Friday, May 30, 2014
Thursday, May 29, 2014
Wednesday, May 28, 2014
40 – 23 የኢህአዴግ የጎሳና የመጥበብ ሰረገላ ሐዲዱ ላይ ነውን?
“ኢትዮጵያን በጎሳ ሳጥን ቆልፎ የሚጓዘው ህወሃትና ድግሱ”
ህወሃት
በነጻ አውጪ ስም ታግሎ ኢትዮጵያን መግዛት የጀመረበትን 23ኛ ዓመት በዓሉን እያከበረ ነው። ወዳጆቹና መሪዎቹ
ባስቀመጡት እቅድ መሰረት ኢትዮጵያን “በመተካካትና በተሃድሶ” ስም ራሱን እያገላበጠ ለመግዛት የቆረጠው ጊዜ በትንሹ
40 ዓመታት እንደሆነ ይታወቃል። አሁን ባለው የሰረገላው ጉዞ ኢህአዴግ ከ40 – 23 ከመቀነሱ ውጪ አሰበበት
ስለመድረሱ መገመት የሚያስችል ምልክት የለም። እንደውም ስጋት እንጂ።
ሲጀመር “የገበሬ ተሟጋች” ነኝ በማለት ራሱን የአርሶ አደሩ
ወኪል አድርጎ የተነሳው ህወሃት፣ ኢህአዴግ ሆኖ አገር መግዛት ሲጀምር ያስቀደመው የብሄር ብሄረሰቦችን የመብት ጥያቄ
እንደ ውዳሴ ጸሎት በመደጋገም ነበር። በዚሁ በጎሳ ላይ ተመስርቶ በቋንቋ የተቆለፈው የአገዛዝ ስልት ሲጀመር
ማስጠንቀቂያ የሰጡ፣ ለመታገል የሞከሩ፣ የታገሉ፣ ያስተባበሩ፣ ያደራጁ የህወሃት የ40 ዓመት ጉዞ ጸር ተደርገው
ተወሰዱ። ስለ ኢትዮጵያ ጥቅምና ኢትዮጵያዊነት ያሳሰቡ ጠላት ተደርገው ተፈረጁ። በስውር በአፈና፣ በግልጽ ህግ
እየተጠቀሰባቸው ከጫወታና ከመኖር ተገለሉ። ብዙዎች እንደሚሉት “የጉዳቱን መጠን ህወሃትና የተጎዱት ቤተሰቦች
ይቁጠሩት”!
ግንቦት ሃያ “የህዝብ የድል ክቡር ቀን ነው” በሚሉና “የህዝብና
የአገር ውድቀት የታወጀበት የክፉ ቀኖች ሁሉ ድምር” ሲሉ በሚሰይሙት መካከል ሰፊ መከራከሪያ አለ። የመንገድ
ግንባታ፣ የህንጻ ግንባታ፣ የኮሌጅና የትምህርት ቤቶች ግንባታ፣ የግድቦች ግንባታና የአባይ ወንዝ ልማት ወዘተ
ጉዳዮች የግንቦት 20 ጣፋጭ ፍሬዎች ስለመሆናቸው “የቀኑ ወዳጆች” ይከራከራሉ። የቀኑ “ባሮችም” ይህንኑ ውዳሴ
በማቀንቀን ታማኝነታቸውን ይገልጻሉ። በጥቅም የተደለሉ ሎሌዎች ስለሆኑ ይህንን ድል ለማስጠበቅ በግልጽና በህቡዕ
አድርጉ የተባሉትን ያደርጋሉ።
በተጠቀሱት የልማት ስራዎች ላይ ተቃውሞ የማያነሱ የቀኑ
“ሰለባዎች” ሰላምና መረጋጋት እንዳለ የሚሰብክ አስተዳደር ልማትን ከመስራት ሌላ ተግባር እንደሌለው ይገልጻሉ።
አያይዘውም ጣሊያንም በ5 ዓመት ጊዜ ውስጥ በርካታ መንገድና ድልድዮችን መገንባቱን ያጣቅሳሉ። ከሁሉም በላይ ግን
ኢህአዴግ በሚገዛት አገርና ሕዝብ ስም የተበደረውን የገንዘብ መጠን “ከተዘረፈው ውጪ” በማለት ከፍተኛ እንደሆነ
ይናገራሉ። በሌላ በኩል ደግሞ “መንገድ መስራትና ህንጻ ማቆም የመብት ጥያቄን በጥይት ለመመለስና በደም ለመጨማለቅ
ዋስትና ሊሆን አይችልም” በማለት ስርዓቱን አጥብቀው ይኮንኑታል።
በሌላም ወገን የተሰሩትን ህንጻዎች፣ የንግድ ተቋማት፣ የገንዘብ
ተቋማት፣ ከፍተኛ ኢንቨስትመንቶች በማንሳት “የግንቦት 20 ፍሬዎች” ሲሉ ይሰይሟቸዋል። ሲያብራሩም “የነዚህ ሁሉ
ሃብቶች መነሻና ባለቤቶች ህወሃትና ህወሃት ዙሪያ የሚሽከረከሩ ባለሟሎች ናቸው። የህዝብ አይደሉም። ሕዝብም
አያምንባቸውም” በማለት ጥርስ ይነክሱባቸዋል። በዝርፊያ ሃብት የሚያግበሰብሰውን ኤፈርት ኢትዮጵያን “ንብረቶችሽን
ባደራ ላስቀምጥ” የሚል እስከሚመስል የንግድ ኢምፓየሩን ማስፋቱን አብዝተው ይኮንናሉ።
Tuesday, May 27, 2014
በኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ላይ የሚፈፀመው ኢሰብአዊ ወንጀል
May 27, 2014
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
እ.ኤ.አ ሜይ 2/2014 ቢቢሲ/BBC እንደዘገበው በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ እንደመዥገር ተጣብቆ የሚገኘው ገዥ አካል የጸጥታ ኃይሎች ከመናገሻ ከተማዋ ከአዲስ አበባ በስተምዕራብ በኩል በ80 ማይሎች ርቀት ላይ በምትገኘው የአምቦ ከተማ ላይ ቢያንስ 47 የዩኒቨርስቲ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎችን በአሰቃቂ ሁኔታ በጥይት ኢሰብአዊ በሆነ መንገድ ረሽነዋል፡፡ ስብዕናው በውሸት እና በሀሰት ውንጀላ የበከተው ገዥ አካል ይህንን እልቂት እንደተለመደው ሽምጥጥ አድርጎ በመካድ “ጥቂት ጸረ ሰላም ኃይሎች በቆሰቆሱት እና በአስተባበሩት አመጽ“ ምክንያት የሚል የሀሰት ፍረጃ በመስጠት በግፍ የተገደሉትን ወገኖቻችንን ቁጥር ለማሳነስ ጥረት አድርጓል፡፡ ይህ በወጣት ተማሪዎች እና ህጻናት ላይ የተፈጸመው የማንአለብኝነት የእብደት አሰቃቂ እልቂት በዓለም አቀፍ የዜና አውታሮች ዘንድ ሰፊ ሽፋን አልተሰጠውም፡፡
ሂዩማን ራይትስ ዎች/HRW የተባለው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት “በአምቦ፣ በነቀምት፣ በጅማ እና በሌሎች ከተሞች በሰላማዊ መንገድ ተቃውሟቸውን ባሰሙት ንጹሀን ዜጎች ላይ እየተፈጸመ ያለው ግድያ እና ድብደባ ይቁም“ የሚል መግለጫ በማውጣት እኩይ ድርጊቱን አውግዟል፡፡ እንደ ሂዩማን ራይትስ ዎች ዘገባ “በኦሮሚያ የሚገኙ ከ15 በላይ የሚሆኑ ህብረተሰብ አቀፍ ገጠራማ እና ከተማ ቀመስ አካባቢዎችን ወደ አዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት የወሰን ክልል የሚያካትተው እና የኦሮሞ አርሶ አደሮችን እንዲሁም ሌሎች ኗሪዎችን የሚያፈናቅለው የአዲስ አበባ የተቀናጀ መሪ የልማት ዕቅድ ሀሳብ ተዘጋጅቶ ይፋ መሆኑን ተከትሎ የተማሪዎች የተቃውሞ አመጽ ገነፈለ“ ብሏል፡፡ በማስከተልም ሂዩማን ራይትስ ዎች በሰላማዊ መንገድ ተቃውሟቸውን ባሰሙት ተማሪዎች ላይ የገዥው አካል የጸጥታ ኃይሎች እየወሰዱ ያሉትን የኃይል እርምጃ በአስቸኳይ እንዲያቆሙ ጠይቋል፡፡
በዚህ መረን በለቀቀ ዕኩይ ድርጊት የተሰማኝን ሀዘን በቃላት ለመግለጽ ተስኖኛል ምክንያቱም ልብን ሰብሮ የሚገባው ይህ የአሰቃቂ እልቂት ሀዘን ልሸከመው ከምችለው ከአቅሜ በላይ ሆኖብኛልና፡፡ የብሩህ አዕምሮ ባለቤት እና የነገይቱ ኢትዮጵያ ተረካቢ የሆኑት እምቦቀቅላ ተማሪዎች ገና በወጣትነት ለጋ እድሚያቸው ኃላፊነት በማይሰማው መንግስት ነኝ ባይ የወሮበላ ቡድን ስብስብ በጥይት ውርጅብኝ በመጨፍጨፋቸው ታላቅ ሀዘን ተሰምቶኛል፣ እንዲሁም ቀጣይነት ባለው መልኩ ስሜቴን እየቆጠቆጠኝ ይገኛል፡፡ ተማሪዎቹ የሚሰማቸውን ቅሬታ በሰላማዊ መንገድ ለማቅረብ ህገመንግስታዊ ያልተገደበ መብት ነበራቸው፡፡ ያንን መብት በመጠቀም በሰላማዊ መንገድ ወደ አደባባይ በመውጣት ተቃውሟቸውን በማሰማታቸው ምክንያት ብቻ የጥይት በረዶ ተርከፍክፎባቸዋል፡፡ እናም ሁላችንም ልናዝንላቸው ይገባል፡፡ ኃላፊነት በጎደለው ገዥ አካል በተፈጸመው እልቂት ምክንያት የምርጥ እና የባለብሩህ አእምሮ ባለቤት የነበሩትን ወጣቶች ኢትዮጵያ በማጣቷ አጅግ በጣም ለኢትዮጵያ አዝናለሁ፡፡ የእልቂቱ ሰለባ ለሆኑት ወጣቶች ወላጆች እና ጓደኞች የተሰማኝን ጥልቅ ሀዘን መግለጽ እፈልጋለሁ፡፡ መጽናናትን እንዲሰጣቸውም ለኃያሉ አምላክ ጸሎቴን አደርሳለሁ፡፡
በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸምን እልቂት አጥብቄ አወግዛሉ፡፡ እ.ኤ.አ የሜይ 2005 የኢትዮጵያን ድህረ ምርጫ ውዝግብ ተከትሎ ምንም ትጥቅ ሳይኖራቸው በሰላማዊ መንገድ ብቻ ተቃውሟቸውን በአደባባይ ለመግለጽ በወጡ ንጹሀን ዜጎች ላይ በተፈጸመው ኃላፊነት የጎደለው እልቂት ምክንያት በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ የሰብአዊ መብት ተሟጋች እንድሆን ተገድጃለሁ፡፡ ከዚያን ጊዜ በፊት በኢትዮጵያ የፖለቲካ ህይወት ውስጥ ምንም ዓይነት ተሳትፎ አልነበረኝም፡፡ መለስ ዜናዊ የሚለውን ስም “እገሌ ወይስ እገሌ” ከሚባል ሰው ለየቼ አላውቀዉም ነበር፡፡ ከድህረ ምርጫው ውዝግብ ጋር በተያያዘ መልኩ ተቃውሟቸውን ለመግለጽ ወደ አደባባይ በወጡ ያልታጠቁ ሰላማዊ ንጹሀን ዜጎች ላይ በሟቹ በአቶ መለስ ዜናዊ ቁጥጥር እና ልዩ ትዕዛዝ ከአንድ አካባቢ ተሰባስበው በመጡ አግዓዚ እየተባሉ በሚጠሩ ደም የጠማቸው ቅጥረኛ ነፍሰ ገዳዮች አነጣጥሮ ተኳሽነት 200 የሚሆኑ ወገኖቻችን ሲገደሉ 800 (ትክክለኛው ቁጥር ከዚህ በላይ እንደሚሆን በማስረጃ ተረጋግጧል) የሚሆኑት ደግሞ የከባድ እና ቀላል ቁስለኛ ሰለባ እንዲሆኑ ተደርገዋል፡፡ በዚያ እኩይ ምግባር እንደ ሰማሁ አሳብዶኝ ነበር፡፡ መለስ እና በወንጀል የተዘፈቁት ግብረ አበሮቹ እንደዚያ ዓይነት አሰቃቂ ወንጀል ፈጽመው ለህግ ሳይቀርቡ እና ከፍርድ አንዳያመልጡ ጥረቴን ጀመርኩ፡፡ እነሆ ላለፉት ስምንት ዓመታት በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ የሰብአዊ መብቶች እንዲከበሩ እና የዴሞክራሲ አስተሳሰቦች እንዲጎለብቱ በማሰብ ለአንድም ሳምንት ሳይስተጓጎል የሰኞ ዕለት ትችት/Monday Commentary በሚል ርዕስ በተከታታይ እያዘጋጀሁ በማሰራጨት ሰብአዊ መብቶች እንዲከበሩ በመሞገት እና የሰብአዊ መብት ትምህርቶች እንዲስፋፉ ጥረት በማድረግ ላይ እገኛለሁ፡፡
እ.ኤ.አ በሜይ 2005 በወቅቱ የገዥው አካል ቁንጮ በነበረው በአቶ መለስ ልዩ ትዕዛዝ ከሁለት መቶ በላይ ያልታጠቁ ሰላማዊ ዜጎች በግፍ ኃላፊነት በጎደለው መልኩ ሲገደሉ እንደ እብድ እንደዘለልኩት ሁሉ አሁንም በተመሳሳይ መልኩ በአምቦ እና በሌሎች አካባቢዎችም በደርዘኖች የሚቆጠሩ ያልታጠቁ ሰላማዊ የዩኒቨርስቲ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች በግፍ በዘፈቀደ እንደ ዋዛ ሲጭፈጨፉ ስሰማ እንደ እብድ በመሆን ዘልያለሁ፡፡ ይህ ድርጊት በእውነት በ21ኛው ክፍለ ዘመን ህዝቦች ሊፈጸም የማይችል እና ለመናገር የሚዘገንን አሳፋሪ እና ዕኩይ ድርጊት ነው፡፡ አሁንም እንደ እብድ ሆኘ እንድዘል የሚያደርገኝ ሌላው ነገር የዱር አራዊት መብት እንኳ ተከብሮ በዘፈቀደ በአንድ ሰው ወይም ቡድን ፍላጎት ምንክያት ብቻ በማይገደሉበት ወቅት በኢትዮጵያ ሰላማዊ ዜጎችን፣ የዩኒቨርስቲ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎችን በህዝብ ገንዘብ በሚገዛ ጥይት እና ክላስተር ቦምብ እንደ ቅጠል እያረገፉ እነዚህን በህዝብ ደም የተጨማለቁ ወንጀለኞች ለህግ ቀርበው ተጠያቂ የሚያደርግ ነባራዊ ሁኔታ ባለመፈጠሩ ማንም በተዘፈቀበት ወንጀል ተጠያቂ ሳይሆን በአዲስ አበባ እና በሌሎች መንገዶች ላይ ደረታቸውን ነፍተው እየተጎማለሉ የአገሪቱን ሀብት በብቸኝነት በመያዝ በመዝረፍ ላይ የመገኘታቸው ሁኔታ ነው፡፡
በኢትዮጵያ በህግ ተጠያቂ ያለመሆን ለረዥም ጊዜየቆየ አሳፋሪ የባህል ችግር አለ፡፡ ኮሎኔል መንግስቱ ኃ/ማርያም በህዝብ ላይ እልቂትን ፈጽመዋል ሆኖም ግን በሰራው የግፍ ወንጀል እስከ አሁኗ ደቂቃ ድረስ ተጠያቂ አልሆነም፡፡ እኒያ የብዙህን እልቂት ፈጻሚ እና አስፈጻሚ የሌባ አይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያወልቅ እንዲሉ በስልጣን ወንበራቸው ላይ በነበረበት ወቅት በሃፍረትቢስ አንደበቱ “ትንኝ እንኳ አልገደልኩም” በማለት ተሳልቆ ነበር፡፡ በተጨባጭ ግን በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ንጹሀን ዜጎችን ገድሏል፣ እንዲገደሉም አድርግዋል፡፡ ስለሆነም በእድሜው የመጨረሻዎቹ ዓመታት ዝምባብዌ በምቾት ተቀምጦ የልብ ወለድ ድርሰት እና በስልጣን ዘመኑ አድርጊያቸዋለሁ የሚ ለውን የተረት ገድሎች ትረካ በመጻፍ ላይ ይገኛል፡፡
አቶ መለስ ዜናዊ በእብሪት ተሞልቶ ንጹሀን ዜጎችን ሲገድል እና ሲያስገድል የተከበሩ ሰዎችን ሲዘልፉ እና ሲያዋርድ ቆይቶ በታላቁ አምላክ ፈቃድ ፍትህ ተበይኖበታል፡፡ በአሁኑ ጊዜ የቀሩት ደቀመዝሙሮቻቸው እና የምግባር ጓደኞቻቸው በፍትህ ላይ አፍንጫቸውን ነፍተዋል፡፡

Friday, May 23, 2014
የወያኔ ጥላቻ ፍሬ (ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም )
May 23, 2014
ወያኔ ለትግራይ ሕዝብ ሀብትንና ብልጽግናን
አመጣ ብለው የሚያምኑ ሰዎች ብዙ ናቸው፤ ወያኔ የሥልጣን ወንበሩ ላይ በመውጣቱ ትግሬዎች ሁሉ አልፎላቸዋል ተብሎ
ይታመናል፤ በተለይ በአውሮፓና በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በዚህ ላይ የጠነከረ እምነት አላቸው፤ በዚህ ጉዳይ
ላይ ከኢትዮጵያ ውጭ ብዙ ውይይትም ይሁን ንትርክ ይደረጋል፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ግን የተፈራ ርእስ ነው፤
ውስጥ-ውስጡን እንጂ አደባባይ አይወጣም፤ ይህንን ጉዳይ በኢትዮጵያ ውስጥ አደባባይ ለማውጣት ጊዜው የደረሰ
ይመስለኛል፤ አረጋዊ በርሄ፣ ገብረ መድኅን አርአያ፣ አስገደ ገብረ ሥላሴ፣ አብርሃ ደስታ (አሥር ቢሞሉልኝ ደስ
ይለኝ ነበር!) እየደጋገሙ ቢያነሡትም ሌሎች በቁም-ነገር የተቀበሉት አይመስልም፤ ሕዝቡ ግን በራሱ መንገድ
እየተናገረና ምስክርነቱን እየሰጠ ነው፤ በመቀሌ የተሠራውን የመኳንንት መንደር ሕዝቡ አፓርቴይድ ብሎ ሲሰይመው፣ በአዲስ አበባ የተሠራውን መንደር መቀሌ ብሎ ሲሰይመው እየመሰከረ ነው፤ ‹‹የለሁበትም!›› እያለ ነው።
የትግራይ ሕዝብ መደህየቱ አልበቃ ብሎት ሲለምንም እየተሳቀቀ ነው፤ የሚለምነው ትግሬ ለብዙ ሰዎች ትግሬና ወያኔ አንድ መስሎ እንደሚታየው ያውቃል፤ አብዛኛው ሰው በወያኔ ላይ ያለውን ስሜት ያውቃል፤ ስለዚህም ሲለምን ሰዎች በወያኔ ላይ ያላቸውን ስሜት ስለሚያራግፉበት እየተሸማቀቀ ነው፤ አንድ የትግራይ ቄስ ከአርሲ ነኝ አሉኝና ለምን እውነቱን አይናገሩም ስላቸው እውነቱን ስናገር የማገኘው ስድብ ብቻ ነው አሉኝ፤ እኒህ ሰው ምን በወጣቸው የወያኔን ኃጢአት ተሸካሚ ይሆናሉ፤ በሌላ በኩል ደግሞ በትግሬነቱ የተጠቀመ አለ፤ እኔ የማውቀው የደርግ ወታደር የነበረ ትግሬ ቆስሎ ከውትድርና ወጣና በአንድ የመንግሥት መሥሪያ ቤት የጥበቃ ሥራ ላይ ነበር፤ በጣም ይቸግረው ነበር፤ ሚስቱ ሕመምተኛ ነበረች፤ የቤት ኪራይ መክፈል ይቸገር ነበር፤ ዛሬ ግን የሚለብሰው ልብስ ሌላ ነው፤ ከኑሮውም ተርፎ ለሲጃራና ለጫት እያወጣ ነው፤ ወይም ሌሎች እያወጡለት ነው፤ ትግሬነታቸው ብቻ እንዲህ የደላቸው በጣም፣ በጣም ጥቂቶች ናቸው፤ ስለዚህም በወያኔ አገዛዝ ትግሬ ሁሉ ተጠቅሞአል ማለት ከጉልሁ እውነት ጋር የሚጋጭ ስሕተት ነው፤ አብርሃ ሰዎች ትግሬ ሁሉ ተጠቃሚ ሆኗል ሲሉ ‹‹ያመኛል›› ማለቱ ይገባኛል።

Thursday, May 22, 2014
Wednesday, May 21, 2014
አንጋፋው የህወሃት መሪ አቶ ስብሃት ነጋ ተቃዋሚዎች እና መንግስት ተቀራርበው መነጋገር አለባቸው ኢንሺኤቲቩንም እኔ እወስዳለሁ አሉ።
አቶ ስብሐት ነጋ ተቃዋሚዎችን እና ኢሕአዴግ እንዲወያዩ ኢኒሼቲቭ እወስዳለሁ አሉየጀርመን ድምጽ ራዲዮ በእንወያይ መድረኩ፣ የሕወሃት አባት ተብለው የሚታወቁት አቶ ስብሐት ነጋ፣ የመኢአድ
ሊቀመንበር አቶ አበባዉ መሐሪ፣ ብቸኛ የተቃዋሚ ፓርቲ የፓርላማ ተወካይ አቶ ግርማ ሰይፉና፣ በቅርቡ አንድነት
ፓርቲን የተቀላቀሉት ደራሲና አክቲቪስት አቶ አስራት አብራሃ፣ በግንቦት ሃይ ዙሪያ ዉይይቶች በማድረግ ላለፉት 23
አመታት የነበረዉን ሁኔታ የቃኘ ሲሆን፣ በዉይይቱ ማብቂያ ላይ ኢሕአዴግን እና ተቃዋሚዎች ለአገር ጥቅም ሲባል
ተቀራረበው መነጋገር እንዳለባቸው ተግባብተዋል።
አቶ ስብሐት ነጋ መንግስትም ድክመቶቹን ማረም አለበት ፣ 1፣ 2፣ 3 እያለን መነጋገር አለብን ያሉ ሲሆን፣ ተቃዋሚዎችን እና ኢሕአዴግ የሚነጋገሩብት መድረክ ማን ያዘጋጅ የሚል ጥያቄ ሲቀርብላቸው «እኔ ኢኒሼቲቩን እወስዳለሁ» ሲሉ በአጭር ጊዜ ዉስጥ መድረኩን እንደሚያዘጋጁ ቃል ገብተዋል።
አቶ ግርማ ሰይፉ ና አቶ አበባዉ መሃሪ በበኩላቸው፣ የአቶ ሰብሐትን ኢኒቼቲቭ እንደሚደግፉና በሚደረጉ ዉይይቶች ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ለመከፈል ዝግጁ እንደሆነ የገለጹ ሲሆን፣ አቶ ስብሐትን ለወሰዱት ኢኒቼቲቭ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። አቶ አስራት በበኩላቸው እኛ ኢትዮጵያዊያን ድሃ የሆንበት ነገር ቢኖር አንዱ ተቀራረቦ መወያያይ አለመቻላችን መሆኑን አስረድተው፣ በአገር ጉዳዩ ዙሪያ ተቀራረቦ መነጋገሩ ተገቢ እንደሆነ አስረድተዋል።
አቶ አበባው የኢትዮጵያ ምሁራን፣ እንዲሁም ኢትዮጵያዊያን የአቶ ስብሐትን ኢኒቼቲቭ እንዲደግፉ ጥሩ አቅርበዋል።

Tuesday, May 20, 2014
በአባይ ጉዳይ ኃያላኑ በግብጽ ላይ ጫና እየፈጠሩ ነው
በአባይ ጉዳይ ኃያላኑ በግብጽ ላይ ጫና እየፈጠሩ ነው
የጫናው መነሻ አነጋገሪ ሆኗል
ምዕራባውያን ሃያላን አገሮች ግብጽ በአባይ ዙሪያ የድርድር ጠረጴዛ ላይ እንድትቀመጥ ጫና እያደረጉ መሆኑ ተሰማ፡፡
ዜናውን የዘገበው አልአህራም ቃል በቃል ግብጽ ላይ ጫና ተፈጠረ ብሎ ባይጽፍም ከዜናው ለመረዳት እንደተቻለው ግብጽ
ላይ ጫና እየተደረገባት ነው፡፡ ሃያላኑ ግብጽ ላይ እያሳደሩት ያለው ጫና መነጋገሪያ ሆኗል፡፡
እንደ ጋዜጣው ዘገባ ያለፈው ቅዳሜ የግብጹ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ከኢትዮጵያ ጋር በአባይ ጉዳይ ለመደራደር አገራቸው
ፈቃደኛ መሆኗን ማሳወቃቸውን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡ ይህንን መግለጫ ከመስጠታቸው በፊት የግብጹ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር
በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር መ/ቤት የውሃ ሃብት ልዩ አስተባባሪ ከሆኑት አሮን ሳልዝበርግ እንዲሁም ከአውሮጳ
ኅብረት ልዩ ልዑክ አልክሳንደር ሮንዶስ ጋር ውይይት ማድረጋቸው ታውቋል፡፡
በተለይ የአሜሪካው ተወካይ ሳልዝበርግ ወደ ግብጽ ከመሄዳቸው በፊት አዲስ አበባ ላይ ቆይታ አድርገው ከኢህአዴግ
ባለሥልጣናት ጋር ግድቡን በተመለከተ ውይይት ማድረጋቸው አብሮ ተዘግቧል፡፡ ሆኖም ኢህአዴግ በምን ነጥቦች ላይ
እንደተደራደረ የተገለጸ ነገር ባይኖርም የአሜሪካው ባለሥልጣን ወዲያው ወደ ግብጽ እንደበረሩ ግብጽ ድርድር መፈለጓ
መገለጹ የበርካታዎችን ትኩረት የሳበ ጉዳይ ሆኗል፡፡
በተያያዘ ዜና ሪፖርተር እሁድ ባስነበበው ጋዜጣ ላይ እስራኤል በኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጨት ሥራ የመሰማራት ዕቅድ
እንዳላት ዘግቧል፡፡ እስካሁን ድረስ እስራኤል በኃይል ማመንጨት ሥራ ውስጥ የመሳተፍ ፍላጎት እንዳለት ሲጠቀስ የቆየ
ቢሆንም ከዚሁ ጋር ተያይዞ በርካታ ጥያቄዎች ሲነሱ ቆይተዋል፡፡ ሆኖም እንደ ሪፖርተር ዘገባ ከሆነ በኢትዮጵያ
የፖታሽ ፕሮጀክት 30በመቶ ባለድርሻ የሆኑትን የሚስተር ኢዳን ኦፈር ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ዘርፍ
የመሰማራት ዕቅድ እንዳላቸው ጠቅሷል፡፡
እንደ ዜናው ከሆነ እስራኤል የምትሰማራበት የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ “የውኃ፣ የጂኦተርማል ወይም የንፋስ መሆኑን”
በግልጽ እንዳላሳወቀች ነገር ግን ጥናቱ በኩባንያው ቴክኒክ ቡድን በኩል እንደሚካሄድ የኩባንያው ባለቤት
መናገራቸውን ጨምሮ ዘግቧል፡፡ ሚስተር ኦፈር የሚመሩት ኢዝራኤሊ ኬሚካልስ የተባለው ኩባንያ በማዳበሪያና መሰል
ምርቶች ላይ የተሠማራ ሲሆን የማዕድን ማውጣት ተግባሩን በእስራኤል፣ በአሜሪካ፣ በአውሮጳና ቻይን ያካሂዳል፡፡
ከኩባንያው አክሲዮን ሁለተኛው ከፍተኛ ባለድርሻ የካናዳው የፖታሽ ኮርፖሬሽን እንደሆነ ይታወቃል፡፡
የእስራኤል በኢትዮጵያ በኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ተግባር የመሰማራቷ ዜና ምናልባትም ከአባይ ግድብ ጀርባ የሃያላኑ
አገራት ድጋፍና ጥበቃ እንዲሁም ቀጥተኛ ወይም ተዘዋዋሪ የሆነ ጥቅም የማስከበር ፍላጎት እንዳለ የሚሰነዘረውን
ሃሳብ ያጠነክረዋል፡፡ አንዳንዶች እንደሚሉት የጫናው መነሻ ይህ የጡንቸኞቹ የጥቅም ጉዳይ እንደሆነ ያስረግጣል
ይላሉ፡፡
በዚህና በተለያዩ ምክንያቶች በአባይ ግድብ ዙሪያ የሚነሱት መላምቶች ወይም መከራከሪያዎች ከሃያላኑ ጫና ጋር
ተዳምረው መነጋገሪያ ርዕስ ሆኗል፡፡ግብጽ ጫናውን አስመልክቶ በይፋ የገለጸችው ተቃውሞ ወይም ቅሬታ የለም፡፡ ይሁን
እንጂ በግብጽ የፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ዘመቻ ላይ ያሉትና የምዕራባውያን ቀጥተኛ ድጋፍ ያላቸው ፊልድ ማርሻል አል-ሲሲ “የውሃ ነገር” ለግብጽ “የህይወትና የሞት ጉዳይ” መሆኑን መግለጻቸውንና ከኢትዮጵያ ጋር በመሆን መፍትሔ መፈለጉ “የግድ” እንደሆነ ማስታወቃቸውን ጎልጉል ዘግቦ ነበር፡፡
በዜናው መሠረት አል-ሲሲ “የሌሎችን ፍላጎትና ጥቅም የምንረዳ መሆናችንን ማሳየት ይገባናል፤ (የዚያኑ ያህልም)
የራሳችንን ጥቅም ለማስጠበቅ ጽኑ መሆን አለብን፤ (ምክንያቱም) ውሃ ማለት ለእኛ የህይወትና የሞት ጉዳይ ነው”
ማለታቸውን ጎልጉል ጨምሮ
በማስታወቅ እጩው ፕሬዚዳንት ከዚህ በፊት ያልታየ መለሳለስ በማሳየት “ለኢትዮጵያና ለሌሎች አፍሪካ ወንድሞቻችን
ተገቢውን ጥረት አለማድረጋችንን ማመን አለብን፤ በዚህ ዓይነቱ ጉዳይ ለመተባበርና መፍትሔ ለማግኘት ድርድርና የጋራ
መግባባት ቁልፍ ናቸው” ማለታቸውን ጭምሮ ዘግቦ እንደ ነበር ይታወሳል፡፡
የአባይ ጉዳይ ኢትዮጵያንና ግብጽን ለዘመናት በተለያዩ እሰጥ አገባ ውስጥ የከተታቸው ነው፡፡ በአባይ ከሚፈሰው
90በመቶ የሚሆነው ውሃ የሚመነጨው እንዲሁም በአባይ ተጠርጎ ከሚወሰደው ለም አፈር 96በመቶ የሚሆነው የሚሄደው
ከኢትዮጵያ ደጋማ ክፍል እንደሆነ ይታወቃል፡፡ የአባይ ወንዝን አጠቃቀም በተመለከተ የሚያስተዳድሩት ሕጎች እኤአ
በ1929 እና በ1959 በግብጽና በሱዳን እንዲሁም በግብጽና በብሪታኒያ በቅኝ ግዛት ዘመን በተፈረሙ ውሎች ሲሆን
በውሉ መሠረት ግብጽና ሱዳን ከአባይ ወንዝ ኃብት በድምሩ 90በመቶ የሚሆነውን የመጠቀም መብት አላቸው (ይህም
በየዓመቱ 55.5 ሜትር ኩብ የሚሆነው ለግብጽ 18.5 የሚሆነው ደግሞ ለሱዳን ማለት ነው)፡፡
ይህ ኢትዮጵያን የሚጎዳ ውልና አሠራር እንዳለ ሆኖ የዛሬ አራት ዓመት አካባቢ በታህሳስ ወር አቶ መለስ ይህንኑ
የቅኝ ግዛት ዘመን ውል እንደገና በመቀበል ግብጽ በአባይ ወንዝ ላይ የተፈቀደላትን የድርሻ ኮታ ማግኘት ይገባታል
በማለት ስምምነት መፈረማቸውን አልአህራም በወቅቱ ዘግቦ እንደነበር አይዘነጋም፡፡
ከጥቂት ቀናት በፊት ደግሞ ኢነርጂ ቢዝነስ ሪቪውን በመጥቀስ ሪፖርተር ለንባብ ባበቃው ዜና ላይ “በምሥራቃዊ ሱዳን
በኩል ከከሰላ ግዛት ተነስቶ ወደ ኤርትራ በሚዘረጋ የ45 ኪሎ ሜትር የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር” በኩል
ሱዳን ከኢትዮጵያ የምትገዛውን የኤሌክትሪክ ኃይል ለኤርትራ ለመሸጥ እንቅስቃሴ ላይ መሆኗን ዘግቧል፡፡ ሱዳን ከዚሁ
የአባይ ግድብ በርካሽ የምትገዛውን የኤሌክትሪክ ኃይል ምን ያህሉን በምን ያህል ትርፍ ለኤርትራ ለመሸጥ እንዳሰበች
እስካሁን አለመታወቁን ጋዜጣው ጭምሮ አስታውቋል፡፡
አቶ መለስ ሥልጣን ላይ በነበሩበት ዓመታት ኤርትራ ከኢትዮጵያ ያለቀረጥ ክፍያ በነጻ ያህል ከኢትዮጵያ የምትወስደውን
ቡና በዓለም ገበያ ላይ በመሸጥ ከቡና አምራችና ሻጭ አገራት ውስጥ ተመዝግባ እንደነበር አይዘነጋም፡፡ ከዚህ ልምድ
በመነሳት አሁንም ኤርትራ ከሱዳን የምትገዛውን ከአባይ ግድብ የሚመነጨውን የኤሌክትሪክ ኃይል በአቅራቢያዋ ለሚገኘው
አጎራባቿ የሰሜን ኢትዮጵያ ክልል መልሳ በትርፍ ትሸጥ ይሆናል የሚለው አስተያየት ስላቃዊ ቢሆንም አነጋጋሪ እየሆነ
መጥቷል፡፡
Saturday, May 17, 2014
አኖሌ…..የባህር ዳር ነውር….አምቦ እና ግምቢ
ህወሃት የአኖሌ ሃውልት እንዲሰራ ሲፈቅድ የሚታየው በዚህ ሃውልት ምክንያት አብረው የኖሩ ህዝቦች ደም ተቃብተው
በጠላትነት ሲቆሙ ነው።የአኖሌ ሃውልት በህወሃት-ኦህዴድ እጅ ሁኖ የሚሰብከው አብሮነትን ሳይሆን ልዩነትን ነው።
ፍቅርን ሳይሆን ጥላቻን ነው። የአኖሌን ሃውልት የሚመስል ሌላ ሰማይ ጠቀስ ኃውልት በመቀሌ ከተማ ለትውልድ
የሚተላለፍ ቂምን እየሰበከ ቁሟል። ስሙንም “የሰማዕታት” ሃውልት ብለው ይጠሩታል። ከአሩሲው አኖሌም ሆነ ከመቀሌው
ሠማዕታት ሃውልት ትውልዱ የሚያተርፈው ቂም እና በቀል ነው። እነዚህ ሁለት ኃውልቶች ሠላምን አይሰብኩም፤ አብሮ
መኖርን አያስተምሩም። ሃውሎቶቹን ያየ ግማሹ ቂም ይቋጥራል፤ ገሚሱ ይገረማል፤ ሌላውም የአገሪቱን መፃኢ ሁኔታ
እያሰበ ይተክዛል። ህወሃቶች እጅግ ብዙ አሰቃቂ፤ አስገራሚ እና አሳዛኝ ነውሮችን በዚያች አገር ላይ መፈፀማቸው
የታወቀ ነው።
የአኖሌ ኃውልት ተሠርቶ ከተመረቀ በኋላ በባህር ዳር ከተማ አማራና ኦሮሞ ኳስ እንዲጫወቱ ተደረገ። በዚያ ስቴዲየም
ህወሃት-ብአዴን ያሰለጠኗቸው ምናምንቴ ካድሬዎች በኦሮሞዎቹ ላይ የስድብ ናዳ አወረዱ። ስድቡም በቀጥታ በቴሌቭዥን
ለህዝቡ እንዲደርስ ሆነ። ይሄን ተመልክተው የሚቆጡ ሌሎች ምናምንቴዎች በህወሃት-ኦህዴዶች ተዘጋጅተው ወደ ህዝቡ
መካከል ዘው ብለው ገቡ። የሚያቆማቸውም የመንግስት አካል አልተገኘም።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በአዲስ አበባ “ልማት” ሰበብ በዙሪያዋ የሚገኙ ብዙ ገበሬዎች ተፈናቅለው ሜዳ ላይ ሊጣሉ
የመሆናቸ ነገር ይናፈስ ጀመር።የሚነፍሰውን ወሬ መንግስት ነኝ የሚለው ቡድን ለህዝቡ ለማስረዳት ፈቃደኛ ሳይሆን
በመቅረቱ ዜጎች ተቆጡ። ተማሪዎችም በየትምህት ክፍላቸው የገበሬዎችን ጥያቄ አንግበው ተነሱ። ”መሬት ላራሹ”
እንደገና ዞሮ መጣ። ህወሃት ከማንም በላይ ለአርሶ አደሩ ቆሜያለው ቢልም እንደ ህወሃት አርሶ አደሩን መሬት አልባ
ያደርገ ሥርዓት በኢትዮጵያ ታሪክ አልታየም። የአርሶ አደሩን መሬት ነጥቆ ለባዕዳን በመሸጥ እና አርሶ አደሩን
ከነቤተሰቡ ሜዳ ላይ በመበተን ህወሃትን የሚመስለው እስከ ዛሬ አልታየም።
በየትምህርት ተቋማቱ ተማሪዎች ”ገበሬ ለምን ይፈናቀላል?” እያሉ መጠየቅ ጀመሩ። ከዚህ ፊትሃዊ ጥያቄ ጀርባ
የአማራውን ህዝብ ስጋት ውስጥ የሚከት ነገር አብሮ ብቅ አለ።የገበሬዎች የመፈናቀል ጥያቄ ተረስቶ የተቃጠለው
‘የአማራ” ነው የተባለ ሆቴል የኢቲቪን መስኮት ያጨናንቀው ጀመር። በግምቢም የድሃ አማሮች ቤት እየተመረጠ በድንጋይ
ይወቀር ጀመር። የንፁሃን አማሮች ደምም በከንቱ ፈሰሰ። እንዲህ ሲሆን ህወሃቶች ከቅጥረኛቸው ኦህዴድ ጋር የደም
ፅዋቸውን አንስተው እየተጎነጩ በደስታ ሰከሩ።
የተከበራችሁ ያገራችን ዜጐች !
ከመቼውም ግዜ በከፋ ሁኔታ አገራችን አስቸጋሪ መንግድ ውስጥ ትገኛለች።በየቦታው በብሄሮች መካከል የሚነሳውን ግጭት
የሚመራው ህወሃት መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል። ደጋግመን ለማለት እንደሞከርነው ህወሃት የህዝብ ጠላት መሆንን
የመረጠ ቡድን ነው። ህወሃት ”አማራና ተፈጥሮ የትግራይ ህዝብ ቀንደኛ ጠላቶች ናቸው” ብሎ የሚያምን ቡድን
ነው።በዋናነት የአማራን ህዝብ ለማጥፋት ባለፉት ሁለት አስርተ ዓመታት ሳይታክት ሠርቷል። አንድን ህዝብ እንደጠላት
የቆጠረ ቡድን ለሌሎች የሰው ልጆች ወዳጅ እንዲሆን የሚያስችል የሞራል ግዴታ ይኖርዋል ለማለት አይቻልም።ስለዚህም
ህወሃት የሰው ልጆች ሁሉ ጠላት ነው። ህወሃት ይሄ ነው ተብሎ የሚጠቀስ በጎ ታሪክ ያለው ድርጅት አይደለም።
የህወሃት ታሪክ የግዲያ ታሪክ ነው። የህወሃት ታሪክ የዝሪፊያ ታሪክ ነው። የህወት ታሪክ የአገርን ክብር የማዋረድ
ታሪክ ነው። ህወሃት ከዚህ የተለየ ታሪክ ያለው ቡድን አይደለም።
ውድ ኢትዮጵያዊያን !
አሁን ከእኛ ከፍ ያለ ትዕግስት፤ አስተዋይነት፤ አርቆ አሳቢነት ይጠበቃል። እኛ እንደ ህወሃቶች ርህራሄ የሌለን
ጨካኞች መሆን አይኖርብንም።ህወሃቶች በዘረጉልን መረብ ውስጥ ገብተን እርስ በእርሳችን እንዳንተላለቅ ብርቱ ጥንቃቄ
ማድረግ ይኖርብናል። በአምቦ የሆነውን አይተናል።ከግምቢም አሳዛኝ ድምፅ ሰምተናል። ይሄ ግን የህዝብ ፍላጎት ሳይሆን
የህወሃት-ኦህዴዶች እቅድ ነው። በባህር ዳር ስቴዲየም የተሰማው ነውረኛ ድምፅ የህዝብ ፍላጎት አይደለም።
የህወሃት-ብ አዴኖች እጅ ሥራ ነው። ህወሃቶች በአማራውና በኦሮሞው መካከል የከረረ ግጭት አስነስተው በሚፈሰው
የንፁሃን ዜጎች ደም እጃቸውን ታጠበው መቶ ዓመት ከነ ልጅ ልጆቻቸው ሊገዙን ይፈልጋሉ። ይሄ በሁሉም ዘንድ የሚታወቅ
እውነት ነው። ይሄ ፍላጎታቻው እውን እንዳይሆን ፈጣሪን በመፍራት እና ለእውነት፤ ለፍትህ፤ለእኩልነት እና
ለሁላችንም የምትሆን ኢትዮጵያን ለመፍጠር ዓይናችንን ከህወሃቶች ላይ ሳናነሳ በፅናት እንታገል።ኢትዮጵያችን ፈርጀ
ብዙ ችግሮች ያሉባት አገር ነች። ከሁሉም ችግሯ የሚልቀው ግን ፍፁም ኃላፊነት የማይሰማቸው አገርን ለመምራት ግዙፍ
የሆነ የሞራልም ሆነ የእውቀት ጉድለቶች ያሏቸው ህውሃቶች በአገራችን ጫንቃ ላይ ቁጢጢ ማለታቸው ነው። እነዚህ
ቡድኖች አደብ ገዝተው ከህግ በታች መሆንን መልመድ ይኖርባቸዋል። እነርሱ ከህግ በላይ ሁነው ሌሎች ዜግች ከእነርሱ
ሥር ሁነው የሚገኝ ልማትም ሆነ ሠላም የለም።
የተከበራችሁ የአገራችን ዜጎች !
ህወሃቶች ለርካሽ የፖለቲካ ጥቅም ሲሉ የሃውዜንን ህዝብ ማስጨፍጨፋቸው የቅርብ ግዜ ትዝታችን ነው። ዛሬም የሚያሰሉት
እንዲህ ዓይነቱን ርካሽ ጥቅም ነው። በዚህ ግዜ እኔ ንፁህ ኦሮሞ ነኝ፤ እኔ ንፁህ አማራ ነኝ፤እኔ ከዚህ ነኝ እኔ
ከዚያ ነኝ ማለት አይጠቅምም። እንዲህ ለማለት ግዜ አለው።ህወሃቶች የመጨረሻውን ካርድ መዘው ምድሪቷን በደም
ሊያጨቀዩ ቆርጠው ተነስተዋል። በህዝቦች መካከል የሚነሳው ግጭትና የሚፈሰው ደም የህወሃቶችን የስልጣን ጥም ለማርካት
የሚቀርብ መሥዋዕት ነው። የንፁሃን ዜጎች ደም በከንቱ እንዳይፈስ ከልዩነቶቻችን በላይ አንድ በሚያደርጉን ቁም
ነገሮች ላይ እናተኩር። ዓይኖቻችን ልዩነቶቻችንን ለመጠፋፊያነት ለመጠቀም ከሚፈልጉት ህወሃቶች ላይ ሳናነሳ
በአንድነት ለእኩልነት፤ ለነፃነት፤ለፍትህ እና ለሁላችንም የምትሆን አገር ለመፍጠር ሳናቅማማ እንታገል። ህወሃት
እያለ ለሁላችንም የምትሆን አገር እንደማትኖር የታወቀ ነው።ለሁላችንም የምትሆን አገር እንድትፈጠር በየትኛውም
መንገድ ህወሃት መወገድ ይኖርበታል።
አኖሌ…ባህር ዳር….አምቦና ግምቢ ላይ የሰማናቸው ድምፆች የጥፋት ድምፆች ናቸው። በዚህ ሁኔታ ለፈሰሰው ደም
ተጠያቂው “መንግስት” ነኝ የሚለው ህወሃት-ኢህአዴግ ነው። የሌላ የማንም እጅ የለበትም። የንፁሃንን ህይወት ቀጥፎ
በሠላም ስልጣን ላይ መቆየት ፈፅሞ አይቻልም። ህወሃት የብዙ የትግራይ ልጆችን መሠዋዕትነት ከንቱ ያስቀረ የጨካኞችና
የነፍሰ ገዳዮች ስብስብ ሁኗል። ይሄን ነፍሰ ገዳይና ጨካኝ ቡድን ከተቆናጠጠበት ወንበር ላይ ለማውረድ ቆርጠን
በምንችለው ሁሉ እየሠራን ነው። ዘወትር እንደምንለው ሁላችሁም በያላችሁበት፤ በምትችሉት መንገድ ሁሉ ለፍትህ፤
ለነፃነትና ለእኩልነት ዘብ የምትቆሙ ሁኑ እንጂ ህወሃቶች ባዘጋጁት የመተላለቂያ መርብ ውስጥ የምትወድቁ ደካሞች
አትሁኑ።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !
Friday, May 16, 2014
አንቀጽ 19 በተግባር ተጥሷል – ሕገ መንግስቱን ሳያከብሩ ማስከበር አይቻልም የታሳሪዎች የምርመራ ሂደትን አስመልክቶ ከዞን 9 የተሰጠ መግለጫ(ዞን9)
May 16, 2014
ከታሰሩ 22 ቀናትን ያስቆጠሩት የዞን
ዘጠኝ አባላትና ጋዜጠኞች በቤተሰብም ሆነ በህግ ባለሞያ የመገናኘት መብታቸውን ለማግኘት 19 ቀናት ፈጅቶባቸዋል፡፡
ከታሰሩ እስከ 17 ቀን ድረስ ማንም የቤተሰብ አባል ሳይጎበኛቸውና በወዳጅ ዘመዶች ሳይጠየቁ የከረሙ ሲሆን ከጠበቆች
ጋር ለመገናኘት ደግሞ 19 ቀናት ወስዷል፡፡ አሁንም ከጠበቆቻቸው ጋር መገናኘት ያልቻሉ ቀሪ እስረኞች አሉ።
በተለምዶው እነደሚደረገው የፓሊስ ማእከላዊ ምርመራ የቤተሰብ ጉብኝትን “አይቻልም” በሚል ቀላል ቃል የከለከለ ሲሆን ለጠበቆች ስብሰባ ላይ ነን የሚል ምክንያት ሲሰጥ ከርሟል፡፡ ይህ በመሆኑም የተነሳ የተያዙ ሰዎች መብት የሆነው የህገ መንግስቱ አንቀጽ 19 ሁለት ላይ ያለው የተያዙ ሰዎች ያለመናገር መብት ( the right to remain silent) በይፋ ተጥሶ ያለማንም የህግ ባለሞያ ምክር ለብዙ ቀናት ምርመራ ሲደረግባቸው ቆይቷል፡፡ ምርመራቸውን ጨርሰዋል ተብለው የታሰቡ ታሳሪዎቸን ካልሆነም በስተቀር በምርመራ ወቅት የህግ ባለሞያ ለማግኘት አልተፈቀደላቸውም፡፡
በመሰረቱ መሰረታዊ የሆነው ያለመናገር መብትና የህግ ባለሞያ የማግኘት መብት መከልከሉ የተለመደውን ማእከላዊ ምርመራ የሚታማበትን የማስገደድ ምርመራ እውነተኛነት የሚያጋልጥ ነው፡፡ በተጨማሪም የአካልና የስነልቦና ጉዳት የማድረስ ምርመራ ሲፈጸምባቸው እነደነበረ የተያዙ የዞን ዘጠኝ አባላት በተናገሩበት ወቅት ፍርድ ቤቱ የነዚህን ጉዳቶች መከልከል ላይ አስተያየት ከመስጠት ውጪ ይሄ ነው የሚባል እርምጃ እና ማጣራት ለመውሰድ አልሞከረም፡፡
ማእከላዊ ምርመራ ከዚህ በፌት የሚታወቅበት ድብደባ፣ ምግብና እንቅልፍ መከልከል፣ የስነልቦና ጫና እና ማስፈራሪያ የተለያዩ ዛቻዎች ሁሉም በተያዙ የዞን ዘጠኝ አባላትና ጋዜጠኞች ላይ በተለያየ መልኩ እነደደረሰ ተረድተናል፡፡ ይህም ምርመራውን ተከትሎ የሚመጣውን ማንኛውንም ማስረጃ በህግም በሞራልም ተቀባይነት እነዳይኖረው እነደሚያደርግ እናውቃለን፡፡
ከታሳሪዎች የሚገኙ ማንኛውም መረጃዎች በከፍተኛ ተጽእኖ ስር እንደተሰጡ አንዲሁም ዝም የማለትና የህግ ባለሞያ ምክር የማግኘት ህገ መንግስታዊ መብቶቻቸው ተጥሰው የተገኙ እንደሆኑ ዞን ዘጠኝ ያምናል፡፡ በወንጀል ህግ ስነስርአት መሰረት እነዚህ ያለህግ ባለሞያ መጎብኝት እና ያለመናገር መብታቸው (የህገ መንግስቱ አንቀጽ 19) ተጥሶ የተገኙ መረጃዎች በዚህ ምክንያት ብቻ ተቀባይነት እነደማይኖራቸውም የአገሪትዋ ህግ ይደነግጋል፡፡ በመሆኑም መንግስት ታሳሪዎቹ አንደፈታ እና ጉዳያቸው ህገ መንግሰታዊ እና የወንጀል ህግ ስነስርአት ህጉን ተከትሎ አንዲሆን እንዲያደርግና ሌሎች እንዲያከብሩ የሚጠይቀውን ህግ መንግስት ራሱ በማክበር አንዲጀምር አሁንም በድጋሚ ጥሪ እናቀርባለን ፡፡
ህገ መንግስታዊ መብታቸው ተጥሶ ማእከላዊ ምርመራ የሚገኙ የዞን ዘጠኝ አባላት እና ጋዜጠኞች ወዳጆቻችን ያለንን ክብር እና ፍቅር እየገለጽን ጽናታቸው አስተማሪ ሲሆን በሚከተሉት ቀናት በሚኖሩት ማንኛውም የህግ ሂደቶች ውስጥ የሚኖሩትን አዳዲስ መረጃዎች ለዞን ዘጠኝ ነዋሪያን እንገልጻለን፡፡ነገ ቅዳሜ ግንቦት 9 እና እሁድ ግንቦት 10 የሚደረጉ የፍርድ ቤት ሄደቶችን አራዳ ፍርድ ቤት አንደኛ ወንጀል ችሎት ጠዋት በመገኘት መከታተልና አጋርነታችሁን ማሳየት ትችላላችሁ፡፡
የዞን ዘጠኝ ስብስብ አባላቶቹ ምንም አይነት ህገ ወጥ ተግባር ላይ ተሰማርተው እንደማያውቁ ለማረጋገጥ ይወዳል፡፡

የኢትዮ-ሱዳን ድንበር ክለላ ዛሬ በድብቅ ሊፈረም ነው! – አብርሃ ደስታ
የኢትዮ ሱዳን ዳር ድንበር በግልፅ የተከለለ እንዳልሆነ ይታወቃል። የኢትዮጵያ አርሶአደሮች የሚጠቀሙት መሬት የኢትዮጵያ እንደሆነ ሲወሰድ ሱዳናውያን የሚገለገሉበትም የሱዳን ነው ተብሎ ይታሰባል። ከቅርብ
ግዜ ወዲህ ግን የኢህአዴግ መንግስት ኢትዮጵያውያን አርሶአደሮችን ከቀያቸው እያፈናቀለ ለሱዳን ማስረከቡ ይታወቃል።
ብዙ የኢትዮጵያ አርሶአደሮች ተፈናቅለዋል፣ የተወሰኑ ተለዋጭ መሬት ሲሰጣቸው ምንም ያላገኙም አሉ።
ድንበሩ ብዙ ዉዝግብና ተቃውሞ ያለው ሲሆን የኢህአዴግ መንግስት ከሱዳኖች ጋር በመተባበር በድብቅ ለመከለል ተስማምቷል። እንዲህ ነው የተደረገው፥ በድንበሩ አከባቢ የሚገኙ ኗሪዎች (የኢትዮጵያና የሱዳን) ድንበራቸውን አይተው ክለላውን ይፈፅማሉ፣ ይፈራረማሉ። ለሱዳን የተሰጠው መሬት ታውቋል። ሁሉም ነገር በኢህአዴግና የሱዳን መንግስት አልቋል። አሁን “የሀገር ሽማግሌዎች” እንዲፈርሙ እየተደረገ ነው። የሀገር ሽማግሌዎች እንዲፈርሙ የተፈለገበት ምክንያት የድንበር ክለላ የተከናወነው በኗሪዎች ነው እንዲባል ነው። ለሌላ ግዜም ምስክር ሁነው እንዲቀርቡ ነው።
በዚህ መሰረት በድንበሩ አከባቢ ከሚገኙ የኢትዮጵያ ከተሞች ማይካድራና በረከት የተወሰኑ ሰዎች በካድሬዎች ተመርጠው “ኮሚቴ” ተሰኝተው ዛሬ ግንቦት 8, 2006 ዓም እንዲፈርሙ ወደ ሱዳን ድንበር ተጉዘዋል። እነዚህ ኮሚቴ ተብለው የተመረጡ ሰዎች ስለ ድንበሩ ይሁን አከባቢው እውቀት የሌላቸው፣ የአከባቢው ኗሪዎች ሳይሆኑ በቅርብ ግዜ ባከባቢው መሬት የተሰጣቸው ሰፈርተኞች ናቸው። ዕድሜየቸውም ከአርባ በታች ነው፣ ትምህርት የላቸውም፣ የድንበሩ ታሪክ አያውቁም፣ መሬት ስለተሰጣቸውና በካድሬዎች ስለታዘዙ ብቻ ሊፈርሙ የሚችሉ ናቸው። ስለዚህ የሀገር ሽማግሌዎች ሊባሉ አይችሉም። ምክንያቱም ሰፈርተኞች እንጂ ኗሪዎች አይደሉም፣ ወጣቶች ናቸው (ድንበሩ ላያውቁት ይችላሉ)፣ ትምህርት የላቸውም (የድንበር ጉዳይ ምን ያህል ጥንቃቄ የሚያስፈልገው እንደሆነ ላይረዱ ይችላሉ) ወዘተ። ዛሬ እንዲፈርሙ የተወሰዱት በድብቅ መሆኑ ነው።
የድንበር ጉዳይና ሌሎች የሑመራ አከባቢ ኗሪዎች በማየሉ ተቃውሞ እየተቀሰቀሰ በመሆኑ ባከባቢው ተገኝቶ መረጃ ማሰባሰብ አስቸጋሪ እየሆነ ነው። የመንግስት አካላት ኗሪዎች ለሌሎች አካላት መረጃ እንዳይሰጡ እያስፈራሩ ነው። መረጃ መሰብሰብም አይፈቀድም። በዚሁ አጋጣሚ ግርማይ ወልደግዮርግስ የተባለ የድምፂ ወያነ ሬድዮ ጋዜጠኛ ባስተዳዳሪዎች ከቀረቡለት አራት ካድሬዎች ዉጭ ሌሎች ኗሪዎችን በማነጋገሩ ምክንያት ባለስልጣናት ፖሊስ ጠርተው አስረውታል። የድምፂ ወያነ ሬድዮ ጋዜጠኛ ህዝብን ሳንፈቅድልህ አገጋግረሃል ተብሎ ነው የታሰረው።
በሑመራ አከባቢ ብዙ ተደራራቢ ችግሮች አሉ። ሕገወጥ የመሬት ሽንሸና እየተደረገ ነው። ኗሪዎችን ከቀያቸው እየተፈናቀሉ ስርዓቱ ያገለግላሉ ለተባሉ ሰዎች መሬት እየተሰጠ ይገኛል። ለምሳሌ አቶ ካሕሳይ ገብረሚካኤል የተባሉ ያከባቢው ኗሪ መሬታቸው ተወስዶ ለሌላ የህወሓት ካድሬ ዉሽማ ተሰጥቷል። ፍትሐዊ ያልሆነ እርምጃ እየተወሰደ ይገኛል።
በድንበሩ ጉዳይ በድብቅ እየተፈረመ ያለው ነገር ተቀባይነት የለውም። ለሱዳን የሚሰጥ መሬት መኖር የለበትም። ተግባሩ ሕገወጥ ነው። ኢህአዴግም ለተግባሩ ይጠየቃል።

Wednesday, May 14, 2014
Tuesday, May 13, 2014
ዶ/ር ሼክስፒር ፈይሳ የሃይለመድህን አበራን ጉዳይ ለመከታተል ወደ ጄኔቫ አመራ
May 13, 2014
13 may 2014 (EMF ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራን ጉዳይ ለመከታተል ኢትዮጵያዊው የህግ ባለሞያ ዶ/ር ሼክስፒር ፈይሳ ባለፈው ሳምንት ወደ ጄኔቭ-ስዊዘርላንድ ተጉዟል።
ሼክስፒር ፈይሳ የረዳት ፓይለቱን ጉዳይ ከሚኖርበት ከሲያትል ከተማ በቅርብ ሲከታተል ቆይቶ ነው ወደ ጄኔቭ ያመራው። ጄኔቭ እንደደረሰም የሃይለመድህን አበራን ጠበቃና ጉዳዩን ከሚከታተሉ አካላት ጋር በስፋት ተወያይቷል። በተለይ ከረዳት ፓይለቱ ጠበቃ ጋር ረጅም ሰዓታት በመውሰድ በበርካታ የህግና የቴክኒክ ጉዳዮች ላይ በጥልቅ ተነጋግሯል።
ረዳት ፓይለቱ ሙሉ በሙሉ ጤነኛ እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል።
ኢትዮጵያዊ የህግና እንዳስፈለጊነቱ የህክምና ባለሞያዎች ጋር እንዲገናኝም ዶ/ር ሼክስፒር ምክር ሰጥቷል።
የረዳት ፓይለቱ ጠበቃ የስዊስ መንግስት ሃይለመድህን አበራን ለኢትዮጵያ አሳልፎ እንደማይሰጥና ግዚያዊ የስደት ፈቃድ እንዲሰጠው ውሳኔ መተላለፉን ያረጋገጠ ሲሆን – ጉዳዩ በቅርብ ጊዜ በሚሰየመው ግልጽ ችሎት እልባት እንደሚያገኝ አመላክቷል።
የሃይለመድህን አበራን ወደ ኢትዮጵያ ለማስመለስ በአቶ አስመላሽ ወልደ-ስላሴ የተመራ ከፍተኛ የኢህአዴግ ቡድን ጄኔቭ፣ ከርሞ ጥያቄው በስዊዘርላንድ መንግስት ውድቅ መደረጉ ይታወሳል።
ቡድኑ የስዊስ ፌዴሬሽን የህግ አካላትን ለማሳመን ካቀረበው ምክንያት ዋነኛው፣ ረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራ የአእምሮ በሽተኛ መሆኑን እና ይህንንም የራሱ ቤተሰብ አባላት እንዳረጋገጡላቸው ገልጸዋል። የስዊዝ መንግስት ግን ጥያቄውን ውድቅ አድርጎታል። ለዚህም የሰጠው ዋነኛ ምክንያት፤ የሞት ፍርድን ተግባራዊ ለሚያደርግ መንግስት ማንንም አሳልፌ አልሰጥም የሚል ሲሆን ይህ ባይሆንም፣ በስዊዘርላንድ እና በኢትዮጵያ መሃል ተጠርጣሪ እስረኛን የማስመለስ ውል የለም ብለዋል።
ረዳት ፓይለቱ ለግዜው ሰው ማግኘት እንደማይፈልግ የተነገረ ሲሆን: ወንድሙ ዶ/ር እንዳላማው አበራ እና በጀርመን የምትኖር እህቱ ሃይማኖት አበራ ጄኔቭ ድረስ በመሄድ ሃይለመድህን አበራን ከሚገኝበት እስር ቤት ጎብኝተውታል።
ወጣት ሃይለመድህን አበራ ባለፈው የካቲት 10፣ 2006 ዓ.ም. የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነውን ቦይንግ 767 አግቶ ጄኔቭ ስዊዘርላንድ ላይ በማሳረፍ እዚያው የፖለቲካ ጥገኝነት መጠየቁ ይታወሳል። የአለም ዜና ርዕስ ሁሉ ትኩረት ስቦ የነበረው ይህ ልዩ ክስተት የኢትዮጵያን የሰብአዊ መብት ሁኔታና የአስተዳደር በደል አደባባይ በማውጣቱ የገዢው ፓርቲ አባላትን እጅግ እንዳበሳጨ ይነገራል።
አንዳንድ መገናኘ ብዙሃን እንደገለጹት የአጎቱ ድንገተኛ ህልፈት ርዳት ፓይለቱን አስቆጥቶት ነበር። የሃይለመድህን አበራ አጎት፤ ዶ/ር እምሩ ሥዩም ህይወት በድንገት ማለፍ ለብዙዎች ያልተፈታ እንቆቅልሽ ነው። ዶ/ር እምሩ ሥዩም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር ነበሩ።
በአለም ዙሪያ ያሉ ኢትዮጵያውያን ወጣቱ ፓይለት ሃይለመድህን አበራን መደገፋቸውን እንደቀጠሉ ሲሆን በረዳት ፓይለቱ ስም የተከፈቱ ድረ-ገጾች እና የፌስቡክ መድረኮች ላይ አሁንም ሰፊ ዘመቻ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።
ዶ/ር ሼክስፒር ፈይሳ በረዳቱ ጉዳይ ላይ ማንኛውንም ትብብር ለማድረግ ቃል የገባ ሲሆን የስዊስ ጠበቆችም በዚህ ከክፍያ ነጸ የሆነ ትብብሩ አድናቆታቸውን ገልጸዋል።

ደቡብ ሱዳን – የሰላም ድርድር ወይስ ቁማር? “ካልፈረማችሁ ለICC አሳልፈን እንሰጣችኋለን” ሃይለማርያም
የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ስምምነቱን የማይፈርሙ ከሆነ ጠ/ሚ/ር ሃይለማርያም ለዓለምአቀፉ የወንጀለኞች ፍርድቤት (ICC) አሳልፈው እንደሚሰጧቸው መግለጻቸውን በጁባ የጎልጉል
ምንጭ አስታወቁ፡፡ ሱዳን ትሪቢዩን በበኩሉ ስምምነቱ የማይፈረም ከሆነ እስር እንደሚጠብቃቸው ሃይለማርያም ለሳልቫ
ኪር መናገራቸውን ምንጮቹን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡ አርብ የተፈጸመው የስምምነት ፊርማ ገና ሳይደርቅ ሁለቱም ኃይላት ወደ
እርስበርስ ውጊያው ተመልሰው በመግባት እየተካሰሱ ነው፡፡
እጅግ ደም አፋሳሽ በሆነውና ለበርካታ ዜጎች መፈናቀል ምክንያት
የሆነው የደቡብ ሱዳን የእርስበርስ ጦርነት ከጥቂት ቀናት በፊት አዲስ አበባ ላይ በፊርማ ሲጸድቅ ብዙ ተስፋ
የተጣለበት ነበር፡፡ ሆኖም ስምምነቱ ከተጽዕኖ ባለፈ መልኩ በዕለቱ በፊርማ ካልጸደቀ ሳልቫ ኪርንም ሆነ ሬክ ማቻርን
ሃይለማርያም ደሳለኝ ለዓለምአቀፉ የወንጀለኞች ፍርድቤት አሳልፈው እንደሚሰጧቸው የተነገራቸው መሆኑን የጎልጉል
ምንጭ ከጁባ አስረድተዋል፡፡ ሳልቫ ኪር ወደ ጁባ ከተመለሱ በኋላ ከካቢኔያቸውና ቅርብ አማካሪዎቻቸው ጋር
በተነጋገሩ ወቅት በስምምነቱ ወቅት የነበረውን ሁኔታ ባስረዱበት ወቅት መናገራቸውን የመረጃው አቀባይ ለጎልጉል አስታውቀዋል፡፡ ሁኔታው ለደቡብ ሱዳን እጅግ አሳፋሪ ከመሆኑ የተነሳ ደቡብ ሱዳን አምባሳደሯን ከኢትዮጵያ እስከማስወጣት እንዳሳሰባት ጨምሮ ተገልጾዋል፡፡
በበርካታ ወንጀሎች የሚጠየቁት ኪርና ማቻር ማስፈራራሪያውን
በቀላሉ እንደማይመለከቱት መገመት የሚቻል ሲሆን በሌላ በኩል ኢህአዴግ ወንጀል በመሥራትና በማሰራት አገር ውስጥ
የለመደውን የማጠልሸት ዘዴ በጎረቤት አገሮችም ላይ በመጠቀም የበላይነቱን መግለጹ ስምምነቱን “የሰላም ድርድር ወይስ
ቁማር?” ተብሎ እንዲጠየቅ የሚያስገድድ መሆኑን አንዳንድ ወገኖች ያስረዳሉ፡፡
ሱዳን ትሪቢዩን በበኩሉ ሳልቫ ኪርን ጠቅሶ እንደዘገበው ስምምነቱ
በማስፈራራትና በተጽዕኖ የተካሄደ መሆኑን ዘግቧል፡፡ “ጠ/ሚ/ሩ ለሬክ ሲነግረው ስምምነቱን ዛሬ ሳትፈርሙ ከዚህ
አትወጡም ብሎት ነበር ለእኔ ደግሞ ሰነዱን ካልፈረምክ አስርሃለሁ” በማለት አስፈራርተዋቸው እንደነበር ሳልቫ ኪር
መናገራቸውን ዘግቧል፡፡ ሳልቫ ኪር ከሬክ ማቻር ጋር ፊት ለፊት ተገናኝተው ምንም ዓይነት ውይይት ሳያደርጉ ለፊርማ
ብቻ መተያየታቸውንም ተናግረዋል፡፡
የሃይለማርያም ደሳለኝ እውነተኛ ባለሥልጣንነትና ተጽዕኖ አድራጊነት የታየበት ይህ ስምምነት በኢህአዴግ ውስጥ በምን ዓይነት መልኩ እንደሚቀጥል የሚያወያይ እንደሆነ አስተያየት ተሰጥቶበታል፡፡
አስተያየቱን ከሰጡ መካከል እንዳሉት “ሃይለማርያም ይህንን ማስፈራሪያ ሲሰጡ በአጠገባቸው የነበሩት የህወሃት
ባለሥልጣናት እነማን ይሆኑ በማለት በዓይነ ልቦናዬ ሳስብ ነበር፡፡ እነ በረከት፣ ደብረጽዮን፣ … ሳልኳቸው” የሚሉት
አስተያየት ሰጪ ሲቀጥሉ “ጠ/ሚ/ሩ በነካ እጃቸው የሕዝብን ድምጽ የሚያፍኑትን፣ ኦሮሞውን በየቦታው እየገደሉ ደሙን
የሚጠጡትን፣ አማራውን ለዘመናት ከኖረበት እያፈናቀሉ መሄጃ ያሳጡትን፣ አኙዋኮችን ያረዱትን፣ ኦጋዴኖችን ያጋዩትን፣
ተናገራችሁ፣ ጻፋችሁ በማለት እስርቤት እስኪጠብ ሃሳቡ የገለጸውን ሁሉ ለስቃይና ስደት የዳረጉትን፣ … ወንጀለኞች
እንዲሁ ግፋችሁን ካላቆማችሁ ቃሊቲ ወይም ዝዋይ ወይም … እወረውርሃለሁ ብለው አንዴ እንኳን በማስፈራራት ጠ/ሚ/ር
መሆናቸውን ቢያሳዩን ብዬ ተመኘሁ” ብለዋል፡፡
በተጽዕኖና ማስፈራሪያ የተፈረመው የደቡብ ሱዳን ስምምነት ፊርማ
ገና ሳደርቅ ሁለቱም ወገኖች ተኩስ አቁሙን ጥሰው ፍልሚያቸውን ቀጥለዋል፡፡ እርስበርስም እየተካሰሱ ይገኛሉ፡፡ እሁድ
ዕለት የሳልቫ ኪር ኃይሎች በከባድ መሣሪያ የታገዘ የምድር ጥቃት እንደሰነዘሩባቸው የማቻር ኃይሎች ይናገራሉ፡፡
የኪር መንግሥት በበኩሉ ማቻር ስምምነቱን ላለመፈረም በመፈለግ ተቃውሞ ሲያሰማ የነበረ ነው በማለት ዶ/ር ሬክ
ማቻርን ይከስሳሉ፡፡
ማቆሚያ የሌለው የሚመስለውና እስካሁን በሺዎች የሚቀቆጠር
ህይወትን የቀጠፈውና ለ1.2 ሚሊዮን ዜጎች መፈናቀል ምክንያት የሆነው ጦርነት ወደ ሰላም የመድረሱ ምኞት እየራቀ
የሄደ ይመስላል፡፡ ኢህአዴግ ማስፈራሪያ፣ ዛቻ፣ ቁማር፣ … ቢጠቀምም ህልሙ ቅዠት ሆኖበታል፡፡
ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (http://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡
በምእራብ ወለጋ የምትገኘው የጊምቢ ከተማ ነዋሪዎች በ አምቦ ከተማ በተገደሉት ኢትዮፒያዊያን በመበሳጨት በትናንትናው እና በዛረው እለት የመንግስት መሪያ ቤቶችን እና ባንኮችን አቃጥለዋል።
Residents in Gimbi town,
Wollega, have burned down banks and government offices in reaction to
the TPLF regime's massacre of students in Ambo.
Gimbi

Ambo

Gimbi
Ambo
Thursday, May 1, 2014
ሰበር ዜና በጎንደር ተኩሱ ቀጥሏል በግጭቱ እስካሁን 6 ሰው ሞቷል.
ፖሊስ በነዋሪዎቹ ላይ የወሰደው እርምጃ ያስቆጣው የጎንደር ህዝብ በቁጣ የአጸፋ እርምጃ እየወሰደ እንደሆነ
ከጎንደር የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ በፖሊስ እርምጃ የተቆጡ ወጣቶች የፖሊስ መኪና በመሰባበር ላይ ናቸው
ተብሏል፡፡ ህዝቡ በነቂስ እየወጣ ግጭቱ እየተባባሰ መሆኑንም ምንጫችን ጠቅሷል።
ጎንደር ከተማ ውስጥ ቀበሌ 18 ልዩ ቦታቸው አርምጭሆ ሰፈር፣ ገንፎ ቁጭና ህዳሴ የተባሉ ሰፈሮች የከተማው
አስተዳደር ‹‹ህገ ወጥ ሰፈራ ነው፡፡›› በሚል ለማፍረስ መዘጋጀቱን ተከትሎ አፍራሾቹ ከህዝብ ጋር በፈጠሩት ግጭት
ከ6 በላይ ሰዎች ሲሞቱ በርካቶች መቁሰላቸውንና መታሰራቸውን ከቦታው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ ግጭቱ ከሶስት
ሰዓት እስከ አራት ሰዓት ተኩል ድረስ ቀጥሎ የነበር ሲሆን ምንጫችን ደውሎ በሚነግረን ወቅት (6፡ 43) ተኩስ
እንደነበር ለመረዳት ችለናል፡፡
የአካባቢው ነዋሪዎቹ ሚያዝያ 7/2006 ዓ.ም ቤታቸውን እንዲያፈርሱ ትዕዛዝ በተላለፈበት ወቅት ህገ ወጥ
አለመሆናቸውን፣ ካልሆነም መንግስት ቅያሬ ቦታና ጊዜ መስጠጥ እንዳለበት በመግለጽ አንለቅም ብለው እንደነበር
ይታወቃል፡፡ በዛሬው ቀን ግጭቱ የተነሳውም አፍራሾቹ እንዲፈርሱ የተወሰነባቸውን ቤቶች ቀለም በመቀባታቸውና ህዝቡም
እንዳይቀቡ በመከልከሉ መሆኑ ታውቋል፡፡
በግጭቱ ፖሊስ፣ ፌደራልና ልዩ ኃይል የተሳተፈበት ሲሆን ከተገደሉትና ከቆሰሉት በተጨማሪ የአካባቢውን ወጣቶች ላይ
ድብደባና እስራት እየፈጸሙባቸው እንደሆነ ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ ‹‹ወጣቶችን እንደ እንሰሳ በአንድ
ገመድ አስረው እየደበደቧቸው ነው፡፡ ህዝብ በጅምላ እየታሰረ ይገኛል፡፡ ግጭቱ ቢያቆምም በአሁኑ ወቅት በሶስቱም
ሰፈሮች ጥይት እየተተኮሰ ነው›› ያሉት የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች የተወሰደው እርምጃ የጎንደርን ህዝብ በማስቆጣቱ
ከዚህ የባሰ ግጭት እንዳይፈጠር ያሰጋል ሲሉም ገልጸውልናል፡፡ በግጭቱ ወቅት የመጀመሪያዋ የሞት ሰለባ የሆነችው ልዩ
ኃይል ቤቷ እንዲፈርስ ቀለም ሲቀባ የተቃወመች የልጆች እናት እንደሆነችም ታውቋ፡፡
ፖሊስ በነዋሪዎቹ ላይ የወሰደው እርምጃ ያስቆጣው የጎንደር ህዝብ በቁጣ የአጸፋ እርምጃ እየወሰደ እንደሆነ ከጎንደር
የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ በፖሊስ እርምጃ የተቆጡ ወጣቶች የፖሊስ መኪና በመሰባበር ላይ ናቸው ተብሏል፡፡
ህዝቡ በነቂስ እየወጣ ግጭቱ እየተባባሰ መሆኑንም ምንጫችን ጠቅሷል
ምንጭ - የሰማያዊ ፓርቲ ልሳን ''ነገረ ኢትዮጵያ'' ዛሬ በድረ-ገፅ እንዳሰራጨው
Posted 8 hours ago by Getachew Bekele
Subscribe to:
Posts (Atom)