሉግዘንበርግ) አገሮች አምባሳደር ዶ/ር ካሱ ኢላላና በፈረንሳይ የኢትዮጵያ አምባሳደር በሆኑት አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ላይ መሆኑን ምንጮች አስረድተዋል፡፡ 
በሚደረገው ዝውውር መሠረት አቶ ዓባይ ፀሐዬ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፖሊሲና ምርምር አማካሪ ሚኒስትር፣ በአቶ ዓባይ ቦታ ደግሞ አቶ ሽፈራው ጃርሶ በሚኒስትር ማዕረግ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር፣ ዶ/ር ካሱ ኢላላ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፖሊሲና ምርምር አማካሪ ሚኒስትር ሲሆኑ፣ ዶ/ር ካሱን በመተካት አምባሳደር ተሾመ ቶጋ የአውሮፓ ኅብረትና ቤኔሉክስ አገሮች አምባሳደር ሆነው ወደ ብራሰልስ እንደሚዛወሩ ምንጮች ገልጸዋል፡፡ 
አምባሳደር ተሾመ ቶጋን በመተካት በፈረንሳይ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሆነው የሚሾሙት ደግሞ፣ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአስተዳደር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ የሆኑት አቶ ነጋ ፀጋዬ መሆናቸውን ምንጮች አክለዋል፡፡ 
አቶ ዓባይ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር ሆነው ሲሠሩ፣ በዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ መሠረት ይገነባሉ የተባሉትን አሥር የስኳር ፋብሪካዎችንና የሸንኮራ አገዳ ልማት በሚመለከት፣ ከተለያዩ የቻይና ኩባንያዎችና ከብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ጋር በመነጋገርና በመስማማት ሥራውን ለማስጀመር ጫፍ ላይ መድረሳቸውን ምንጮች አስታውቀዋል፡፡ 
የሽንኮራ አገዳ ልማቱ በመስኖ መካሄድ ስላለበትና ለዚህ ደግሞ ባላቸው ዕውቀትና ልምድ ለሥራው ቅርብ ናቸው የሚባሉት የቀድሞው ውኃ ሀብት ልማት ሚኒስትር አቶ ሽፈራው ጃርሶ በመሆናቸው፣ በአቶ ዓባይ ምትክ እንዲሾሙ ውሳኔ ላይ መደረሱን ምንጮች አረጋግጠዋል፡፡ 
የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የመስኖ ልማት ፕሮጀክቱን በተባለው ፍጥነት በማቀላጠፍ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱን ለማሳካት በመዘግየቱ፣ አቶ ሽፈራው ያላቸውን ዕውቀትና ልምድ በመጠቀም ሊያሳኩት ይችላሉ የሚል ግምት መያዙን ምንጮች አክለዋል፡፡ 
የባለሥልጣናት የሥራ ዝውውርና ሽግሽግ ሊቀጥል እንደሚችል ምንጮች ጠቁመው፣ የአራቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናትና የሚኒስቴር ዴኤታው ምደባ በዚህ ሳምንት መጨረሻ ይፋ ሊደረግ ይችላል ብለዋል፡፡ ከዚህ ቀደም አቶ በረከት ስምኦንና አቶ ኩማ ደመቅሳ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፖሊሲና ምርምር አማካሪ ሲደረጉ፣ አሁን ደግሞ አቶ ዓባይ ፀሐዬና ዶ/ር ካሱ ኢላላ ተጨምረዋል፡፡ 
source: ethiopian reporter
posted by Aseged Tamene

Tuesday, October 8, 2013

ESAT Fundraising event for G7 Popular force in Oslo Oct 6, 2013 Ethiopia | ESAT Tube

ESAT Fundraising event for G7 Popular force in Oslo Oct 6, 2013 Ethiopia | ESAT Tube

የዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ጀርባ ሲገለጥ


http://freedom4ethiopian.wordpress.com/2013/10/08/57-3/

የዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ጀርባ ሲገለጥ

ከርዕሶም ኃይለ
ፕ/ት ሆነው የተመረጡት ሙላቱ ተሾመ ትምህርታቸውን በሰባዎቹ አመታት የተከታተሉትና “ዶ/ር” የሚል ማእረግ ያገኙት በቻይና ነው። በትምህርታቸው በጣም ደካማ ነበሩ። ሙላቱ ሁለት አመት ወድቀው ከመባረር የተረፉት በነዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ አማካይነት ሲሆን፣ በወቅቱ ዶ/ር ነጋሶ ያሉበት ኮሚኒቲ ለዩኒቨርሲቲው ያቀረቡት የextension ጥያቄ ተቀባይነት አግኝቶ መቀጠል እንደቻሉ፣ እንዲሁም ቻይና በነበሩ ጓደኞቻቸው እገዛ ለመጨረስና “ዶ/ር” ለመባል እንደበቁ፣ ጉዳዩን በቅርብ የሚያውቁ ምሁር በወቅቱ አጋልጠው ነበር። ምሁሩ ጉዳዩን ለማጋለጥ የተነሱት ዶ/ር ነጋሶ በገዛ ፈቃዳቸው ስልጣን ለመልቀቅ ጥያቄ ማቀረባቸውን ተከትሎ በስብሰባ ላይ « መንግስቱ ሃ/ማሪያምን መሰልከኝ» ሲሉ አቶ መለስ ዜናዊን ተናግረው ስብሰባውን ጥለው በመውጣታቸው፣ ከዚያም ዶ/ር ሙላቱ በያዙት አቋምና ጭራሽ «ነጋሶ መጠየቅና መታሰር አለበት» በማለት ከመለስ ወግነው በመናገራቸው ምክንያት እንደሆነ ተመልክቷል። ከዩኒቨርሲቲ ጀምሮ የረዷቸውና የኦ.ህ.ዴ.ድ አባል እንዲሆኑ ያደረጓቸው ዶ/ር ነጋሶ ሆነው ሳለ፣ ያን ሁሉ ውለታ ረስተውና በአደርባይነት ተሰልፈው እንዴት «ነጋሶ መታሰር አለበት» ብለው በጭፍን ይፈርዳሉ?..ሲሉ ምሁሩ በግርምት በወቅቱ ጠይቀዋል። ለአቶ መለስ ባሳዩት ታማኝነት ዶ/ር ነጋሶን ተክተው ፕ/ት እንዲሆኑ በወቅቱ ታጭተው የነበረ ቢሆንም፣ እንዲሰረዝ የተደረገው «የፓርቲ አባል ያልሆነ ነው ፕ/ት መሆን የሚችለው» የሚልና በተጨማሪ የቀድሞውን ፕ/ት ዶ/ር ነጋሶን ከፖለቲካ ተሳትፎ ውጭ የሚያደርግ አሳፋሪ ህግ በመለስ እንዲወጣ በመደረጉ ነበር። ሌላው አነጋጋሪ ነጥብ ይህ አዋጅ ሳይሻር፣ ማለትም « የፓርቲ አባል ያልሆነ ግለሰብ ፕ/ት ይሆናል» የሚለው ህግ በአዋጅ ሳይሻር፥ የገዢው ፓርቲ አባል የሆኑት ሙላቱ ተሾመ ፕሬዝዳንት ሆነው መመረጣቸው አስገራሚና ምን ያክል ለራሳቸው ህግና አዋጅ እንደማይገዙ የሚያሳይ ሆኗል።
ዘ-ሐበሻ የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ናት።
በሌላም በኩል “ዶ/ር” ሙላቱ ሚኒስትር በነበሩበት ወቅት፣ መጋቢት 1996ዓ.ም ፓርቲው ባደረገው ግምገማ በአቶ መለስ ከተዘለፉት አንዱ ሲሆኑ፣ ጉዳዩን በመንተራስ «ኢትኦጵ» ጋዜጣ «ከሕወሐት መንደር ከቃረምኩት» በሚል አምዱ በወቅቱ ይፋ ባደረገው መረጃ እንደዘገበው፥ « አቶ መለስ ንቀት በተሞላበት ሁኔታ “ ሙላቱ – አንተን ሚ/ር አድርጌ መሾሜን ረስቸዋለሁ። ያለስራ በሚ/ርነት የተጎለትክ ነህ፤ እዛው ጃፓን አምባሳደር እንደሆንክ ብትቀር ይሻላል። ..ኦ.ህ.ዴ.ድ ማለት ለትግል ፈጥረነው የት እንደገባ የማይታወቅ ድርጅት ነው።” » በማለት መለስ ዜናዊ መናገራቸውን አመልክቶ ነበር።
የ“ዶ/ር” ሙላቱ ባለቤት ወ/ሮ መአዛ አብርሃም ትባላለች። ሸንቃጣዋና የደስ ደስ ያላት መአዛ አንድ ጃፓናዊ አግብታና ልጅ ወልዳ በቶኪዮ ከተማ ትኖር ነበር። እራሷን በጣም ስለምትጠብቅና አለባበሷን (አጭር ሚኒ ቁምጣ ነው የምትለብሰው) ለተመለከታት በወጣትነት የእድሜ ክልል እንደሆነች አድርጎ ይገምታታል፤ ሃቁ ግን ወ/ሮ መአዛ 53 አመት እድሜ ይሆናታል። ከሙላቱ ተሾመ ጋር የተዋወቁት ጃፓን ነበር። መአዛ በጣም ብልጥ ሴት ናት። በጃፓን የኢትዮጲያ አምባሳደር የነበሩት ሙላቱ ተሾመን ታጠምዳለች። ያጠመደችው ወላጅ አባቷ አቶ አብርሃም ነጋ በቀይ ሽብር ወንጀል ተከሰው ስለታሰሩ ነበር። ጃፓናዊ የልጇን አባት ባሏን በመግፋት አምባሰድሩን ትቀርባለች። እንዳጋጣሚ አቶ ተሾመ የስራ ጊዚያቸውን ጨርሰው አገር ቤት ሲመጡ አብራ ትመጣለች። ክዛም ወላጅ አባቷን እንዲያስፈታላት ትጠይቃለች። የተጠየቁት ሙላቱ « ይህን በጭራሽ አልችልም። እነመለስ ከሰሙ ከእንጀራዬ ወዲያው ያባርሩኛል። ይህን ጥያቄ ዳግም እንዳትጠይቂኝ።» ይላሉ። ወላጅ አባቷ በ2000ዓ.ም ከእስር ተፈቱ። ወ/ሮ መአዛ ጃፓናዊ ባሏንና ልጇን በመተው ለፈፀመችው የትዳር ማፍረስ ተግባር ወደዛች አገር ዳግም እንዳትገባ ውሳኔ ስለተላለፈባት፣ ከ”ዶ/ር” ሙላቱ ጋር መጠቃለልን መረጠች። መአዛና ሙላቱ አንድ ልጅ አፍርተዋል። ሙላቱ ተሾመ በ1994ዓ.ም በሰባት ሚሊዮን ብር በቦሌ ያስገነቡት ዘመናዊ ቪላ በወር 36ሺህ ብር እንደሚከራይ ማረጋገጥ የተቻለ ሲሆን፣ ቪላውን ለመገንባት ገንዘቡ በሙስና እንዲገኝ ትልቅ ሚና የተጫወቱት ባለቤታቸው ወ/ሮ መአዛ መሆናቸው ታውቋል።
zehabesha.com
posted by Aseged Tamene

በወያኔ መንግስት “ሳንባ” መተንፈስ ለ“ቲቢ” ያጋልጣል

http://freedom4ethiopian.wordpress.com/2013/10/07/8923-2/

በወያኔ መንግስት “ሳንባ” መተንፈስ ለ“ቲቢ” ያጋልጣል

ፖለቲካዊ ወጋችንን የምንጀምረው በቀልድ ነው፡፡ ግዴለም ባትስቁም አልቀየማችሁም፡፡ ፈገግ ካላችሁ መች አነሰኝ! (ኑሮ “ሃርድ” ሲሆን ሳቅም ይገግማል አሉ) ይልቅስ ሳልረሳው ቀልዱን ቶሎ ልንገራችሁ፡፡ – ፡፡ አንድ የሰው አገር ሰው (ፀጉረ ልውጥ ማለቴ አይደለም!) ከጅቡቲ እየተጫኑ ወደ አዲስ አበባ የሚገቡትን የመኪኖች መዓት በትዝብት ሲመለከት ይቆይና እነዚህ ሁሉ መኪኖች የት ነው የሚገቡት?” ሲል ይጠይቃል፡፡ የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊም  “የሌሎቹን አላውቅም…አይሱዙ ግን ገደል ነው የሚገባው” አሉ (አሉ ነው!)
በነገራችሁ ላይ… በመዲናዋ የሚርመሰመሰው የመኪና ብዛት እኮ ከነዋሪው እኩል ሊሆን ትንሽ ነው የቀረው፡፡ አንዳንዴ ሳስበው ግን ባለሀብቱም ሆነ ሌላው ትንሽ ገንዘብ እጁ ላይ ከተረፈው ዝም ብሎ መኪና የሚያስጭን ነው የሚመስለኝ። (ጀት ለማስጫን አቅም የለችማ!?) እናላችሁ… የመዲናዋ ተሽከርካሪዎች ከህዝቡ በልጠው መፈናፈኛ ከማጣታችን በፊት “አራርቆ መግዛት” የሚል ፖሊሲ ቢቀረጽ ሸጋ ይመስለኛል፡፡ (“አራርቆ መውለድ” እንደሚባለው) ትራፊክ ፖሊስና መንገድ ትራንስፖርት ጥናት አላደረጉ ይሆናል እንጂ የመኪና አደጋ እንዲህ ህዝብ የሚፈጀው የተሽከርካሪው ቁጥር ያለቅጥ በዝቶ ሊሆን ይችላል እኮ! (“የመኪና ምጣኔ” ሳያስፈልገን አይቀርም!)
እኔ የምላችሁ…ባለፈው ሳምንት የኢቴቪ “ዓይናችን” ፕሮግራም ላይ ከመንጃ ፈቃድ አወጣጥና የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ት/ቤቶች አሰራር ጋር በተገናኘ የተጠየቁት የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊ የሰጡትን ምላሽ ሰምታችሁልኛል? ሃላፊዋ የተናገሩትን በአማርኛ ተርጉሞ ለነገረኝ (የገባው ካለ ማለቴ ነው) ወሮታውን እከፍላለሁ፡፡
ቆይ ግን ኢህአዴግ ሌላ ቋንቋ ጀመረ እንዴ? (የደበቀን የትግል ሜዳ ቋንቋ ካለው ብዬ እኮ ነው!) ሃቁን ልንገራችሁ አይደል….ሴትየዋ ከተናገሩት ውስጥ በትክክል የገባኝ “ኪራይ ሰብሳቢነት” የምትለዋ ቃል ብቻ ናት፡፡ እሱም የገባኝ ቃሏን ስለደጋገሟት ነው፡፡ ከ10 ጊዜ በላይ እኮ “ኪራይ ሰብሳቢ” የምትለዋን ቃል ጠቅሰዋል፡፡ (አጋነንኩት እንዴ?)
በነገራችሁ ላይ… “ዓይናችን” ፕሮግራም በመንጃ ፈቃድ አሰጣጥና በአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ት/ቤቶች ዙሪያ ያሉትን ችግሮች የሚያጋልጥ (በአራዳ ቋንቋ “አቧራ የሚያስነሳ”) ዘገባ ባቀረበ ጥቂት ቀናት ውስጥ ለኪራይ ሰብሳቢነት የተጋለጡ ናቸው ከተባሉት ማሰልጠኛዎች መካከል 40 ያህል ት/ቤቶች ሰሞኑን ተዘግተዋል፡፡ (እንኳን ማሰልጠኛ የአሜሪካ መንግስትም Shut down ተደርጓል!)፡፡
እናንተዬ… ፕሬዚዳንት ኦባማ ያመጡት የጤና ዋስትና ሽፋን (Obamacare) ጉድ አፈላ እኮ! እንግዲህ በአሜሪካ እንደኛ አገር አንድ አውራ ፓርቲ ሳይሆን ሁለት አውራ ፓርቲዎች ናቸው ያሉት፡፡ ዲሞክራትና ሪፐብሊካን፡፡ (በአሜሪካ ሰማይ ሁለት ፀሐይ መውጣት ይፈቀድለታል ማለት ነው!) እናላችሁ …ባለፈው ሳምንት የመንግስት ባጀት እንዲፀድቅ በኮንግረስ ሲቀርብ ሪፐብሊካኖቹ ስውር ደባ ፈፀሙ ተባለ፡፡ “የጤና ዋስትና ሽፋን ፖሊሲው ካልተሰረዘ ባጀቱን አናፀድቅም” ብለው ገገሙ፡፡ ሁለቱ የአሜሪካ አውራ ፓርቲዎች እልህ ውስጥ በመገባባታቸውም የበጀቱ ጉዳይ ሳይፀድቅ ቀረ፡፡ በዚህም የተነሳ የአሜሪካ ፌደራል መንግስት ተቋማት በሙሉ ካለፈው ማክሰኞ ተሲያት በኋላ ተዘጉ – ከመከላከያና የፖሊስ ሃይል በስተቀር፡፡ ስሙ ደሞ “Government Shut down” ይባላል። እናላችሁ… ባጀቱ እስኪፀድቅ ድረስ 3 ሚሊዮን የሚደርሱ የፌደራሉ መንግስት ሰራተኞች ደሞዝ ላይከፈላቸው ይችላል ተብሏል፡፡
አብዛኞቹ የመንግስት መ/ቤቶች በር ላይም “የፌደራል መንግስቱ ስራ ስላቆመ አገልግሎት አንሰጥም” የሚል ማስታወቂያ ተለጥፏል፡፡ ዋሺንግተን በሚገኝ አንድ ፓርክ በር ላይ የተለጠፈው ማስታወቂያ “Because of The Federal Government Shut down All National parks are closed” ይላል፡፡ ወደ አሜሪካ!…የማታሰማን ጉድ የለም እኮ! (መንግስት የሚዘጋበት አገር!) እኔን ከሁሉም የገረመኝ ግን ምን መሰላችሁ? የመንግስት መ/ቤቶች በሙሉ ተዘግተው ህይወት መቀጠሉ! በነገራችሁ ላይ… የዛሬ 17 ዓመትም በክሊንተን ዘመን ለ28 ቀን ገደማ የአሜሪካ ፌደራል መንግስት ስራ አቁሞ ነበር፡፡ እስቲ አስቡት…እኛ አገር እንኳን 28 ቀን ሁለት ቀን “ልማታዊ መንግስታችን” ስራ ቢያቆም የሚፈጠረውን ምስቅልቅል
ለነገሩ…የእኛ አገር አንዳንድ የመንግስት ተቋማት እኮ እንኳን ተዘግተው ሳይዘጉም የተዘጉ ያህል ናቸው፡፡ (አሁን ለምሳሌ መብራት ሃይል አልተዘጋም ብሎ የሚከራከረኝ አለ?) አንዳንድ የፖለቲካ ተንታኞች፤ የአሜሪካ መንግስት ተቋማት ተከርችመው የዕለት ተዕለት ህይወት የማይስተጓጐለው ህዝቡ በመንግስት ሳንባ ሳይሆን በራሱ ሳንባ ስለሚተነፍስ ነው ይላሉ፡፡ “እኛ ግን መንግስት ድንገት shut down” አብረን shut down እንሆናለን፤ ምክንያቱም የምንተነፍሰው በመንግስት ሳንባ ነዋ!” ሲሉ ይተነትናሉ – ባለሙያዎቹ፡፡ (እንዴ የራሳችን ሳንባ የት ሄዶ ነው?)
ይኸውላችሁ… በአሜሪካ የመንግስት መ/ቤቶች ተዘግተዋል ቢባልም መሰረታዊ አገልግሎቶች እኮ አይቋረጡም፡፡ ለምን መሰላችሁ… እንደኛ አገር “የምትታለብ ላም” ምናምን አይሰራማ! መብራት፣ ውሃ፣ ትራንስፖርት፣ ቴሌ፣ ባንክ ወዘተ ሁሉም በግሉ ዘርፍ ስር ናቸው፡፡ ስለዚህ መንግስትም በራሱ ሳንባ፣ ህዝብም በራሱ ሳንባ ይተነፍሳሉ ማለት ነው፡፡
እኔ የምለው ግን… እኛ አገር ህዝብና መንግስት በአንድ ሳንባ ሲተነፍሱ የጤና ችግር አያስከትልም እንዴ? መንግስት አያድርስበትና በቲቢ ከተጠቃ እኮ የአበሻ ዘር አብሮ ማለቁን ነው፡፡ (ጤና ጥበቃ እያለ?) “በአውብቶስ ስትሄዱ መስኮት በመክፈት ቲቢን ተከላከሉ” ማለት ብቻውን እኮ አይበቃም (በአንድ ሳንባ መተንፈስስ?) እባካችሁ ለኢቴቪ “ጤናዎ በቤትዎ” ፕሮግራም እቺን ጥያቄ ጠይቁልኝ። (ወሮታውን እንደተለመደው እከፍላለሁ!)
አንድ ዘወትር ከመንግስት ሹመኞችና ከኢህአዴግ ካድሬዎች አፍ የማትጠፋ አባባል አለች። (ፕሮፖጋንዳ ልትሆን አንድ ሃሙስ የቀራት!) “ወጣቱ ሥራ ጠባቂ ሳይሆን ሥራ ፈጣሪ መሆን አለበት” ትላለች፡፡ እውነት ለመናገር… አባባሏ እኮ እንከን የማይወጣላት ወርቅ አባባል ናት፡፡ ችግሩ ግን ምን መሰላችሁ? በመንግስት ሳንባ እየተነፈሱ የራስን ሥራ መፍጠር ከባድ ነው፡፡ (የመተንፈስ ነፃነት ይቀድማል ወይስ ሥራ መፍጠር?) እናም መንግስት “ሥራ ፍጠሩ” የሚለው ከአንጀቱ ከሆነ በራሳችን ሳንባ የመተንፈስ ተፈጥሮአዊ፣ ሰብአዊና ጤናዊ መብታችንን ያስከብርልን (ያክብርልን ማለቴ ነው!) በነገራችሁ ላይ …ይሄ የመብት ጥያቄ ወደው በመንግስት ሳንባ የሚተነፍሱ ወገኖችን (“በአንድ ሳንባ እንተንፍስ” ባዮችን) አይመለከትም፡፡ ያለፍላጐታቸው ተገደው በመንግስት ሳንባ የሚጠቀሙትን ብቻ ነው፡፡ በዚህ አጋጣሚ በመንግስት ሳንባ በመተንፈስ የመብት ጥሰት የተፈፀመባችሁ ወገኖች …በቅርቡ በሚደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ እንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል፡፡ (መስተዳድሩ ከፈቀደ ማለት ነው!)
አንድ ጥያቄ አለኝ፡፡ ለምንድነው መንግስት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለትንሹም ለትልቁም ልማቱን “ሰበብ” ማድረግ የጀመረው? (ይሄ ከልማታዊ መንግስት አይጠበቅም!) ተቃዋሚዎች ለሰላማዊ ሰልፍ ቦታ ሲጠይቁ፣ ከጃንሜዳ ሌላ ቦታ የለም ብሎ በልማቱ ማሳበብ አይደንቅም? (ጦቢያ በቦታ ትታማለች?)
ጠዋትና ማታ ለሚያሰቃየን የትራንስፖርት እጥረት መፍትሔ ከመሻት ይልቅ በልማት ማሳበብ ምን ይባላል? ለመብራት መቆራረጥ፣ ለውሃ መጥፋትና ለኔትዎርክ መንቀራፈፍ አሁንም ሰበቡ የፈረደበት “ልማት” ሆኗል፡፡
ትንሽ ከታገስነው ደግሞ አንድ ቀን፣ የህዝቡን ቅሬታና እሮሮ ለመስማትም “ልማት ላይ ስለሆንን ፋታ የለንም” ይለን ይሆናል፡፡ (ልማት ጆሮ ይደፍናል እንዴ?) የውጭ ጉዳይ ሚ/ሩ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ግን ጆሮ የሚደፍነው ሌላ ነው ባይ ናቸው) (ቃል በቃል ሳይሆን ሃሳባቸውን ነው) “የስልጣን ቁጥር በጨመረ መጠን ጆሮ መስማቱን ይቀንሳል” ብለዋል፡፡ እናላችሁ…ትክክለኛ ልማታዊ መንግስት ልማቱን በማናቸውም ሁኔታ ሰበብ አያደርግም ለማለት ያህል ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ “አገሪቱን ለማልማት 30 እና 40 ዓመት በስልጣን ላይ መቆየት እፈልጋለሁ” ማለትም ልማቱን ማርከስ ነው ይላሉ – የልማት ኤክስፐርቶች፡፡ (ገዢ ፓርቲ ብቻ ነው የሚያለማው ያለው ማነው?
በነገራችሁ ላይ… ኢህአዴግም በመንግስት ሳንባ ከመተንፈስ እንዲላቀቅ እንታገላለን፡፡
ማሳሰቢያ
በመንግስት ሳንባ መተንፈስ “ጥገኝነት” ለተባለ ቫይረስ እንደሚያጋልጥ ጥናቶች ይጠቁማሉ!
addis admas
posted by Aseged Tamene

(አቦይ ቆምጬ) ሃይለማርያም ደሳለኝ ከቴድሮስ ሐይሌ | Zehabesha Amharic

(አቦይ ቆምጬ) ሃይለማርያም ደሳለኝ ከቴድሮስ ሐይሌ | Zehabesha Amharic

Monday, October 7, 2013

ኤርትራ በኢትዮጲያ መከላከያና ደህንነት ውስጥ ሰላዮችን ማሰማራቷን ኢትዮጲያ አመነች፥ ኢሳት ዜና

October 4, 2013
The charges under the files Fikru Abebe Haile, Tesfu Abate Abyneh, Mohmamed Umer Mohammed, Tamene  Tememte Zewde and Zerfu Melka, members of the Ethiopian Defense Forces, and accused of spying for Eritrea, reads that theEthiopian government has admitted that it has been infiltrated by the Eritrean IntelNetwork built between Addis Abeba, Borena and Nairobi, Kenya, ESAT has reported tonight.
The dossier that ESAT has accessed also states that Getachew Assefa, Head of the Ethiopian Intel, had told Intel members on a February 26, 2012 meeting that they had collected public opinion if they should go to war with Eritrea and the public’s response was against the idea. The details of this meeting were sent to Eritrea.
ESAT also reported that the dossier shows that the Ethiopian government has no interest of going into war with Eritrea but wanted to wipe out Ethiopian rebels that came from Eritrea through the North Western border of EthiopiaHumera and decided to weaken local opposition parties before the next election, 2015.
Listen to ESAT’s extended reportage here

ዶክተር ሙላቱ ተሾመ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሬፐብሊክ ፕሬዘደንት በመሆን ተመረጡ።

http://freedom4ethiopian.wordpress.com/2013/10/07/8923-2/

ዶክተር ሙላቱ ተሾመ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሬፐብሊክ ፕሬዘደንት በመሆን ተመረጡ።

ዶክተር ሙላቱ ተሾመ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሬፐብሊክ ፕሬዘደንት በመሆን ተመረጡ።
ዶክተር ሙላቱ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዘደንት ዘቶ ተገኔ ጌታነህ አማካኝነት ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።
ተሰናባቹ ፕሬዘደንት አቶ ግርማ ወልደ ጊዮርጊስም ለተመራጩ ፕራዘደንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ስልጣናቸውን አስረክበዋል።
ፕሬዘደንት ዶክተር ሙላቱ ለህዝብ ተወካዮችና የፌደረሽን ምክር ቤት የጋራ ስብሰባ ላይ ባደረጉት ንግግር ምክር ቤቶቹ የጣሉባቸውን አደራና ሐላፊነት ባላቸው ሙሉ አቅም ለመወጣት ቃል ገብተዋል።
ፕሬዘደንት ዶክተር ሙላቱ ለሐገራቸው ህዝብም የሚጠበቅባቸውን በሃላፊት እንደሚሰሩም ተናግረዋል።
ዶክተር ሙላቱ ተሾመ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሬፐብሊክ ፕሬዘደንት በመሆን ተመረጡ።ዶክተር ሙላቱ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዘደንት ዘቶ ተገኔ ጌታነህ አማካኝነት ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።ተሰናባቹ ፕሬዘደንት አቶ ግርማ ወልደ ጊዮርጊስም ለተመራጩ ፕራዘደንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ስልጣናቸውን አስረክበዋል።ፕሬዘደንት ዶክተር ሙላቱ ለህዝብ ተወካዮችና የፌደረሽን ምክር ቤት የጋራ ስብሰባ ላይ ባደረጉት ንግግር ምክር ቤቶቹ የጣሉባቸውን አደራና ሐላፊነት ባላቸው ሙሉ አቅም ለመወጣት ቃል ገብተዋል።ፕሬዘደንት ዶክተር ሙላቱ  ለሐገራቸው ህዝብም የሚጠበቅባቸውን በሃላፊት እንደሚሰሩም ተናግረዋል።
Netsanet Lehagere
posted by Aseged Tamene

Saturday, October 5, 2013

ገዢው ፓርቲ በጠራቸው ስብሰባዎች ላይ ሁሉ ተቃውሞ ገጠመው

ገዢው ፓርቲ በጠራቸው ስብሰባዎች ላይ ሁሉ ተቃውሞ ገጠመው

መስከረም ፳፬(ሃያ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢህአዴግ መራሹ መንግስት ባለፈው ሳምንት በመላ አገሪቱ የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞችን እየሰበሰበ በ2005 የስራ አፈጻጸምና የ2006 ዓም በጀት እቅድ ትግበራ ላይ ሲያወያይ ቢሰነበትም፣ ለኢሳት ሚደርሱት መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በሁሉም ቦታዎች ላይ በተደረጉት ስብሰባዎች ከፍተኛ ተቃውሞ አጋጥሞታል።
በአዳማ የተካሄደውን ስብሰባና ተሰብሳቢዎች ያቀረቡዋቸውን ቅሬታዎች ኢሳት ቀደም ብሎ የዘገበ ሲሆን፣ በአማራ ክልል በሰሜን ጎንደር ዞን በአርማጭሆ ወረዳ የነበረው ስብሰባም እንዲሁ በተመሳሳይ ተቃውሞ መጠናቀቁን በውይይቱ የተሳተፉ የመንግስት ሰራተኞች ገልጸዋል።
በውይይቱ ላይ በርካታ አጀንዳዎች የነበሩ ሲሆን፣ ከጸጥታ ጋር በተያያዘ የተነሱት ጉዳዮች ተሰብሰባዊውን በከፍተኛ ሁኔታ አወዛግበዋል።
በ2006 ዓም የጸረ ሰላም ወይም የጥፋት ሀይሎችን ማምከን የሚል በእቅድ እንዲካተት በቀረበው አጀንዳ ላይ ጸረ ሰላም ማን ነው የሚለው ጥያቄ በተሰብሳቢው ተነስቶ የመድረኩ መሪዎች የተለያዩ መልሶችን ሰጥተዋል። የዞኑ የጸጥታ ጉዳዮች ሀላፊ የሆኑት አቶ ወርቁ ሀ/ማርያም ” ነሀሴ ወር ገደማ 30 የሚሆኑ ሰዎች በጎንደር ከተማ ህዝቡን ተነስ በማለት ሲቀሰቅሱ የነበሩ ሰዎች  ጸረ ሰላም ሀይሎች ናቸው።” በማለት አንድነት ፓርቲ በጎንደር ያካሄደውን የተቃውሞ ሰልፍ በምሳሌነት አንስተዋል።
ሌላው የሲቪል ሰርቪስ ባለስልጣን የሆኑት አቶ ገዛሀን ተክሌ በበኩላቸው ” የኢትዮጵያ መሬት ለሱዳን ተሰጠ ብሎ መናገር ጸረ ሰላምነት ነው” ሲሉ አብረራርተዋል። ባለስልጣኑ አክለውም ህገመንግስቱን ለመጣስ የሚነሳ ሁሉ ጸረሰላም ተብሎ ይፈረጃል ብለዋል።
የጸጥታ ጉዳዮች ዘርፍ ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ደግሞ ” ከመድረክ አፈንግጦ መውጣትና ሳያስፈቅዱ መናገር፣ ሳያስፈቅዱ ጽሁፍ መጻፍና ማሰራጨት፣ ሳያስፈቅዱ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ፣ በጥፋት መልእክተኝነት ያስፈርጃል ሲል ገልጸዋል።
አቶ ፈንታ የተባሉ ባለስልጣንም እንዲሁ ” የጎንደርን መሬት ኢህአዴግ አሳልፎ እየሰጠ ነው ” ብሎ መናገር ጸረ-ሰላም ተግባር ነው በማለት የራሳቸውን ትርጉም አቅርበዋል።
ስለ ጸረ ሰላም ሀይሎች፣ አክራሪነትና ሽብረተኝነት ከአንደኛ ደረጃ ጀምሮ ትምህርት እንዲሰጠጥ በቀረበው ሀሳብ ላይ ደግሞ በስብሰባው የተሳተፉ ተቃውሞአቸውን ገልዋል። ተሳታፊዎቹ ከ15 ዓመት በታች ያሉ ህጻናትን ስለ ሽብረተኝነት፣ አክራሪነትና ጸረሰላም ሀይሎች ማስተማር በህጻናቱ ላይ የስነልቦና ጫና ይፈጥራል በማለት ተከራክረዋል።
ሌላው አወዛጋቢ የነበረው ነጥብ ” ኢህአዴግ የ2006 እቅድን ተቋሞችን በድርጅት አባላት በመሙላት እናሳካለን በማለት ያቀረበው ” ሲሆን፣ ተሰብሳቢዎቹ የመንግስት መስሪያ ቤቶችን ሁሉ በድርጅት አባላት ከሞላችሁ የተቃዋሚ ድርጅት አባላትን ምን ልታደርጉዋቸው ነው?” በማለት ጥያቄ አንስተዋል።
ለሱዳን ተላልፎ የተሰጠውን መሬት በተመለከተ የአካባቢው ሰራተኞች የሁለቱን አገሮች ድንበሮች ጠንቅቀው የሚያውቁ በመሆኑ በኢህአዴግ የቀረበውን ማስጠንቀቂያ አልተቀበሉትም።

Sea Tragedy Strikes Eritrean Refugees Off Italian Coast

በትግራይ እንደርታ ሙስናን ያጋለጠ የሕወሓት አባል ተባረረ | Zehabesha Amharic

በትግራይ እንደርታ ሙስናን ያጋለጠ የሕወሓት አባል ተባረረ | Zehabesha Amharic

የፊታችን ሰኞ የኢሕአዴግ ፓርላማ “አበባ ቆራጭ” ይሾማል | Zehabesha Amharic

የፊታችን ሰኞ የኢሕአዴግ ፓርላማ “አበባ ቆራጭ” ይሾማል | Zehabesha Amharic

ግንቦት ሰባት፤ ብርሀኑ፤ አንዳርጋቸው፤ የኤርትራ ነገር? የኛ ነገር፡ ክፍል 16፤ ከኔ ማእዘን፤ | Zehabesha Amharic

ግንቦት ሰባት፤ ብርሀኑ፤ አንዳርጋቸው፤ የኤርትራ ነገር? የኛ ነገር፡ ክፍል 16፤ ከኔ ማእዘን፤ | Zehabesha Amharic

Thursday, October 3, 2013

የኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ድምፅ ከየመን

የኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ድምፅ ከየመን

በየመን እና በሳዑዲ አረቢያ ድንበር ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች የሚገኙት በአስቸጋሪ ሁኔታ ላይ መሆኑ ተሰምቷል፡፡
የሳዑዲ-የመን ድንበር አጥር
የሳዑዲ-የመን ድንበር አጥር
የፊደል ቁመት 
ሰሎሞን አባተ