Monday, April 28, 2014

በፖሊስ ቁጥጥር ሥር የዋሉት ጋዜጠኞችና ብሎገሮች ፍርድ ቤት ቀረቡ | Zehabesha Amharic

በፖሊስ ቁጥጥር ሥር የዋሉት ጋዜጠኞችና ብሎገሮች ፍርድ ቤት ቀረቡ | Zehabesha Amharic

የሰማያዊ ፓርቲ አባል ፈተና እንዳይፈተን ተከለከለ

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሶስተኛ አመት የምህንድስና ተማሪ የሆነው ዮናስ ከድር ሰማያዊ ፓርቲ ለጠራው ሰልፍ ሲቀሰቅስ ተይዞ ጉለሌ ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ ይገኛል፡፡ እስር ቤት ውስጥ ያለ ተማሪ በፖሊስ ታጅቦ ፈተናውን የመፈተን መብት ቢኖረውም ዮናስን ግን ‹‹አንተ የፖለቲካ እስረኛ ነህ፣ አንተን አጅበን ማስፈተን አንችልም፣ አንተን የሚያጅብ ፖሊስ የለንም!›› የሚሉ የተለያዩ ምክንያችን በመደርደር ለፈተና እንዳይቀርብ ተደርጓል፡፡10330474_10152416602689743_8094249108584679939_n

Sunday, April 27, 2014

ከ1.5 ቢሊዮን ብር በላይ ያልተሰበሰበ ከ2.3 ቢሊዮን ብር በላይ ያልተሠራበት በጀት ከ785 ሚሊዮን ብር ሕጋዊ ያልሆነ ወጪ ተጋለጠ (ሪፖርተር)

የፌደራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ላለፉት በርካታ ዓመታት ለፓርላማ ሲያቀርበው እንደቆየው ሁሉ፣ ለብክነት የተጋለጠ በቢሊዮኖች የሚቆጠር የመንግሥት ሀብት መኖሩን ባለፈው ሚያዝያ 14 ቀን 2006 ዓ.ም.
ለፓርላማው ይፋ አድርጓል፡፡ ተመሳሳይ ሪፖርቶችን ሲሰማ የቆየው ፓርላማው ፈጣን ዕርምጃ ከመውሰድ ይልቅ የአንድ ዓመት ገደብን መስጠት መርጧል፡፡
በዝቅተኛ የደመወዝ ክፍያ ምክንያት ሠራተኞችን ለማቆየት መቸገራቸውን የገለጹት የፌደራሉ ዋና ኦዲተር አቶ ገመቹ ዱቢሶ፣ ችግሩን ለመቅረፍ ራሳቸው ጭምር በቡድን መሪነት በተሳተፉበት የ130 የፌደራል መንግሥት መሥሪያ ቤቶችን የ2005 ዓ.ም. በጀት ኦዲት በማድረግ፣ እንዲሁም በኦዲት ሰርቪስ ኮርፖሬሽን የስምንት መሥሪያ ቤቶችን ኦዲት በማሠራት፣ በአጠቃላይ የ138 መሥሪያ ቤቶችን ኦዲት በመተንተን የኦዲት ግኝቱን ለፓርላማ አቅርበዋል፡፡
ከቀረበው የፋይናንስ ሕጋዊነትን የተመለከተ የኦዲት ሪፖርት ውስጥ አንድ ቢሊዮን 527 ሚሊዮን ብር ተሰብሳቢ ሒሳብ መኖሩን፣ ሕጋዊ ሥርዓቱን በልተከተለ መንገድ የተለያዩ የመንግሥት ድርጅቶች 785 ሚሊዮን ብር ወጪ ማድረጋቸውን፣ የተፈቀደው በጀት በትክክል ሥራ ላይ መዋሉን ለማረጋገጥ በተደረገ ኦዲት ደግሞ 2.3 ቢሊዮን ብር ያልተሠራበት በጀት መገኘቱን ይፋ አድርገዋል፡፡
ውዝፍ ተሰብሳቢ ሒሳብ ሕጉ በሚፈቅደው መሠረት በወቅቱ ካልተወራረደ ወይም ካልተሰበሰበ በቆየ ቁጥር የመሰብሰብና ወደ ሀብትነት የመለወጥ ዕድሉ አሳሳቢ መሆኑን የገለጹት ዋና ኦዲተሩ፣ ኦዲት ከተደረጉት መሥሪያ ቤቶች 77 በሚሆኑት ላይ 877.1 ሚሊዮን ብር በደንቡ መሠረት ሳይወራረድ መገኘቱን አስረድተዋል፡፡
ከላይ ከተጠቀሰው ያልተወራረደ ውዝፍ ተሰብሳቢ ሒሳብ ውስጥ ከፍተኛውን ድርሻ ከያዙት መካከል በግብርና ሚኒስቴር የግብርና ቴክኒክ ሙያና ትምህርት ሥልጠና ማስተባበሪያ 173.6 ሚሊዮን ብር፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር 149.5 ሚሊዮን ብር፣ የትምህርት ሚኒስቴር 100 ሚሊዮን ብር ይገኙበታል፡፡
ዋና ኦዲተር የመንግሥት ገቢ በአግባቡ መሰብሰቡን ለማጣራት ባካሄደው ኦዲት 32.2 ሚሊዮን ብር ከገቢ ግብር፣ ከቀረጥና ታክስ እንዲሁም ከሌሎች ገቢ መሰብሰብ በሚፈቅዱ ደንቦች መሠረት አለመሰብሰቡን አረጋግጧል፡፡
ገቢ ሰብሳቢ መሥሪያ ቤቶችና ድርጀቶች አግባብ ባለው ሕግና ደንብ መሠረት የመንግሥት ገቢ በአግባቡ መሰብሰባቸውን ለማረጋገጥ በተደረገ ኦዲት 326.7 ሚሊዮን ብር ያልተሰበሰበ ውዝፍ ገቢ መኖሩ ተረጋግጧል፡፡ አብዛኛው ይህ ውዝፍ ያልተሰበሰበ ገቢ የሚመለከተው የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣንን እንደሆነ ከኦዲት ሪፖርቱ ለመረዳት ተችሏል፡፡ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣንን በጊዜያዊነት ወደ አገር የሚገቡ ዕቃዎች የጊዜ ገደባቸውን ካጠናቀቁ በኋላ፣ የጊዜ ገደቡ በሕግ አግባብ እንዲራዘም ካልተደረገ በስተቀር በዋስትና የተያዘውን ገንዘብ የመውረስ መብት በሕግ ተሰጥቶታል፡፡ ነገር ግን በጊዜያዊነት ገብተው የመቆያ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁ በድምሩ 222.5 ሚሊዮን ብር የዋስትና ገንዘብ አለመሰብሰቡን የኦዲት ሪፖርቱ ያስረዳል፡፡
‹‹የሚሰበሰብ ገቢ መንግሥት ለሚያከናውናቸው የልማትና ማኅበራዊ አገልግሎቶች መስፋፋትና ለአገሪቱ የዕድገትና ትራንስፎሜሽን ዕቅድ መሳካት ወሳኝ ሚና የሚኖረው በመሆኑ፣ የመንግሥት ሕግና ደንብ ተከብሮ መሠራት አለበት፤›› ሲሉ ዋና ኦዲተሩ አቶ ገመቹ አሳስበዋል፡፡
ሕጋዊነት የጎደላቸው ወጪዎችን በተመለከተ ባቀረቡት ሪፖርት 785 ሚሊዮን ብር አግባብነት የጎደላቸው ወጪዎች መኖራቸውንም አስረድተዋል፡፡ ከዚህ ውስጥ በዋነኝነት የሚጠቀሰው በ25 መሥሪያ ቤቶች በወጪ ተመዝግቦ ነገር ግን የወጪውን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ ማስረጃ ሊቀርብበት ያልቻለ 202.6 ሚሊዮን ብር በወጪ ተመዝግቦ ተገኝቷል፡፡
የግዥ አዋጁን እንዲሁም ደንብና መመርያን ያልተከተሉ ግዥዎችን በተመለከተ ደግሞ፣ 43 መሥሪያ ቤቶች 165.9 ሚሊዮን ብር ደንብና መመርያን በመጣስ ወጪ አድርገዋል ብለዋል፡፡ ሌሎች 41 መሥሪያ ቤቶች ደግሞ 76 ሚሊዮን ብር ደንብና መመርያን በመጣስ ክፍያ መፈጸማቸውን በሪፖርታቸው ገልጸዋል፡፡
ሒሳቦች በወጪነት የሚመዘገቡት የሚፈለገው አገልግሎት መገኘቱን ወይም የሚፈለገው ንብረት በአግባቡ በእጅ
መግባቱ ሲረጋገጥ ቢሆንም፣ 13 መሥሪያ ቤቶች አገልግሎቱን ወይም ንብረቱን ሙሉ በሙሉ ሳያገኙ የከፈሉትን
የ234.8 ሚሊዮን ብር ቅድመ ክፍያ በወጪ መዝገብ ይዘው ተገኝተዋል፡፡ በመሆኑም የተፈለገው አገልግሎት ወይም
ንብረት ሙሉ በሙሉ እስኪፈጸም ድረስ በተሰብሳቢ መያዝ ይኖርበታል የሚል አስተያየት ሰጥተዋል፡፡
በ104 መሥሪያ ቤቶች ደግሞ ለተለያዩ ግዥዎች አራት ሚሊዮን 471 ሺሕ ብር ያላግባብ በብልጫ መከፈሉን የኦዲት ሪፖርቱ ያስረዳል፡፡
በተጨማሪም በአሥር መሥሪያ ቤቶች የንብረት ገቢ ደረሰኝ ያልቀረበለት 22.6 ሚሊዮን ብር ወጪ መኖሩን፣ በሌሎች ሰባት መሥሪያ ቤቶች ደግሞ 1.6 ቢሊዮን ብር ቀረጥ የተከፈለባቸው ንብረቶች ገቢ መሆናቸውን ለማረጋገጥ አልተቻለም፡፡
ቀረጥ ተከፍሎባቸው ንብረቶቹ ገቢ ለመሆናቸው ለማረጋገጥ ካልተቻለባቸው መሥሪያ ቤቶች ትልቁን ድርሻ የያዘው፣ የቅድሚያ ማስጠንቀቂያና ምላሽ ዳይሬክቶሬት ሲሆን፣ በቀጣይነት ደግሞ ጤና ጥበቃና ትምህርት ሚኒስቴር ተጠቅሰዋል፡፡
በ23 መሥሪያ ቤቶች የወጪውን ትክክለኛነት ማረጋገጥ ያልተቻለ 90.9 ሚሊዮን ብር መኖሩን ሪፖርቱ ያስረዳል፡፡
የፌደራል መንግሥት ግዥ አፈጻጸም መመርያ በግንባታ ቦታ ላይ ላሉ ዕቃዎች፣ ወይም ግንባታ ላይ ላልዋሉ ክፍያ መፈጸምን የሚከለክል ቢሆንም፣ 11 መሥሪያ ቤቶች ይህንን በመጣስ 168.6 ሚሊዮን ብር መክፍላቸውን ሪፖርቱ ያስረዳል፡፡ መንግሥት የግንባታ ዕቃዎችን በብድር ሲያገኝ የተገኘው ቁስ መጠን ተሰልቶ ከግንባታ ወጪ ላይ መቀነስ የሚገባው ቢሆንም፣ አራት መሥሪያ ቤቶች ግን 18.3 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ በብድር የተገኙ የግንባታ ዕቃዎች ወጪን ሳይቀንሱና ለመንግሥት ካዝና ሳያስገቡ በኦዲቱ ተገኝተዋል፡፡

Friday, April 25, 2014

ሰበር ዜና፡ “ሰማያዊ ፓርቲ የእሁዱን ሰልፍ በታቀደው መሰረት ለማከናወን በሙሉ ቁርጠኝነት ላይ ይገኛል!!!”

April 25, 2014
ከአመራሩ በተጨማሪም የታሰሩ አባላት ዝርዝርSemyawi party leaders arrested
የካ ክፍለ ከተማ ሾላ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የታሰሩ
1. ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት -የፓርቲው ሊቀመንበር
2. ስለሽ ፈይሳ- ምክትል ሊቀመንበር
3. ብርሃኑ ተክለያሬድ-የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ
4. ዳዊት ጸጋዬ
5. አወቀ ተዘራ
6. ኢብራሂም አብዱሰላም
7. ሁሴን
8. ሙሉጌታ መኮንን
ጉለሌ ፖሊስ መምሪያ የታሰሩ
1. ዮናስ ከድር
2. እየሩስ ተስፋው
3. እመቤት ግርማ
4. የሽዋስ አሰፋ
5. አበራ
6. አበበ መከተ
ካሳንቺስ ስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ የታሰሩት
1. ብሌን መስፍን
2. አስናቀ በቀለ
3. መስፍን
4. ተስፋዬ አሻግሬ
5. እዮብ ማሞ
6. ኩራባቸው
7. ተዋቸው ዳምጤ
ከየካ ፖሊስ ጣቢያ ወደ ቤላ አካባቢ ተዛውረው ታስረው የሚገኙት
1. ፍቅረማሪያም አስማማው
2. እያስፔድ ተስፋዬ
3. ጋሻው መርሻ
4. ተስፋዬ መርኔ
5. ሀብታሜ ደመቀ
6. ዘሪሁን ተስፋዬ
7. ጌታነህ ባልቻ
8. ንግስት ወንዲፍራው
9. ሜሮን አለማየሁ
ስማቸው ያልደረሱን የታሰሩ ሌሎች ወደ 15 የሚጠጉ አባለት እንዳሉ(አድዋ ድልድይ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያና ለጊዜው ቦታቸውን ባላወቅናቸው ፖሊስ ጣቢያዎች ታስረው እንደሚገኙ) መረጃ ደርሶናል ስማቸው ሲደርሰን እናሳዉቃለን፡፡
በተጨማሪ መረጃ ህወሓት/ኢህአዲግ ሰልፉን በተለያየ መልኩ ለማደናቀፍ ቢጥርም ሰማያዊ ፓርቲ የእሁዱን ሰልፍ በታቀደው መሰረት ለማከናወን በሙሉ ቁርጠኝነት ላይ ይገኛል፡፡ የአመራሮችም ሆነ የአባላት እስር የምናደርገውን ትግል ከፍ አድርጎታል፡፡ የያዝነውን የሰላማዊ ትግል ስልትም ከዚህ በበለጠ አጠናክረን ወደፊት እንጓዛለን፡፡ እሁድ 03:00 ሰዓት ላይ ካሳንቺዝ እንደራሴ ሆቴል አካባቢ በሚገኘው በፓርቲያችን ጽ/ቤት ተገናኝተን ስለመብታችን በጋራ እንተማለን!
ኑ ራሳችንን ነፃ በማውጣት የሀገራችንን እጣ ፈንታ እንወስን
ሰማያዊ ፓርቲ!

በሰሜን ጎንደር ጭልጋ ከተማ አቅራቢያ በምትገኝ የገጠር ቀበሌ በአካባቢው ገበሬዎች እና በፌደራል ፖሊስ መካከል በተነሳ ግጭት የብዙ ሰዎች ህይወት ሲቀጠፍ ብዙዎችም ከባድና ቀላል ቁስለኛ ሆነዋል። ባጠቃላይ 11 መኪኖች ቁስለኛ እና አስከሬን ጭነው ማለፋቸውም ተረጋጧል።

ከሰሜን ጎንደር ጭልጋ ከተማ የደረሰኝ መረጃ  | Zehabesha Amharic

Ethiopia Prison Alert: Journalist in danger – An Urgent Appeal from Professor Mesfin Woldemariam

April 25, 2014
To
The UN Human Rights Commission
The African Union Human Rights Commission
The International Red Cross
Amnesty International
Human Rights Watch &
All Men and Women of GOOD WILL
Reeyot Alemu is a budding Ethiopian poet, essayist, and journalist. There are not many Ethiopians of her caliber inside the country. She has been languishing in the famous Ethiopian Prison in Qalliti for almost three years. She was charged of terrorism, a crime she totally abhors. She was sentenced first for eighteen years but later reduced to three.Reeyot Alemu is a budding Ethiopian poet, essayist, and journalist.
With the exception of her mother and father, she is not allowed to communicate with anyone, including her sisters, brothers as well as her fiancée.
Reeyot, although constantly in agonizing pain and in need of help, is held in solitary confinement with a very old and sickly foreign woman who herself requires assistance.
Reeyot is suffering from some growth in her breasts. The prison authorities have been reluctant to take her to hospital for medical checkup, even when her parents were prepared to pay the bill. When she became seriously ill she was allowed to see a doctor as a result of which she was taken to the hospital and operated upon. But no sooner had the surgeon finished the operation than she was immediately taken back to prison even before she had fully recovered from the Anastasia.
She now suffers from a relapse on the operated breast and similar growth in her other breast. The prison authorities still demonstrate their reluctance to provide medical treatment even at the expense of her parents.
May God provide the necessary courage to all those institutions and organizations to cry out effectively for this young lady who is suffering at the hands of insensitive prison administration.
Mesfin Woldemariam

“የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴን በተመለከተ በኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች ላይ ያለን እምነት በመሟጠጡ ወደ አፍሪካ ኮሚሽን ወስደነዋል” – ዶ/ር አወል | Zehabesha Amharic

“የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴን በተመለከተ በኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች ላይ ያለን እምነት በመሟጠጡ ወደ አፍሪካ ኮሚሽን ወስደነዋል” – ዶ/ር አወል | Zehabesha Amharic

ፍርድ ቤት በአንድነትና በመንግስት ተቋማት ዙሪያ ውሳኔ ለመስጠት ቀጠረ


ፍርድ ቤት በአንድነትና በመንግስት ተቋማት
ዙሪያ ውሳኔ ለመስጠት ቀጠረ
በአሸናፊ ደምሴ
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ሕገመንግሥታዊ መብቴን በመጣስ ቅስቀሳ እንዳላካሄድ
ታግጃለሁ፤ አባላቶቼ ያለ አግባብ ታስረውብኛልና ያቀረብካቸው አማራጭ ቦታዎች ወደጎን ተደርገው ህጉ በማይፈቅድለት
አካባቢ ሰላማዊ ሰልፍ እንዳደርግ ተነግሮኛል በሚል በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ በአዲስ አበባ ከንቲባ ጽ/ቤት እና
በአዲስ አበባ ፖሊስ ላይ በመሰረተው ክስ የቀረቡትን የክርክር ሃሳቦች ያደመጠው የፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ
ቤት ልደታ ምድብ 8ኛ ፍትሃ ብሔር ችሎት ውሳኔ ለመስጠት ለግንቦት 26 ቀን 2006 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ።
ሶስቱ የመንግሥት ተቋማት የተመሰረተባቸውን ክስ በችሎት ቀርበው የተከላከሉ ሲሆን፤ በተለይም የአዲስ
አበባ ፖሊስ የፓርቲውን አባላት ማሰሩንና ማገዱን በተመለከተ ሙሉ በሙሉ ድርጊቱን ስለአለመፈፀሙ በህግ አግባብ
ክዶ ባይከራከርም ድርጊቱን የፈፀመው ሕግ እና ስርዓትን ለማስከበር ሲል የመከራከሪያ ሃሳቡን ለፍርድ ቤቱ አሰምቷል።
ፓርቲው ለሰላማዊ ሰልፍ የመረጠው ቦታ ተከልክሎ ከጦር ካምፕ 500 ሜትር ውጪ በሆነ ቦታ ላይ
እንዲያካሂድ የሚያዘውን ህግ በመተላለፍ 50 ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው በጃንሜዳ ሰልፉ እንዲካሄድ መፈቀዱ
ህገወጥ ነው ያለው አንድነት፤ በመቀጠልም ተመሳሳይ ስህተቶች እንዳይደገሙ ይደረግልን ሲል ተከራክሯል። ሌላ
የመከራከሪያ ነጥብ የነበረው አንድ ፓርቲ ለመቀስቀስ ማስታወቅ እንጂ ማስፈቀድ አለበት የሚል ሕግ የለም ሲል
ተከራክሯል። በዚህም ላይ ምላሽ የሰጡት ወገኖች ጃንሜዳ ላይ ሰላማዊ ሰልፉ እንዲደረግ መፍቀዳቸው ህጋዊ ነው
በሚል አስረድተዋል።
ባሳለፍነው ሳምንት ማክሰኞ ሚያዚያ 7 ቀን 2006 ዓ.ም የግራ ቀኙን ክርክር ያደመጠውና በፅሁፍ የደረሱትን
የመከራከሪያ ሃሳቦች የመረመረው የፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 8ኛ ፍትሃብሔር ችሎትም
የውሳኔ ሀሳቡን ለማሰማት ተለዋጭ ቀጠሮ ለግንቦት 26 ቀን 2006 ዓ.ም ሰጥቷል።
sendek

Wednesday, April 23, 2014

የወያኔዎች አስቂኝ መመሪያዎችና ዐዋጆች

April 23, 2014
ነፃነት ዘለቀ (ከአዲስ አበባ)
በመጀመሪያ የክርስትና እምነት ተከታይ አንባቢዎች እንኳን ለ2006ዓ.ም የትንሣኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፡፡
ሕወሓት ወደ ሥልጣን መጥቶ በዓይነቱ የተለዬ የጥቁር አፓርታይድ ሥርዓትን በዓለማችን ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ ካቆመ ወዲህ እጅግ ብዙና ለመቁጠርም የሚያዳግቱ መመሪያዎችንና ዐዋጆችን ቀርፆአል፡፡ አንዳንዶቹን በዘፈቀደና በነሲብ እየቸከቸከ በፈለገው ሰዓትና ወቅት ራሱ ተግባራዊ በማድረግ፣ አንዳንዶቹንም ለማስመሰል ያህል በእንቅልፋምና ደናቁርት የ“ፓርላማ” አባላቱ አማካይነት በዐይን ጥቅሻ በሚታዘዝ የሆዳም ማይማን ጭብጨባ “አጸድቆ” ሥራ ላይ በማዋል ሀገርንና ሕዝብን ማተራመስ ከያዘ ሁለት ዐሠርት ዓመታትን ጨርሶ የሦስተኛውን ዐሠርት አንድ ሦስተኛ ያህል ጊዜ ለማገባደድ ጥቂት ወራት ብቻ ይቀሩታል፡፡
ከቅርቦች ልጀምር፡፡ ቅድም ቡና ስጠጣ እንዲህ የሚል ወሬ ሰማሁ፡፡ እውነት ይሁን ሀሰት ገና አላረጋገጥሁም – ይሁን እንጂ የወያኔን ባሕርይ ለሚያውቅ ይህን ወሬ ሀሰት ነው ማለት የሚያስችል አዲስ ነገር አይገኝም፡፡ ከዚህ የበላለጡ አስቂኝና አስገራሚ መመሪያና ዐዋጆችን እየታዘብን 23 የመከራና ፍዳ ዓመታትን ስላቀናን ይህኛውን የተለዬ አያደርገውም፡፡ የሰማሁት ምን መሰላችሁ – ልማታዊ የወያኔ ሙዚቀኞችና ዳንኪረኞች በኮፒራይት መቸገራቸውን ስላመለከቱና ለዚህም ችግር መባባስ ትልቁን ሚና እየተጫወቱ የሚገኙት የስልኮች ሚሞሪዎችና ብሉቱዝ በመሆናቸው እነዚህን አገልግሎቶች የሚሰጡ ማናቸውም የቴክኖሎጂ ውጤቶች ወደ ሀገር እንዳይገቡ መንግሥት ማገጃ አውጥቷል የሚል ነው፡፡ በዚህም ሳቢያ የእጅ ስልኮችና የመሳሰሉት የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ማዕቀብ ሊጣልባቸው እንደሆነ እየተነገረ ነው፡፡ ለነገሩ ከኢትዮጵያ የወያኔ ሚዲያዎች በውዴታየ ስለራቅሁ ይህ መመሪያ በገሃድ ወጥቶ ይሁን አይሁን እስካሁን አላወቅሁም፡፡ በበዓሉ ምክንያት ከጎረቤት ውጪ ራቅ ወደሚል ሌላ ውጪ አልወጣሁም፡፡ ግን አይሆንም አይባልም፡፡ ወያኔ ከፈለገ “ከዛሬ ጀምሮ ከትግሬ በስተቀር ነጭ ጤፍ እንጀራ የሚበላና ጮማ የሚቆርጥ ሌላ የማኅበረሰብ ክፍል እንዳይኖር ዐውጃለሁ፤ ቢኖር ግን ህገ መንግሥቱን በኃይል ለመናድ እንደቃጣ ተቆጥሮ በአሸባሪነት የክስ ቻርጅ እስከሞት ሊደርስ በሚችል ከፍተኛ ቅጣት ዋጋውን ያገኛል፡፡” ብሎ ሊያውጅ ይችላል፡፡ ማንን ወንድ ብሎ ነው ወያኔ የፈለገውን ከማድረግ የሚቆጠበው? ወያኔ በምን ይዳኛል? በምንም፡፡ ለነገሩ ቀን የሰጠው ጅብ አንበሣንና ነብርን ሲቆረጣጥም ቢታይ ዘመኑ የትንግርት ነውና አያስገርምም፡፡ በኢትዮጵያም ሆነ በተቀረው ዓለም እየሆነ ያለውም ይሄውና ይሄው ብቻ ነው፡፡ ግን ግን በሀገራችን ለወደፊቱ ጅብ የማያሸንፍበትን ቀዳዳ መዝጋት የሚያስችለንን ታላቅ የሦስተኛው ሚሌንየም ሥልት መንደፍ እንደሚገባን ከወያኔው አዋራጅ የተፈጥሮ ልክስክስ ጠባይ የተማርን ይመስለኛል፤ የመንጌን አማርኛ ልጠቀምና ብታምኑም ባታምኑም የአፄውና የደርጉ ሥርዓቶች መንገዱን ባበጃጁለት ወያኔ ክፉኛ ተዋርደናል፡፡ አሸንፎ የማያውቅ ትንሽ ሰው እንዳያሸንፋችሁና መሣቂያና መሣለቂያ እንዳያደርጋችሁ በርትታችሁ ጸልዩ፡፡ ትንሽ ስል ማሸነፍን እንደህልም ይቆጥር የነበረ የባንዳዎችና የሥነ ልቦና ደዌ የተጣባቸው በበቀልና ጥላቻም የተሞሉ ዜጎች ውላጅ የሆኑ መለስን፣ ስብሃትንና ሣሞራን የመሰሉ የታሪክ አራሙቻዎች ማለቴ ነው፡፡ እንደነዚህ ያሉ ቀላሎች በታሪካዊ መደላድሎች መመቻቸት ምክንያት አንዳች ዕድል ካገኙ እንዴቱን ያህል ወጥ እንደሚረግጡና ነገሮችን በምን ያህል ደረጃ እንደሚያበለሻሹ በሚገባ ተረድተናል፡፡ ለማንኛውም ሚሞሪ ያላቸው ስልኮችና መሰል ጋጄቶች ሊከለከሉ ነው አሉ፡፡ አልጋህ ውስጥ ተደብቀህም በሙዚቃ መቆዘም ሊቀር ነው፡፡ ኧረ ባል በሚስቱና ሚስትም በባሏ ቀረጥ እንዳይከፍሉ ያሰጋል፡፡ “እያንዳንድሽ ማን በሚገዛው ሀገር ውስጥ ተኝተሸ ዓለምሽን ትቀጫለሽ?” ብሎ ምቀኛው ወያኔ ለአንድ ግንኙነት ብር 50 ግብር ቢጥልና በየጉያችን ኤሌክትሮኒክ ሥውር ባልቦላ(ማይክሮቺብስ) እንደኖር ፕላንት ቢተክል ባለትዳሮች ምን ይውጠናል? ያቺው ብቸኛ መዝናኛችን ላይ ወያኔ በመብረቃዊ የማጥቃት እርምጃው ቢዘምትባት ወዴትና ለማንስ አቤት እንላለን? የሰይጣን ጆሮ ይደፈን፡፡ የምንተነፍሰውን አየርና የፀሐዩንማ በኑሮ ውድነቱ ላይ ጨምሮ ባልተወለደ አንጀት እያስገፈገፈን ነው፡፡
ከውጭ ሀገራት በበርሜል ዕቃ ማስገባት ተከልክሏል፡፡ በካርቶንና በከረጪት እንጂ በርሜል አይገባም፡፡ ምክንያቱን መጠየቅ አያስፈልግም፡፡ ሊሆን የሚችለው ብቸኛ ምክንያት አንዱ ወያኔ ትግሬ – አንዱ ዘመነኛ በጥጋብ የተወጠረ ትግሬ ወያኔ – የበርሜል ፋብሪካው ገበያው ቀንሷል ማለት ነው፡፡ ለዚህ መፍትሔው ደግሞ ቀላል ነው፡፡ ማታ ሼራተን ወይ ሂልተን ላይ ለሚጋብዛቸው ወያኔ ተጋዳላዮች ለአንዱ ሹክ ማለት ነው – “ከነገ ጀምሮ ከዐረብም ይሁን ከሌላ ሀገር የበርሜል ዘር በቦሌም ይሁን በባሌ ወደኢትዮጵያ ሕዝቦች መኖሪያ ክልሎች እንዳይገባ ጥብቅ መመሪያ አውጣልኝ፡፡” በቃ፡፡ ይቺ ትዕዛዝ ብቻ በቂ ናት፡፡ ከማግስቱ ጀምሮ በርሜል ይቅርና አንዲትም የላስቲክና የብረት ኩባያ ወደሀገር እንዳትገባ ማድረግ ነው፤ ለወያኔዎች ይህን ማድረግ ቀላል ነው፡፡ ሣተናዎቹ ወያኔዎች የፈለጉት ይሆናል፤ ያልፈለጉት አይሆንም – ዘጠና ሚሊዮን ሕዝብ አንቀጥቅጠው መግዛት የቻሉ የአጋንንት ወኪሎች በመሆናቸው ለጊዜው የሚያቅታቸው ነገር የለም፡፡ ይህንን ደግሞ ዕንወቅ፡- እነዚህ ሽል መንጣሪ ዘረኛ የሣጥናኤል ልጆች ከራሳቸው የሚወጣ አንዳችም ኃይል የላቸውም፤ ኃይላቸው የኛ ክፋት፣ የኛ ብዙ ክፋት ነው፡፡ (ለምሳሌ አሁን አንቺ ለኔ መልካም ታስቢያለሽ? ካሰብሽልኝ እሰዬው – ካልሆነ ግን አሁኑኑ ጀምሪውና ሞክሪው፡፡) አዎ፣ በርግጥም ክፉዎች ነን፡፡ በክፋታችንና በአመፀኝነታችንም ሰበብ እያገኘን ያለነውን እያገኘን ነን – በኢትዮጵያ ውስጥ ብቻም ሣይሆን በመላው ዓለም ዙሪያ፡፡ እንጂ እነዚህ የት እንዳሉ እንኳን የማይታወቁ ‹ረቂቅ› ጠላቶቻችን ይህን ሁሉ ሚሊዮን ሕዝብ እንዲህ ኮድኩደው ባላሰቃዩት ነበር፡፡ ወደኅሊናችን ብንመለስ፣ ብንደማመጥ፣ ቁስላችንን ብንመለከት፣ የተፋፋቅነውንና የተጋጋጥነውን በጋራ ለማከም – ለመተካከም- ብንቆርጥ….. እውነቴን ነው የምለው ችግራችንን ለማስወገድ ጥቂት ወራት ብቻ በበቁን፡፡ ግን ብዙዎቻችን በአሉታዊነት የተጠመቅን፣ የክፋታችን ክርፋት ቀድሞን አካባቢን በመጥፎ ጠረን የሚበክል፣ በአስመሳይነትና በሥልጣን ጥም የታወርን፣ በንቀትና በትዕቢት ተወጥረን በጥላቻ ገመድ አንዳችን አንዳችንን የምንጠልፍ፣ በመታች ደብተራና በአባይ ጠንቋይ ድቤ መቺ አበጋር በሰው ላይ እያስመተትንና እያስተበተብን የተቀየምናቸውን ወይም የተመቀኘናቸውን ሰዎች የምናሳብድና የምናደኸይ፣ ለአገዛዝ እንዲያመቸን ብዙኃኑን ዜጎች በማይምነት ጥቁር መጋረጃ ሰነካክለንና በማይረባ የትምህርት ሥርዓት ወጣት ትውልድን አደንቁረን የምናስቀር፣ በሚዲያና በወረቀት ላይ ያልሠራነውን እንደሠራን እያስመሰልን የውሸት ልቃቂት የምንተረትርና የሀሰት እስታትስቲክስ በየዋሃን ዜጎች ጆሮ ዙሪያ የምናዳውር፣ ከጥረት ይልቅ በሰይጣናዊ መንገድና በሙስና በአቋራጭ እንዲያልፍልን የምንሞክር ግብዞችና አንዳችን ለሌላኛችን የማንተኛ ሸፍጠኞች … በመሆናችን የምናስበውን ከመፈጸማችን በፊት ልብንና ኩላሊትን የሚመረምር አምላከ ኢትዮጵያ ስንኩል ዕቅዳችንንና በራስ ወዳድነት ላይ የተመሠረተ አጥፊ ሤራችንን አስቀድሞ የእምቧይ ካብ ያደርገዋል – ይህን ነገር ‹ሀሰት ነው› ብለህ የምትሞግተኝ ካለህ ወደ ኢትዮጵያ ምጣና ተጨባጩን ማኅበረሰብኣዊ ተራክቦ ተመልከት፤ ከዚያም “አሃ፣ እውነትም ወያኔም ሲያንሰን ነው ለካንስ” ብለህ ልትፈርድ ትችላለህ – ይህንን እነሱም ያውቁታል፤ እኛም እናውቃለን፤ ፈጣሪም ያውቀዋል፤ ሰይጣንም ሣይቀር በሚገባ ያውቀዋል – የክፋት ሠራዊት አባላት ግና ጊዜያቸውን በደንብ እንደሚጠቀሙበት የታወቀ ነውና ካለሰዓቱ ንቅንቅ አይሉም፤ ጅብ የጎረሰውን እያላመጠ ይሞታታል እንጂ እየሞተም ቢሆን መብላቱንና ግዳይ መጣሉን በተስፋ መቁረጥ ምክንያት አይተውም፡፡ የሚመር አውነት ነው፡፡
በሳይጋገር ተቦካና በላም አለኝ በሰማይ ገና ለገና ሥልጣን ተገኝቶ፣ ገና ለገና ወያኔ ወድቆ፣ ገና ለገና በሀገር ላይ “ዴሞክራሲ” ‹ሰፍኖ›፣ ገና ለገና ከአንበሣ አፍ ሥጋ ወድቆ ለጅብ ተርፎ … ተቃዋሚዎቻችን የሚያሳዩትን የርስ በርስ መጠላለፍና የሚያካሂዱትን ዶንኪሾታዊ ፍልሚያ እንኳን አታይም? ከዚህ አንጻር ውጥንቅጡንና አስጠሊታውን የታሪካችንን ገጽታ ስናይ በመቶዎችና በሺዎች በሚገመቱ የፖለቲካና ማኅበረሰባዊ ኩይሣዎች እየተቧደንን በሁለንተናዊ የሥነ ልቦናና አካላዊ ጦርነት ለዘመናት መፈሳፈሳችን የወያኔን ተልእኮ ስኬታማነት ለማረጋገጥ ከማገዛችን ውጪ የትም ልንደርስ አልቻልንም፤ ያማረ ንግግር፣ ያማረ የፖለቲካ ፕሮግራምና የተዋበ ፍልስፍናም እንዲሁ የዕውቀታችንን ምጥቀትና የመጻፍ ችሎታችንን ከማሳየት ባለፈ የረዳን ነገር የለም – እንጂ ለምሁር ለምሁርማ ስንት ሺህ ዶክተርና ፕሮፌሰር ሞልቶን አልነበረምን? የጥንት አስተሳሰብ በዘመናዊ ቆዳ ተሸፍኖ በጠበጠን እንጂ ንግግር ዐዋቂና ነገር ሰላቂማ ሞልቶናል፡፡ እናሳ፡- ከእኛ ከኢትዮጵያውያን በላይ ጉዶችና ተዓምረኞች ይገኛልን? “እባብ ልቡን አይቶ እግሩን ነሣው” እንደምንል የብዙዎቻችን ፍላጎት ከአነጋገራችንና ከዐይነ ውኃችን ጭምር ይታወቃል፤ በክፉ አሳባችንም ምክንያት ውጥናችን ሳይጀመር ይከሽፋል፡፡ እናም እንደመፍትሔ ሁላችንም እውነተኞች እንሁን፤ ማስመሰልን እንጠየፍ፤ ለወገናችን የዓዞን ሣይሆን ለልጇ ስትል እንደተወጋችው ጎሽ ከአንጀት እናልቅስ፤ ከዘረኝነትና ጎጠኝነት አረንቋ ባፋጣኝ እንውጣ፤ ያለንበትን ዘመን እንረዳ፡፡ ወገናችንን እንውደድ – እናፍቅርም፤ ሀገራችንንና ሕዝባችን የምንለውን ወገናችንን ለሥልጣን መወጣጫነት ሣይሆን በሀቅ ወደን እስከሕይወት መስዋዕትነት ትልቅ ዋጋ በመክፈል ከገቡበት አዘቅት እናውጣቸው፡፡ ያኔ ነው ፈጣሪ የሚባርከንና ዕቅዳችንን ቀድሶ በተገቢው መንገድ እውን የሚያደርግልን፡፡ አለበለዚያ ወያኔ አሁን እንደሌለ ሁሉ በሌለበት ሁኔታ አገዛዙን በእጅ አዙር ቀጥሎ የመለስና የመሪ ድርጅቱ የወያኔ አፅም ጉድጓድ ውስጥ ሆነው በሹምባሾቻቸው አማካይነት እስከወዲያኛው እያንቀጠቀጡ ይገዙናል – ልብ አድርጉ የሚገዛን ግን የወያኔ ጥንካሬ ሣይሆን የኛ ልፍስፍስነትና የኛ መጥፎ ሃሳብ ካርማዊ ዕድፍ የሚያጠላብን የመርገምት ውጤት ነው፡፡ አሁንና እስካሁን አንድ ያላደረገን የተለያየው ፍላጎታችን እንጂ የሚደርስብን ግፍና በደል ተለያይቶ እንዳልሆነ ይታወቃል፡፡ እስከዚህን ደረጃ ያለያየን ለምንም ዓይነት ሕዝባዊ ስቃይ ሊንበረከክ ያልቻለው ግላዊ የሥልጣንና የሀብት ፍላጎታችን እንጂ በርግጥም በእውነት ተለያይተን እንዳልሆነ ኅሊናችን ያውቀዋል፡፡ (በሰላም ቀን የሀገራችን ልዩ መመኪያ ሊሆናት ይችል የነበረውና በሥልጣንና ሀብት አራራው ምክንያት ግን የወያኔ ሥውር ወኪል (mole/double agent) ሆኖ ሀገሩን በክፉ ቀን ከድቶ ከጠላቶቿ ጋር ያበረው ልደቱ አያሌው እንዲያ በመንታ እያነባ ለኢትዮጵያና ሕዝቧ “ሕይወቱን” እስከመሰዋት በሚደርስ “ጽናት” ዝዋይና ሸዋሮቢት የተንከራተተው ለማንና ለምን እንደሆነ በተለይ አሁን ላይ ቁልጭ ብሎ ይታየናልና ከዚህ ዓይነቱ ቁጭ በሉ አስተሳሰብና ዕኩይ ድርጊት በቶሎ እንውጣ፡፡ እውነቴን ነው – በተለይ ከእንግዲህ ማንም ማንንም ሊያታልል አይችልም፡፡ ሁሉም ነቅቷል ፤ ቀኒቷን ግን በጉጉት ይጠብቃል – የነፃነቷን የማትቀር ቀን፡፡) በበኩሌ የወደፊቷ ኢትዮጵያ ለዚህ ዓይነቱ ፖለቲካዊ ድራማ የማትመች እንደምትሆን ተስፋ አለኝ፡፡ አማራ – ትግሬ፣ ኦሮሞ – ሶማሌ …. መባባሉ የታይታና ዘመን ያለፈበት የትግል ስትራቴጂ እንጂ ውስጠ ምሥጢሩ ሌላ መሆኑን እናውቃለን፡፡ ሌላው ልብ ማለት የሚገባ ነገር ደግሞ አራት ኪሎ ቤተ መንግሥት ዘጠና ሚሊዮን ወንበር የለውም፤ አንድ ነው፡፡ ያንንም በዘር ሣይሆን በ‹ሜሪት›ና በሕዝብ እውነተኛ ምርጫ ማስያዝ ይጠበቅብናል – ጊዜው ሲደርስ፡፡… እውነትን ተናግሮ እመሸበት ማደር እንዲህ ይመስለኛል፡፡ ወዳልተነሳሁበት ርዕስ ጥልቅ እያልኩ ማስቸገሬን ይቅርታ አድርጉልኝ፤ ወድጄን እንዳይመስላችሁ፡፡
በዚህ ዘመን ወያኔዎችን “ይህ እኮ ህገ መንግሥታዊ መፍቴ ነው!” ብትል “እሱን ቀቅለህ ከቤተሰቦችህ ጋር ሆነህ ብላው!” ሊሉ ይችላሉ ብቻ ሣይሆን ዘወትር የሚደግሙልህ ውዳሤ ማርያማቸውና መዝሙረ ዳዊታቸው ነው፡፡ ህገ መንግሥቱ – ምን አለፋህ ወንድሜ – የዐዋጁን በጆሮ እንዳትለኝ እንጂ ለአሰለጥ ትግሬዎችና ለፌዴራል የትግሬ ሠራዊት በፍጹም አይሠራም – ሀገርን በቅኝ ግዛት ለወረረ የአንበጣ መንጋ ምክንያታዊነትና ሰብኣዊነት የሚገመዝዘው ቀልድ በመሆኑ ከጠበንጃ ውጪ የሚታየው የችግሮች ማስወገጃ ሌላ ብልሃት ብሎ ነገር የለም፤ ጤናማና ለኅሊናው ተገዢ የሆነ ትግሬ እንደኛው መሰቃየቱን በታሳቢነት ያዝልኝ ታዲያ – ጥቂትም ቢሆኑ አሉ፤ የምን ጥቂት – ብዙ ናቸው ኧረ! እርግጥ ነው ነገሩ ዕንቆቅልሽና ግራ የሚያጋባ ሊመስል ይችላል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት የሚባለውን የሥልጣን ቦታዎችን፣ የንግድ ተቋማትን፣ የአነስተኛና ጥቃቅን ንግዶችን፣ የሕንፃዎችንና የፋብሪካዎችን ባለቤቶች፣ የመንግሥት ቤቶችን በነፃ ተከራዮችን፣ ኮንዶሚኒየም ቤቶችን፣ የወታደርና የፖሊስ ተቋማትን፣ የደኅንነት መዋቅሩን፣ የባንኩንና የአክሲዮን ሸያጩን፣ ውድ ውድ የሚከፈልባቸው ትምህርት ቤቶችንና ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን፣ መዝናኛ ሥፍራዎችን፣ … በጠቅላላው በሀብቱ ማማ ላይ ፊጥ ያለውንና በትንሹም በትልቁም ሲቆጣ የቀድሞ ወንድምና እህቶቹ የአሁን አሽከሮቹና አጫዋች አኗኗሪዎቹ ላይ፣ የሀብቱም አድናቂዎች የሆኑ ሌሎች ምሥኪን “ወገኖቹ” ላይ በዕብሪት “እቧይ” ሲል የምትሰማውን ትግሬ ስታይ ኢትዮጵያ በአንዳች ትግሬያዊ ምትሃትና ሰሜናዊ ዋግ የተመታች ሊመስልህ ቢችል ዘመኑና አበቅቴው ነውና ቻል ማድረግ ሊኖርብህ ነው፡፡ ኧረ እንዲያውም በተጋቦት ትግሬ የሆነ ሌላ ዜጋም ሲያስመስል “እቧይ!” ሲልና የስልክ መጥሪያውን ካለውዴታው ለማስመሰልና ለመወደድ ሲል ብቻ የትግርኛ አድርጎም ልትታዘብ ትችላለህ፤ አቤት ይህ ጊዜ ሲገርም – ራስን ሲያሳጣና ባዶ ሲያስቀር፡፡ ዘመቻው እኮ ሁለገብ ነው – ኢኮኖሚያዊም፣ ወታደራዊም፣ ሥነ ልቦናዊና ባህላዊም፣ ሃይማታዊም፣ ምናምናዊም ሁሉ ነው፡፡ ታዲያን እንዲህ ያለ ነገር በታሪክ አልፎ አልፎ ሊያጋጥም እንደሚችል “ሚዉቴሽናል ክስተት” በመቁጠር መታገስ ይኖርብናል – ቂሎችን ተከትሎ ቂል መሆንና ለቂም በቀል መነሳሳት አይገባም ብቻ ሣይሆን ቂም በቀል የሚወልደው ሌላ ቂም በቀልንና የዐመፃ ተግባርን በመሆኑ ከዚህ ዓይነት ሃሳብ መታቀብ አማራጭ የሌለው ግዴታ ነው – ከእግዚአብሔር መንገድ የወጡ ሰዎች ከዚሁ የፈጣሪ መንገድ ሊያስወጡን አይገባም – ምንም እንኳን የነሱ ፍላጎት ይሄው ቢሆንም እኛ ግን እነሱ በመጡበት መንገድ በጅልነት ልንማገድበት አይገባንም – ጎጂ ነው፤ ለጊዜው ካልሆነ በዘለቄታዊነት አያዋጣምም፡፡ የአነስታይንን ምክር መቀበል አለብን – “አንድ ችግር በተፈጠረበት የአስተሳሰብ ደረጃ ተጉዞ ችግሩን ማስወገድ አይቻልም፡፡” ክርስቶስም ቀድሞ አለ “ጠላትህን ውደድ፤ አንድ እርምጃ ከእርሱ ጋር እንድትራመድ ቢጠይቅህ ሁለት ድገምለት፤ እጀ ጠባብህን ቢጠይቅህ መጎናጸፊያህንም ድገምለት፤ ግራ ጉንጭህን ቢጠፋህ ቀኝህንም ድገምለት …” ይህ ምክሬ የተለያዩ የትግል አማራጮችን ለሚከተሉ ወገኖች እንደማይጠቅማቸው አውቃለሁና ከነርሱ አንስቻለሁ፡፡ ምርጫን ደግሞ አከብራለሁ – እንደምርጫ፡፡ ይህ አስተያየቴ ተቀባይነት እንዲኖረው የምሻው በተለይ በሃይማኖቱ ማኅበረሰብና በሰላማዊው ሕዝብ መካከል ነው፡፡

የህወሓት ጁንታ ከሰሞኑ መረር ያለ እርምጃ ‹‹ግድያ›› ማሰቡን ከጓዳው የወጣ የወሬ ምንጭ ደረሰን፡፡

ሀገር የመገንጠል ዓላማ ይዞ የተነሳው የህወሓት ጁንታ፣ በስውር እና በአደባባይ የጫካ ልማዱን መሰረት አድርጎ ሲገድል መኖሩ አዲስ ባይሆንም፣ ከሰሞኑ መረር ያለ እርምጃ ‹‹ግድያ›› ማሰቡን ከጓዳው የወጣ የወሬ ምንጭ ደረሰን፡፡
ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት በአዲስ አበባ አስተዳደር ጽ/ቤት ተገኝቼ ነበር፡፡ የመገኘቴ ዓላማም የፊታችን እሁድ ሚያዚያ 26 የሚደረገውን ሰላማዊ ሰልፍ አስመልክቶ የዕውቅና ደብዳቤውን ለመስጠት የተያዘውን ቀጠሮ በማክበር ነበር፡፡
የሰላማዊ ሰልፍ እውቅናን በተመለከተ ኃላፊ የሆኑት አቶ ማርቆስ ፎርም እንዲሞላ አዘዙ፤ የተባለውን ፎርም ሞላን፤ ያን ጊዜ የአቶ ማርቆስ የቢሮ ስልክ አንቃጨለ፤ አነሱት ……ቀጭን ትዕዛዝ ከወዲያ ማዶ……………
‹‹የአንድነትን ሰላማዊ ሰልፍ በተመለከተ ዕውቅናው እንዳይሰጥ ይቆይ›› አቶ ማርቆስ ፊቱ ተለዋወጠ ‹‹ ይቅርታ አድርግልኝ የኔ ችግር አይደለም›› ሌላ ቃል ካፉ አልወጣም፡፡
«አልገባኝም ….ቀጠልኩ ….የአንድነት ሰላማዊ ሰልፍ ተከለከለ እያልከኝ ነው ? »
መለሰ …..«እኔ ምን ላድርግ ? …..»
«የከለከለው ማነው የበላይ ኃላፊ ነው ? »
«አዎ» አጭር መልስ፡፡
ትቼው ወደ ከንቲባ ጽ/ቤት ኃላፊው አመራሁ፤ ስብሰባ ላይ ናቸው፡፡ ወደ ፓርቲ ጽ/ቤት ደውዬ ሁኔታውን አሳወኩ። የፓርቲው ፕሬዘዳንት ኢንጅነር ግዛቸውን ጨምሮ በርካታ አመራሮች ፈጥነው ደረሱ፡፡ የአስተዳደሩ ስብሰባም ለሻይ እረፍት ተቋርጦ ኃላፊው ወደ ቢሯቸው ሲገቡ ተከታትለን ገባን፡፡ ላለማናገር ጥቂት አንገራገሩ ። የቢሯቸውን በር አንቀን አናግሩን በማለት ጸናን፡፡
‹‹ምንድነው ችግሩ የሰልፉ ጉዳይ ከሆነ ጨርሰናል፤ እውቅናውን ወሰዳችሁ አይደለም ? ›› አሉ።
ባጭሩ መልስ ተሰጣቸው ፤ «አልወሰድንም ። የአቶ ማርቆስ መልስ ተከልክሏል የሚል ነው፡፡ »
ጥያቄ አስከተልን ……«እርሰዎ መረጃ የለዎትም ? መንግስታዊ ኃላፊነቱ የርስዎ ነው፤ ማነው ከልካዩና ፈቃጁ ? »
መልስ የለም ። ጥቂት ዝም ብለው ‹‹የጠየቃችሁን ሚያዚያ 19 ለማድረግ ነበር፡፡ በዚያ ቀን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የጥበቃ እጥረት አለብኝ በማለት ስላመለከተ የእናንተ ሰልፍ ለሚያዚያ 26 እንዲደረግ ጠየቅናችሁ ። ተስማማን ከዚህ ውጪ የተደረገ ነገር ካለ በኔ በኩል መረጃ የለኝም። ማን እንደከለከለ አናውቅም››
« ስለዚህ ይህንን ከተማ ከንቲባው ካልሆነ ማን ነው የሚመራው? »
ከወዲያ ማዶ መልስ የለም……….ስልክ አነሱ እና አቶ ማርቆስን ወደ ቢሯቸው ጠሩ ። ሰውዬው መጡ ። ማጣሪያ ተጠየቁ። «መመሪያ ደርሶኛል» ሲሉ ለከንቲባው ጽ/ቤት ኃላፊ በኛው ፊት ተናገሩ፡፡ «መመሪያ ሰጪው ማነው?» ወደ አንዱ ቢሮ ዘው ብለን አንድ ሰው አናገርን ………..
‹‹እባካችሁ ይቅርባችሁ ደህንነቶቹ የሚውሉት እዚህ ግቢ ነው፡፡ አንድነቶች ከወጡ እርምጃ ይወሰድ ሲሉ ሰምቻለሁ›› አለን በማንሾካሾክ ድምጽ ………….
ጎበዝ ይሙት ሰነፍ ይኑር ቢሻው
አተላ መሸከም ይችላል ትከሻው………..
ፍርሃት ማነው ቢሉኝ ስሙን አላውቀውም
ሞትን በቁሜ እንጂ ሞቼ አልጠብቀውም፡፡
………………..ህወሓት ሊተኩስ ተዘጋጅቷል እኛም የነሱን ጥይት የሚሸከም ደረት …….እመነኝ ካልገደሉ አያቆሙንም፡፡፡
posted by Aseged Tamene

Monday, April 21, 2014

ስለፍትህ ሲባል ስርዓቱ ይፍረስ! ክፍል ሶስት (ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ)

ልዕለ ኃያሏ ሀገረ-አሜሪካን ዛሬ ለተጎናፀፈችው የሕግ የበላይነት የተከበረበት ሥርዓት መሰረት የጣሉት እነ ቶማስ ጃፈርሰን በነፃነት አዋጃቸው ላይ ‹‹ሁሉም ሰዎች በእኩልነት የተፈጠሩ ናቸው›› በማለት ሲደነግጉ፤ እንግሊዛዊው ደራሲ ጆርጅ ኦርዌል ደግሞ “Animal Farm” በሚለው መፅሐፉ፣ ጉልበታም ‹‹ገዥ›› አድርጎ በሳላቸው ገፀ-ባሕሪያት አማካኝነት ‹‹…አንዳንድ እንስሳት (ሰዎች) ግን የበለጠ እኩል ናቸው›› ይለናል፡፡ በርግጥ ሁለቱም አይነት አስተዳደሮች መሬት ወርደው ዓለማችንን ዲሞክራት እና አምባ-ገነን በማለት በሁለት ጎራ የከፈሉ የመሆናቸው ጉዳይ አከራካሪ አይደለም፡፡ ራሷ አሜሪካንን ጨምሮ አብዛኛው የአውሮፓ አገራት ከሞላ ጎደል በዜጎች እኩልነት ላይ የተመሰረተ ማሕበረሰብ መገንባት ከቻሉት ውስጥ ሲመደቡ፤ ብዙሃኑ የአፍሪካ እና የእስያ መንግስታት ደግሞ ‹‹አንዳንድ ሰዎች ይበልጥ እኩል ናቸው›› በሚል መንፈስ የተቃኘ አገዛዝ አንብረው፣ የትኛውንም ተግዳሮት በጠብ-መንጃ ዓይን መመልከትን ፈቅደዋል፡፡ ከእነዚህኞቹ መካከል የእኛይቷ ኢትዮጵያ ዋነኛዋ ናት፡፡Temesgen Desalegn "Fact" Ethiopian Amharic newspaper editor
ባለፉት ሁለት አስርታት በጠቅላይነት የጨዋታ ሕግ እየተመራ፣ ከሰሜን-ደቡብ የተንሰራፋ መዋቅር መዘርጋቱ የተሳካለት ኢህአዴግ፤ የፖለቲካ ሳይንስን በአብዮታዊነት ለውጦ፣ ሀገሪቱን ለጥቂቶች የፌሽታ፣ ለብዙሃኑ የዋይታ መድረክ ሲያደረጋት አንዳች ኮሽታ ያለመሰማቱ መነሾም ይኸው ነው፡፡ ለሕግ ከማይገዙ ፖለቲከኞች እና ወዳጅ ዘመዶቻቸው አንስቶ፣ በአንድ ጀንበር ሰማይ-ጠቀስ ህንፃን እንደጓሮ አትክልት የሚያፀድቁ ‹‹አባ-መላዎች›› መበርከታቸው አስማታዊ-ጥበብ ያልሆነብንም ለዚሁ ነው፡፡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን እንኳ ያላጠናቀቁ አፍላ-ወጣቶች ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ባላቸው መኪኖች መምነሽነሻቸውም ሆነ፣ ለአቅመ አዳም ሳይደርሱ ግዙፍ የአስመጪና ላኪ ድርጅት ባለቤት ሆነው ማየታችን ይህንኑ ያስረግጥልናል፡፡
አብዮታዊ ግንባሩ ከፊተኞቹ ንጉሳዊም ሆነ ወታደራዊው አስተዳደር የሚለይበት ክፉ ገፅታዎች አሉት፡፡ ለአብነትም ከአጀንዳችን ጋር በሚዛመደው የፍትሕ ሥርዓት ማነፃፀር ይቻላል፡፡ በአፄው ዘመን በአንፃራዊነት የሰፈነው የሕግ የበላይነት በሂደት ተንኮታኩቶ ቢወድቅም፤ ደርግ በጎዳና ላይ የፈፀመው ዘግናኙ የቀይ ሽብር ጭፍጨፋ ምዕራፍ ከተዘጋ በኋላ ባሉት የሥልጣን ዘመናቱ፣ በእውቀት የበቁ እና ከአድሏዊነት የራቁ ሊባሉ የሚችሉ ዳኞች እና ዐቃቢያነ-ሕግ በመሾም፣ ዛሬ ካለው የተሻለ ተቋማዊ የፍትሕ ስርዓት ለመገንባት መሞከሩን የጊዜው መዛግብት ያወሳሉ፡፡ ከዚህ ባሻገር በሕግ ባለሞያዎች እንደመልካም ነገር የሚጠቀሰው ‹‹ጠቅላይ ዐቃቤ-ሕግ›› ተብሎ አንድ ሰው ተመርጦ የሚሾምበት አሰራር ነበር፡፡ ምክንያቱም በዚህ ቦታ የሚመደብ ግለሰብ የሀገሪቱን መሪዎችን ጭምር መክሰስ የሚችልበት ተቋማዊ ሥልጣን ያለው ከመሆኑም በላይ ‹‹አደገኛ ናቸው›› የተባሉ የህትመት ውጤቶችንም ሲያምንበት ሳይሰራጩ ቀድሞ እስከማገድ የሚያደርስ ሥልጣን ነበረውና፡፡ ይህ አይነቱ አሰራር በምዕራባዊያን ሀገራት የተለመደ ሲሆን፤ የቀጥታ ሥርዓታዊ ተጠያቂነትንም ስለሚያስከትል በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ሕግ ለማስከበር ጠቃሚ መሆኑ በዘርፉ ምሁራንም ዘንድ የታመነበት ነው፡፡ በደርግ ዘመን (ለርዕሰ-ብሔሩ ታማኝ የመሆን ግዴታውን ሳንዘነጋ) ለክስ የሚያበቃ ማስረጃ ካገኘ፣ በየትኛውም የሥልጣን እርከን ላይ ያለ ሹመኛን በሙሉ ፍርድ ቤት ከመገተር የማያስመልስ ሥልጣን እንደነበረው ይነገራል፡፡
ይሁንና ይህ ሁናቴ የግርንቢጥ ተመንዝሮ የፍትህ ስርዓቱን ከማፀየፍም ተሻግሮ፣ በሕግ ፊት እኩል ያልሆኑ ወይም በኦርዌላዊያን ቋንቋ ይበልጥ እኩል የሆኑ ‹‹ዜጐች› ተበራክተው የታዩት በዘመነ-ኢህአዴግ ነው ብል ብዙም ስሁት ድምዳሜ አይሆንም፡፡ ከዓመታት የጥምዝምዞሽ ጉዞ በኋላም የተቀደሰችዋ የፍትሕ ምኩራብ ረክሳ፣ የዜጎች መብት ተደፍጥጦ፣ ‹‹ሕገ-አራዊት›› ገንግኖ፣ ጠብ-መንጃ መንገሱ ሊስተባበል የማይችል ሀቅ ሆኗአል፡፡በርግጥ ከሁሉም አስከፊውና አሳሳቢው ጉዳይ የፍትሕ ሥርዓቱ ለዝግመታዊ ሞት መዳረጉ ነው፡፡ ይህንን እውነታ ፕሮፍ መስፍን ወልደማርያም ‹‹አገቱኒ›› በተሰኘው መጽሐፋቸው የነገሩን ግላዊ ገጠመኝ በሚገባ ከማስረዳቱም ባሻገር፤ ይህን ዘመን ካለፈው ዘመን እንድናነፃፅረው ዕድል ይሰጠናልና ልጥቀሰው፡-
“ሁለት በጣም የተለያዩ አሰራሮች አጋጥመውኛል፤ መጀመሪያ በአፄ ኃይለሥላሴ ዘመን ተይዤ ነበር፤ በአንድ መጻሕፍት ቤት ቆሜ ስመለከት አንድ ሰው መጣና መታወቂያውን ከአሳየኝ በኋላ መጥሪያ ወረቀት አሳየኝ፤ እንሂድ ብሎ ይዞኝ ሄደና በወንጀል ምርመራ አንድ ክፍል ውስጥ አስገባኝ፤ ሁለተኛው በወያኔ ዘመን በ1992ና በ1998 የተያዝኩበት ነው፤ ሁለቱንም ጊዜ ከአስር እስከ አስራ አምስት የሚሆኑ የታጠቁ ወታደሮች ነበሩ፤ በ1992 የተያዝኩት አንድ የመጻሕፍት መደብር ውስጥ ቆሜ ነበር፤ ከአስር እስከ አስራ አምስት የሚሆኑ የታጠቁ ወታደሮች በአካባቢው ተበታትነው ለጦርነት የተዘጋጁ ሆነው ሲጠብቁ ሶስት ያህሉ በመጻሕፍት ቤቱ ገብተው ይዘውኝ መኪና ውስጥ አስገቡኝ፤ በጥቅምት 22/1998 ግን ታምሜ ተኝቼ ነበር፤ ብርቱካንና ሙሉነህ ሊጠይቁኝ መጥተው ቁጭ ብለን እናወራ ነበር፤ በድንገት የቤቱን በር ሊያፈርስ የተቃጣ ድብደባ ሰማሁና ስከፍት ጠመንጃውን ደግኖ ‹ኑ ውጡ!› እያሉ ማንገላታት ጀመሩ፤ ልብሴን እንድለብስም አልፈቀዱልኝም፤ ማዕከላዊ ወስደው በአንዳንድ ክፍሎች ውስጥ ቆለፉብን፡፡” (ገፅ 54)
መንግሥታዊው ሙስና
በደርግ ዘመን ከጥሬ ስጋ እና ከውስኪ ግብዣ ያላለፈው ሙስና፤ ዛሬ በቢሊዮን ደረጃ የሀገር ሀብትን እስከ ማስበዝበር ተደርሷል፡፡ ከሶስት ዓመት በፊት የተባበሩት መንግስታት፣ በኢህአዴግ የሥልጣን ዘመን ከሀገሪቱ 8.6 ቢሊዮን ዶላር በሕገ-ወጥ መንገድ ተዘርፎ በአንዲት የላቲን አሜሪካ ደሴት መደበቁን በሪፖርቱ መግለፁ አይዘነጋም፡፡ በአናቱም ‹‹ሲሾም ያልበላ…›› እንዲሉ፤ ምንም እንኳን የዛሬው ቁጭታቸው አግባብ ባይሆንም፣ አንድ የቀድሞ የደርግ ባለሥልጣን፣ ከእስር በተለቀቁ ማግስት ማረፊያ የማጣታቸው ነገር አንገብግቧቸው እንዲህ ብለውኝ እንደነበር ትዝ ይለኛል፡- ‹‹(ከኢህአዴግ ጉምቱ መሪዎች አንዱ የነበረና በሙስና የተከሰሰን ሰው በስም ጠቅሰው) እስር ቤት ካየሁት በኋላ፣ አንዳች ነገር ከዚህች ሀገር ባለመውሰዴ ይቆጨኛል፡፡ እርሱ ስለታሰረ ቤተሰቦቹ ምን ሆኑ? በደህና የስልጣን ጊዜው ባካበተው ሀብት ለልጆቹም መትረፍ ችሏል፡፡ እኔ ግን የምኖረው በሌሎች ሰዎች ደግነት ነው››፡፡ ይህ የሰውየው ፀፀት ያረበበበት አስተያያት በጥቂቱም ቢሆን የደርግና የዚህን ሥርዓት የሙስና ሁለንተናዊ ሥርዓት መጠቆሙ አይቀርም፡፡
በርግጥ ኢህአዴግ አራት ኪሎን በተቆጣጠረ ማግስት የግንባሩ ቀዳማይ መሪዎች (የተከሰሱትም፤ ያልተከሰሱትም) ‹ኢትዮጵያ አጣዳፊ ዕዳ ውስጥ ገብታለች› በሚል ሰበብ ‹ሙስናን በግላጭ ጀመሩ› ከሚባሉት አንስቶ፤ የኮንትሮባንድ፣ የንግድ ማጭበርበርና የታክስ ስወራና ቅነሳን ጨምሮ፣ ከዚህ ቀደም ተሰምቶ በማይታወቅ መልኩ በሚሊዮን የሚቆጠር ብር ለአራጣ ብድር የመዋሉ እውነታ አገዛዙ ከጥቂት ባለሀብቶች ጋር በጥቅመኝነት የተሳሰረ መሆኑን ይነግረናል ብዬ አስባለሁ፡፡ እንደ ምሳሌ ከአራጣ ብድር ጋር ተያይዞ የተከሰተውን አስደንጋጭ ጉዳይ ብናነሳው ውንጀላውን ምክንያታዊ ያደርገዋል፡፡
እንደሚታወሰው በ2001 ዓ.ም የጌታነህ ትሬዲንግ ሥራ አስኪያጅ አቶ ዮሐንስ ጌታነህን ጨምሮ የ‹‹አሴ ማርብል›› ድርጅት ባለቤት አቶ ምክንያቱ ኃይሌ ራሳቸውን መግደላቸው፣ ጉዳዩን ከጓዳ ወደ አደባባይ አምጥቶታል፡፡ በወቅቱም አሳዛኙን ክስተት ተከትሎ ወሬው ከቁጥጥር ውጪ በመውጣቱ በማሕበረሰቡ ውስጥ የፈጠረው ውዥንብርና ጉሩምሩምታን ለማለዘብ፣ መንግስት በአራጣ ማበደር የጠረጠራቸውን ዘጠኝ ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር ከማዋል አልፎ፣ በኢቲቪ በኩል ዶክመንተሪ ፊልም አዘጋጅቶ የአንድ ሳምንት ርካሽ ፕሮፓጋንዳ ነዝቶበታል፡፡ ‹‹ማነህ ባለሳምንት?›› የሚል የምስጢር ኮድ (ርዕስ) በተሰጠው በዚህ ዶክመንተሪ ፊልም፤ የዛሬን አያድርገውና ገብረዋህድ ወ/ጊዮርጊስ የዘመቻው ፊት-አውራሪ መስሎ በመቅረብ ‹‹ጀብዱውን›› አለቅጥ አጋንኖ እንደተረከልን
እስታውሳለሁ፡፡ እንዲህ እንደዛሬው ‹ባለሳምንት፣ በል አንተም ግባ!› ከመባሉ በፊት፤ የሙስና-ፀር፣ የሙሰኞች ቀንደኛ ጠላት መስሎ በመተውን ብቃቱ የሚታወቀው ገብረዋህድ ወ/ጊዮርጊስ በዶክመንተሪው ‹ለሙሰኞች ምንም ምህረት የለንም!› እያለ ሲዝት የተመለከተው ሕዝብ በእጅጉ አድንቆት ነበር (በነገራችን ላይ በዶክመንተሪው ፊልም ውስጥ ከገብረዋህድ እኩል መሬት አልበቃው ብሎት የነበረው የገቢዎችና ጉምሩክ ዓቃቢ-ሕግ እሸቱ ወ/ሰማያት ከእነ ገብረዋህድ ጋር አብሮ የታሰረ ቢሆንም፤ አሁን ከእስር ተፈትቶ በቀድሞ አለቆቹ ላይ ምስክር እንዲሆን መደረጉን ከምንጮቼ አረጋግጫለሁ)፡፡ የሆነው ሆኖ አሳማው ናፖሊዮን ‹‹አንዳንድ ሰዎች ግን ይበልጥ እኩል ናቸው›› እንዲል፤ በወቅቱ እነ ገብረዋህድ ከተከሳሾቹ መካከል ለፍርድ እንዳይቀርቡ ያደረጓቸው ጥቂት ወንጀለኞች መኖራቸውን ማወቅ የምንችልበት የነብይነት ፀጋ አልነበረንም፤ የሆነው ግን እንዲያ ነው፡፡ ለአብነትም በጊዜው በስፋት ያነጋገረው የዮሐንስ ጌታነህ ራስን የማጥፋት ወንጀል፣ ከኬኬ ትሬዲንግ ባለቤት አቶ ከተማ ከበደ ጋር የተያያዘ ስለመሆኑ ‹‹ጉዳዩ ይመለከተኛል›› ለሚለው ጉምሩክና ገቢዎች መረጃው ቢደርሰውም ተጠርጣሪው በነፃ መለቀቁን መጥቀስ ይቻላል፡፡ጌታነህ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማሕበር ከዋና ስራ አስኪያጁ አቶ ዮሀንስ ህልፈት በኋላ በሐምሌ 13 ቀን 2001 ዓ.ም ለኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን‹‹ጉዳዩ፡- መረጃ ስለመስጠት›› በሚል ርዕስ ሥር የፃፈውን ደብዳቤ ቀንጭበን እናንብብ፡-
‹‹ድርጅታችን ጌታነህ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በአራጣ አበዳሪዎች ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበትና በአሁኑ ጊዜም ለከፋ ኪሳራ የተዳረገ ሲሆን፣ ከአራጣ አበዳሪዎች መካከል የኬኬ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማሕበር ዋና ስራ አስኪያጅ እና የድርጅቱ ባለቤት አቶ ከተማ ልጅ የሆኑት ወ/ት ትዕግስት ከተማ አንዱ ናቸው፡፡ …በኚህ ግለሰብ የጭካኔ ተግባር ኩባንያውን በፍትሐ ብሔር ክስ መስርተው ከማዋከብ በተጨማሪ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ አጥናፉ ጌታነህን በእጃቸው በሚገኝ ቼክ /በአራጣ ዋስትና/ በወንጀል በመክሰስ የ6 ወር እስራት በማስፈረድ፤ እንዲሁም በኩባንያው ስራ አመራሮች ላይ ከፍ ያለ የሥነ ልቦና ጫና በመፍጠር በምናካሄደው የንግድእንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ ኪሳራና በደል አድርሰውብናል…››
ከጉዳዩ ሰለባ ይህ አይነት ተጨባጭ መረጃ፣ የደረሰው ገቢዎችና ጉምሩክ ግን፣ በወቅቱ አቶ ከተማ ከበደ ላይ ክስ ለመመስረት አልደፈረም፡፡ እኮ ለምን? ለዚህ ጥያቄ፣ የምናገኘው ብቸኛ ምላሽ ከሙስና ጋር የተያያዘ ስለመሆኑ፣ ራሱ የተቋሙ የወቅቱ ዳይሬክተርአቶ መላኩ ፈንቴ በቁጥጥር ሥር ከዋለ በኋላ ለመርማሪዎች ከሰጠው ቃል ውስጥ፡-
‹‹ሳሙኤል ታደሰ የተባለና በመሥሪያ ቤቱ የሕግ ምክር ቡድን ዐቃቢ ሕግ የሆነው ግለሰብ እቢሮዬ መጥቶ ‹የከተማ ከበደን ክስ ገብረዋህድ በገንዘብ ተደራድሮ ክሱ እንዲነሳ እያደረገ ነው› አለኝ›› በማለት መጠቀሱን ተመልክቻለሁ፡፡
በርግጥ ይህን መሰል አደገኛ የሕግ ጥሰት እየተፈፀመ ስለመሆኑ የሚያመላክት ከባድ መረጃ ለመላኩ ፈንቴ የሰጠው የበታች ሰራተኛው አቶ ሳሙኤል ብቻ አይደለም፤ በፓርቲውም ሆነ በፖለቲካው ላይ ተፅእኖ ፈጣሪ የሆነው በረከት ስምኦንም ጉዳዩን አንስቶለት ነበር፡-

‹‹አቶ በረከት ቢሮ በአካል እንድገኝ ጠርቶኝ በሄድኩበት ወቅት ‹የከተማ ከበደን የአራጣ ኬዝ ገብረዋህድ ተደራድሮ ክሱን አንስቶለታል ይባላል፣ ጉዳዩን ታውቀዋለህ ወይ?› ብሎ ጠየቀኝ፡፡ እኔም ‹ግለሰቡ ተደጋጋሚ ጊዜ እንደስራ {እንደ መደበኛ ሥራ} አድርጎ መስራቱን የሚያሳይ ማስረጃ ስላልተገኘ ክስ አልመሰረትንበትም› አልኩት፡፡ ‹ኬዙን የምታውቀው ከሆነ ጥሩ ነው› ብሎኝ ተለያየን፡፡ እኔም አቶ ገብረዋህድ ማስረጃ አልተገኘም ስላለኝ ኬዙን አልተከታተልኩትም፤ የት እንደደረሰም አላውቅም››
ማለቱን የምርመራ መዝገቡ ላይ ተጠቅሷል (በነገራችን ላይ በዚሁ ርዕሰ-ጉዳይ በሚያጠነጥነው ክፍል አንዱ ጽሑፍ ላይ፣ አቶ ኮነ ምህረቱ ከእስር የተለቀቁት ‹‹መረጃ ስለሰጡ ነው›› በሚል የጠቀስኩት የአቶ መላኩ ቃል በምርምራ መዝገቡ ላይ ቢኖርም፤ አቶ ኮነ ነፃ የወጡት በፍርድ ቤት እንደሆነ ከሌላ ሰነድ ላይ ተመልክቻለሁ)
እንግዲህ እነዚህ የመረጃ ምስክሮች ሁለት ታላላቅ እውነቶችን ያስረግጡልናል ብዬ አስባለሁ፡፡ የመጀመሪያው ሙስና በዚህች ሀገር እጅግ ጠልቆ ሥር መስደዱንና ሥርዓቱ ራሱ እጁን ከቶ የሚያቦካበት ተጨባጭ እውነታ መሆኑን አምነን እንድንቀበል መገደዳችን ጋር ይያያዛል፡፡ ምክንያቱም የጌታነህ ዮሐንስ ቤተሰቦች የድርጅቱ ህጋዊ ማህተም በታተመበት ደብዳቤ ላይ በአራጣ ብድር ከነበራቸው ዕዳ 10 ሚሊዮን ብር ውስጥ ግማሹን ለአቶ ከተማ ድርጅት መክፈላቸው እና ለቀሪው 5 ሚሊዮን ብር ደግሞ የጌታነህ ትሬዲንግ ንብረት በሀራጅ እንዲሸጥ መወሰኑን መግለፃቸው፤ እንዲሁም እንደ አቶ በረከት ስምኦን ያለ ወሳኝ ባለሥልጣን ስለጉዳዩ መስማቱን በቀጥታ ለአቶ መላኩ መናገሩ ነው፡፡ መቼም በረከት ‹‹መረጃ አገኘሁ›› የሚለው ከአልፎ ሂያጅ መንገደኛ አለመሆኑን መገመት አይሳነንም፡፡ ይህ ከሆነ ደግሞ፣ በ2001 ዓ.ም ማስረጃ የቀረበበትን ተጠርጣሪ ከአራት ዓመት በኋላ ያንኑ ክስ እና ማስረጃ በመቁጠር ወደ ፍርድ ቤት ሊወስድ የሚችልበት ያልተሰማ ተአምር የሚኖር አይመስለኝም፡፡ ምን አልባት የዚህ ምስጢር በሁለተኛነት ከምጠቅሰው ጭብጥ ጋር ሊተሳሰር ይችላል፤ ይኸውም ሥርዓቱ የራሱን ሰዎች በ‹‹ሙስና›› ወደ እስር ቤት የሚወረውረው ሙስናን ለመዋጋት ባለው ተነሳሽነት ሳይሆን፣ ከአቶ መለስ ህልፈት በኋላ የተፈጠረበትን የውስጠ-ፓርቲ ክፍፍል ለማብረድ ‹እንደ አጀንዳ ይጠቅመኛል› ብሎ ሊሆን የሚችልበት ገፊ-ምክንያት መታየቱ ነው፡፡ በተለይም የህወሓት አመራር አባላት ‹‹የመቀሌው›› እና ‹‹የአዲስ አበባው›› በሚል በወቅቱ መከፈላቸው፤ እንዲሁም ብአዴን ከመቀሌው ቡድን ጎን መቆሙ እና ለእስር የተዳረጉት ባለሥልጣናትም በዚሁ መስመር የተሰለፉ መሆናቸው ከሹክሹክታ ያለፈ እንደነበረ ይታወሳል፡፡ እንዲሁም ሁሉም ተከሳሾቹ የተጠየቁበት ወንጀል በአቶ መለስ ዘመን ተፈፅሞ፣ የተከሰሱት ግን ከሞቱ በኋላ መሆኑ ጉዳዩን ሙስናን ከመታገል ለይተን እንድንመለከተው ያስገድደናል፡፡
እዚህ ደርሰናል¡
ይህ ስርዓት ከቀደሙት ያፈነገጠበት አንዱ መለዮው፣ የጥቅመኝነት ሰንሰለቱን ተቋማዊ ቅርፅ መስጠቱ ነው፡፡ ከስልጣን ፒራሚዱ አናት ላይ የተቆናጠጡት ገዢዎች፣ በጥቅም የሚደልሏቸውን ከስራቸው እየሰበሰቡ በ‹‹እከክልኝ…›› ጥብቅ ዝምድና ውስጥ ይጋመዱና፣ ግንባሩ ቢነካ የእነርሱም ህልውና እንደሚናጋ በማመን አንዳች ክፉ ነገር እንዳይደርስበት የተቻላቸውን ሁሉ ያደርጋሉ፡፡ ዳሩ ግን፣ የሀገሪቷ ብሄራዊ ኬክ በእጅጉ አነስተኛ ነውና፤ አንደኛው የበለጠ ድርሻ ሲሻ፤ ከሌላኛው ጥቅመኛ ጋር መናረቱ እውነት ሆኗል፡፡ በመንግስታዊው ሙስናም እያየን ያለነው ይኸው ነው፡፡ አሁን በእስር ላይ ያሉት የቀድሞ ባለስልጣናትም ሆኑ፤ በድሆች ጉሮሮ ላይ የቆሙት አራጣ አበዳሪ እና ‹‹ልማታዊ ባለሀብቶች››፣ እነርሱን ከሚበልጡ ጥቅመኞች ጋር የገጠማቸው ግድድር ለወህኒ እንዳበቃቸው መጥቀስ አንደኛው የመከራከሪያ ጫፍ ነው፡፡ ሙሉ ለሙሉ በሙስና በተዘፈቀ መንግስት ውስጥ፣ ማንም ማንንም በሙሰኝነት ሊከስስ የሚችልበት የሕግ መሰረት አለመኖሩ ግልፅ ነው፡፡ ይሁንና ቻርለስ ዳርዊን ‹‹ጉልበታሞቹ ደካሞቹን እየዋጡ ይቀጥላሉ›› እንዲል፤ ምንም ያህል አምባገነን እና ጨቋኝ ስብስብ ቢሆንም ራሱን በራሱ ከመበላት ለማዳን ‹‹የእርምት እንቅስቃሴ›› ማድረግ አለበትና፤ ጥቂት ሙሰኞችን ሰብስቦ እስር ቤት ቢከት እልል በቅምጤ አያስብልም፡፡
ሌላኛው ነገሩን ሊያብራራልን የሚችለው ጉዳይ፣ የሙስና ክስ እና የፖለቲካ ኃይል አሰላለፍ ለዚህ መሰሉ ሰበብ ምክንያት ሊሆን ይችላል ያልነው ነው፡፡ ከዚህ ቀደም በርዕስ-ጉዳይ ዋነኛ ማጠንጠኛ ባደረኳቸው ጽሑፎቼ በሙስና ተከሰው ዘብጥያ የወረዱት ባለስልጣናት፣ በውስጠ-ኢህአዴግ ለተፈጠረው የስልጣን ትንቅንቅ ማብረጃ የተመረጡ መሆናቸውን በአመክንዮ አስደግፌ ለማስረዳት መሞከሬ አይዘነጋም፡፡ መቼም መላኩ ፈንቴም ሆነ ገብረዋህድ፣ የኢኮኖሚው እንቅስቃሴ በነፃነት እንዳይጎለብት ከማድረግ አልፈው፣ የህወሓት የንግድ ተቋማት የሀገሪቱን ሁለንተና እንዲቆጣጠሩ ከፍ-ዝቅ እያሉ ሲለፉ መቆየታቸውን በማስታወስ፣ ዛሬ ስለገጠማቸው መንከራተት ሀዘኔታ ሊኖረን የሚገባ አይመስለኝም፡፡ ይህ ጉዳይ አሉባልታ ሳይሆን በተጨባጭ ማስረጃ የተደገፈ መሆኑን ለማስረዳት ሁለት ሰነዶችን ልጥቀስ፡፡ የመጀመሪያው ራሱ የፀረ-ሙስና ኮሚሽን መርማሪዎች አቶ መላኩንም ሆነ አቶ ገብረዋህድን ከመረመሩበት መዝገብ ላይ የተገኘ ነው፡-
‹‹1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች (መላኩና ገብረዋህድ) በተለያየ ጊዜ ለ5ኛ ተከሳሽ (እሸቱ ግራፍ ይባላል፤ በገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን አቃቂ ቅርንጫፍ የሕግ ማስከበር ኃላፊ እና በሚሌ ቅርንጫፍ ሥራ-አስኪያጅ የነበረ) ትዕዛዝ በማስተላለፍ ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 2005 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ የትራንዚት ፍቃድ ተሰጥቷቸው በጅቡቲ በኩል ከውጪ አገር ወደ አገር ውስጥ ገብተው ሚሌ የመቆጣጠሪያ ጣቢያ ከሚደርሱት መኪኖች (ዕቃዎች) ውስጥ፡- መቴክ፣ መስፍን ኢንዱስትሪያል ኢኒጅነሪንግ፣ ሜድሮክ፣ ኒያላ ሞተርስ የመኪና መገጣጠሚያና መለዋወጫ ዕቃ አስመጪ፣ ሳሊኒ ኮንስትራክሽን እና ሌሎች ድርጅቶች የሚያስመጡትን ዕቃዎች በ5ኛ ተከሳሽ አማካኝነት ተመርጠው ሳይፈተሹ፣ ‹ተፈትሸዋል› የሚል ማረጋገጫ እየተሰጣቸው ወደ አገር ውስጥ እንዲገቡ በማስደረጋቸው›› ይላል፡፡
ሁለተኛው ሰነድ ደግሞ ሐምሌ 24 ቀን 2005 ዓ.ም ገቢዎችና ጉምሩክ ለፀረ-ሙስና የላከው ደብዳቤ ሲሆን፤ እንደሚከተለው እንቀንጭብለት፡-

ኢትዮጵያ ከሰሜን ኮሪያ በምስጢር መሳሪያ መግዛቱዋ ተሰማ

የህብር ሬዲዮ ሚያዚያ 12  ቀን 2006 ፕሮግራም
<<…ኢትዮጵያውያን የፋሲካን በዓል በውጭ አገር ስናከብር በአገር ቤት በዓሉን በደስታ ለማሳለፍ ያልቻሉ ኑሮው የከበዳቸው እንዳሉ መርሳት የለብንም…>>
ብዑዕ አቡነ ዮሴፍ የኔቫዳ፣የአሪዞናና ዩታ አገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ለህብር ሬዲዮ ከሰጡት ማብራሪያ (ሙሉውን ያዳምጡ)
ላሊበላ በውጭ ጎብኒ እይታ  
ኦቲዝም ምንድነው? እውን ልጆቻችንን አውቀን በጊዜ ተገቢውን ቴራፒ እንዲወስዱ እናደርጋለን?
በኦቲዝም ውስጥ ያሉ ልጆች ያሏቸው ልጆች ወላጆች ምን ይላሉ?
ሰናይት አድማሱ የስነ ልቦና ባለሙያ እና  
ወ/ሮ ፌበን ፋንቱ ወላጅ ከሎስ አንጀለስ ማብራሪያ ሰጥተውናል (ክፍል ሁለት ሙሉውን ያዳምጡ)
 የጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ ማስታወሻ ከሳውዲ እስር ቤት  
ሌሎችም ዝግጅቶች http://soundcloud.com/hiber-radio-las-vegas-1/hiber-radio-042014-042714
posted by Aseged Tamene

Thursday, April 17, 2014

ሚሊዮኖች ድምጽ - የእሪታ ቀን ሰልፍ በሚያዚያ 26 ቀን እንደሚደረግ የአዲስ አበባ አስተዳደሩ እውቅና ሰጠ !

ሚሊዮኖች ድምጽ - የእሪታ ቀን ሰልፍ በሚያዚያ 26 ቀን እንደሚደረግ የአዲስ አበባ አስተዳደሩ እውቅና ሰጠ !

ሰማያዊ ፓርቲ ገዢው ፓርቲ በዋና ዋና አገልግሎቶች አሰጣጥ ላይ የፖሊሲ ማሻሻያ እንዲያደርግ ጠየቀ

በጃንሜዳ ሰላማዊ ሠልፍ እንደሚያደርግ አስታወቀመንግሥት በዋና ዋና አገልግሎቶች አሰጣጥ ላይ የፖሊሲ ማሻሻያ እንዲያደርግ ሰማያዊ ፓርቲ ጠየቀ
መንግሥት የከተማ ነዋሪዎች ዋና ችግር በሆኑባቸው የኤሌክትሪክ፣ የውኃ፣ የትራንስፖርትና የቴሌኮም አገልግሎቶች ላይ የፖሊሲ ማሻሻያ በማድረግ ነዋሪዎችን ሊታደግ እንደሚገባ ሰማያዊ ፓርቲ ጥያቄ አቀረበ፡፡
መንግሥት በተለይ በከተማ የሚኖረውን ሕዝብ የሚመጥን ፖሊሲ ባለመንደፉ ዝርክርክ የሆነ የአፈጻጸም ችግር መታየት ከጀመረ ዓመታት እየተቆጠሩ መሆኑን በመግለጽ፣ በአሁኑ ጊዜ ከላይ በተጠቀሱት የአገልግሎት ዘርፎች ያለው ችግር እየተባባሰ በመምጣቱ በአፋጣኝ ሊስተካከል እንደሚገባ፣ የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ ይልቃል ጌትነት ሚያዝያ 7 ቀን 2006 ዓ.ም. በጽሕፈት ቤታቸው በሰጡት መግለጫ ላይ አስታውቀዋል፡፡
የግል ሴክተሩ እንዳይሳተፍ ሁሉንም ነገር በሞኖፖል በመያዝ ችግሮች እንዲባበሱ እንጂ አበረታችና አስደሳች ሥራ በገዢው መንግሥት ኢሕአዴግ ሲሠራ እንደማይስተዋል የተናገሩት አቶ ይልቃል፣ የችግሮቹ ምክንያት ኢሕአዴግ የሚከተለው የተሳሳተ ፖሊሲ እንጂ፣ የአገልግሎት ሴክተሮቹ በራሳቸው ችግር አለመሆናቸውን አስረድተዋል፡፡ መንግሥት ማንም ሳይጠቁመውና ሳይነግረው ችግሩ ዓይን አፍጥጦ የወጣ መሆኑን እየተመለከተው እንደሚገኝ የገለጹት አቶ ይልቃል፣ ፖሊሲውን አስተካክሎ የሕዝብን ችግርና ብሶት መፍታት ካልቻለ የሕዝብ ሥልጣንን ማስረከብ እንዳለበትም ገልጸዋል፡፡
በየአምስት ዓመቱ አገራዊ ምርጫ ተደርጎ አመራሩ የሚቀየር ወይም የሚፀድቅ ቢሆንም፣ በአምስት ዓመት ውስጥ የማስፈጸምና የመልካም አስተዳደር ችግሮች በሚገጥሙት ጊዜ፣ ሕዝቡ ሰላማዊ ሠልፍ የማድረግ መብት ስላለው መብቱን በሰላማዊ ሠልፍ የማስጠበቅ ግዴታ ውስጥ እንደሚገባ መንግሥት ማወቅ እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡
በተለይ ከተወሰኑ ወራት ጀምሮ ውኃ፣ ኤሌክትሪክ፣ ኢንተርኔት፣ ስልክና ሌሎችም አገልግሎቶች መቆማቸውን የገለጹት አቶ ይልቃል፣ ‹‹በአጠቃላይ አገር ቆሟል ማለት ይቻላል፤›› ብለዋል፡፡ ሁኔታው ሥር የሰደደና የመኖርና ያለመኖር የህልውና ጥያቄ በመሆኑ፣ መንግሥት ባስቸኳይ ምላሽ መስጠት እንዳለበትም አክለዋል፡፡ ሌላው አቶ ይልቃል ያነሱት ነጥብ የዜጐችን መፈናቀል በሚመለከት ሲሆን፣ ዜጐች ከአገራቸው ወይም ከሚኖሩበት ቀዬ በ24 ሰዓታት ውስጥ ለቀው እንዲወጡ መደረጉን ፓርቲያቸው እንደሚያወግዘው ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ የሥልጣን ባለቤት ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች እንጂ ዜጐች ባለመሆናቸው፣ በአንድ ክልል ውስጥ የሚኖር የሌላ ብሔር ተወላጅ በሌላ አገር እንደሚኖር ሰው በአስቸኳይ እንዲለቅ እንደሚደረግ፣ በሕገ መንግሥቱ ተዘዋውሮ ሀብት ማፍራት የተሰጠው መብት እንደማይከበርለትና እንደሚባረር አቶ ይልቃል አስረድተዋል፡፡ ይህንን ደግሞ ኢሕአዴግ የወደደው ስለሆነ የማፈናቀሉ ተግባር እየቀጠለ መሆኑንና ሰሞኑንም ተግባራዊ እየሆነ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡ ምናልባት ማፈናቀል የሚቆመውና የዜጐች መብት መከበር የሚጀምረው ኢሕአዴግ ሥልጣን ሲለቅ ሊሆን እንደሚችል አክለዋል፡፡
በሕገ መንግሥቱ ይቻላል የሚባለው የመብት ጥያቄና ተግባራዊነት እውነት ቢሆን ኖሮ እስካሁን ተግባራዊ ሆኖ ታይቶ ምስክር ሊሆን ይችል እንደነበርም ጠቁመዋል፡፡ የቀድሞዎቹ መንግሥታት ጭቆናን እንጂ ማፈናቀልን አድርገውት እንደማያውቁ የተናገሩት ሊቀመንበሩ፣ መሬትና አገር የሁሉም ኢትዮጵያዊ ዜጋ እንጂ የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ባለመሆኑ ሕገ መንግሥቱ ሊከበር እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ የሚያስበው በቁጭትና በእልህ ሳይሆን እንደ ፓርቲ ማድረግ ያለበትን የመፈጸም ግዴታ ስላለበት መሆኑን አውስተዋል፡፡ ፓርቲው ሕዝቡ መፍትሔ እስከሚያገኝ ከጎኑ ሆኖ እንደሚሠራ፣ የማይሠራ ከሆነ ግን መጥፋት እንዳለበትም እምነቱ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
በመሆኑም ፓርቲው በሕዝቡ ላይ እየደረሰ ያለውን አገልግሎት የማጣት ችግር መፍትሔ ለማስገኘት በተደጋጋሚ ያቀረባቸው ጥያቄዎችን በሚመለከት ለመንግሥት ለማሳወቅ፣ ሚያዝያ 19 ቀን 2006 ዓ.ም. ከቢሮው እንደራሴ ሠፈር እስከ ጃንሜዳ ከጠዋቱ አራት ሰዓት እስከ ስምንት ሰዓት የተቃውሞ ሰላማዊ ሠልፍ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል፡፡
posted by Aseged Tamene

Friday, April 4, 2014

የኦሮሞ ሊቃውንት በጎጃም

ከጎጃም ታላላቅ ሊቃውንት ውስጥ የኦሮሞ ተወላጅ የሆኑት ሁነኛ ደረጃ ይዘው ይገኛሉ፡፡ የኦሮሞ ሊቃውንት በየትኛውም የጎጃም አድባራትና ገዳማት ለትውልድ የሚተላለፉ ታላላቅ ሥራዎችን ሠርተው አልፈዋል፡፡ በአሁኑ ሰዓትም በየገዳማቱና አድባራቱ በመምህርነት የሚያገለግሉ የኦሮሞ ሊቃውንት በጎጃም ሞልተዋል፡፡
ታዋቂ ከሆኑት ሊቃውንት ውስጥ አለቃ ተክለ ኢየሱስ ዋቅጅራ፣ ታላቁ ሊቅ መምህር ገብረ ሥላሴ ክንፉ ዘደብረ ኤልያስ፣ ታላቁ ምሁር መልአከ ብርሃን ፋንታ ገብርየ (በጥናት የሚረጋገጥ) ታዋቂው የቅኔ መምህር ሀብተ ኢየሱስ ጋረደው ዘመርጡ ለማርያም (በአሁኑ ጊዜ በሕይወት የሚገኙ)፣ መምህር ወልደ ሚካኤል (በአሁኑ ጊዜ የደብረ ገነት ኤልያስ የአቋቋም መምህር)፣ መሪጌታ ወልዴ ዘሆሮጉድሩ የጫቢ ማርያም የቅኔ መምህር እና ሌሎች ተጠቃሾች ናቸው፡፡

Thursday, April 3, 2014

“ለነሱ (ለማ/ቅዱሳን) የተሰጠው ስም ለእኔም ይገባኛል”

ለነሱ (ለማ/ቅዱሳን) የተሰጠው ስም ለእኔም ይገባኛል”(ክቡር አቶ ግርማ ሰይፉ፤ የፓርላማ አባል)ክቡር ሆይአኔ የአንድ እምነት አንድ ሀገር አራማጅ ነኝ መንግሥትበማኅበረ ቅዱሳን ላይ
ዘመቻ ጀመረ በሚል እሰጥ አገባእንደበዛ አውቃለሁ፡፡ በሌለኝ መረጃ የእኔን ስም እየጠቀሱሰዎች
ፖስት እንደሚያደርጉ ከሰዎች ብሰማም የእኔ ፌስቡክ ይህን አልገለፀልኝም፡፡ ለማንኛውም
መንግሥትበእምነት ላይ ዘመቻ ሲጀምር በኦርቶዶክስ ላይ በማኅበረ ቅዱሳን መስመር እንደነበር
ትዝ ይለኛል፡፡ሟቹ ጠቅላይ ሚኒሰትር አቶ መለስ ይህን አሰመልክተው ለሰጡት አሰተያየት
የሰጠሁትን ምላሽበድጋሚ ላጋራችሁ፡፡ ይህ ነው የእኔ አቋም፡፡ ይህ ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር ከገጠመ
እሰየው ነው፡፡ ለነሱየተሰጠው ስም ለእኔም ይገባኛል፡፡ የሰጠሁት ምላሽ እንደወረደ ይህን ይመስል
ነበር፡፡ብዙ ጉዳዮች እንደተርጓሚው እንደሚሆን መገመት ይቻላል። ነገር ግን “አንድ እምነት
አንድ ሀገር”ማለት ግን ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እንደተረጎሙት ሳይሆን፤
አንድ ሰው ሊኖረውየሚገባው አንድ እምነት ብቻ ነው (ሰኞ፤ ዕሮብና አርብ ሙስሊም ማክሰኞ፤
ሀሙስና ቅዳሜክርስቲያን፤ ወዘተ መሆን አይቻልም)። ይህ ደግሞ አምላካዊ ቃል ነው።
(እኔ ቀናተኛ አምላክ ነኝ ሲል)ይህ አምላካዊ ቃል ደግም የሚሰራው ለሚያምኑበት ነው፡፡
ቃልቻ ቤት እየሄዳችሁ ቤተ ክርስቲያንአትምጡ ማለት ነው፡፡ ሊኖረን የሚገባው አንድ እምነት ነው፡፡
በእርግጠኝነት ሙስሊም ሆኖምክርስቲያን መሆን አይቻልም። ስለዚህ ይህ ለአንድ እምነት የመገዛት
ፍልስፍና የሁሉም የእምነት ዘርፎችመለያ ነው፡፡ ጥንቆላ ብቻ ነው ይህንን የሚፈቅደው።
ይህ ደግም በሁሉም እምነቶች የተወገዘ የመጥፎመንፈስ ሥራ ነው፡፡ ስለዚህ እኔ ያለኝ አንድ እምነት ብቻ ነው፡፡
መፍክሬም ይኸው ነው፡፡
ከአንድ እምነት ጋር ተያይዛ የመጣችው የአንድ ሀገር ጉዳይ ነው፡፡ ይህ በእርግጥ አከራካሪ ነው፡፡
አንድአንድ ሀገሮች ጥምር ዜግነትን የሚፈቅዱ አሉ። ይህም ሆኖ እኔ በግሌ ኢትዮጵያ ከምትባል
ሀገርበሰተቀር ሌላ ሀገር የለኝም- እንዲኖረኝም አልፈልግም። ይህን አቋሜን ስገልፅ ግን እኔ
ኢትዮጵያዊ ነኝስል “ሌሎች ኢትዮጵያዊ አይደላችሁም አለ” ተብሎ ልከሰስ አይገባም፡፡
አንድ የእስልምና እምነትተከታይ ኢትዮጵያዊ ሊሆን እንደሚችል ብዥታ ኖሮብኝ
አያውቅም ወይም የሌላ ክርስትና እምነትተከታዮች ኢትዮጵያዊ እንደሆኑ አልጠራጠርም፡፡
ኢ-አማኒያንም ቢሆኑ፡፡
አንድ ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር አለችኝ ብዬ ነው ለዚህች ሀገር እድገት
(ሁሉ አቀፍ እድገት ማለቴ ነው)የሚከፈል መሰዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ የሆኑኩት፡፡
ሌላ አማራጭ የለኝም - አማራጭ ያለው ግንካልተመቸው ወደዛኛው ሊሄድ ይችላል፡፡
ሁለት ጉርጓድ ያላት አይጥ እንደሚባለው፡፡ እኔ ግን ሀገሬአንድ እና አንድ ነች፡፡ ኢትዮጵያ፡፡
ይህ ማለት ግን በምንም መመዘኛ ይህች ሀገር የኔ ብቻ ነች ማለትአይቻልም፡፡ አይሆንምም፡፡
እኔ የአንድ እምነት እና አንድ ሀገር ባለቤት ነኝ፡፡
ምንጭ፦ የፌስቡክ ገጻቸው።
posted by Aseged Tamene