Wednesday, August 13, 2014

ከወያኔያዊ ምርጫ በፊት የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ሊያሰጋ ይችላል ሲሉ ዲፕሎማቶች ተናግረዋል።

August 13/2013
በምእራብ ኢትዮጵያ ለኩምሩክ ድንበር አቅራቢያ ጦርነት ተካሄደ።
ምንሊክ ሳልሳዊ

ወያኔ ራሱን ለማንገስ ከሚጠራው ምርጫ በፊት በኢትዮጵያ እና በኤርትራ ድንበር አከባቢዎች ጦርነት ሊካሄድ ይችላል ሲሉ በኢትዮጵያ የሚኖሩ ዲፕሎማቶች ተናግረዋል።በተለያዩ አጋጣሚዎች የተነሱ የሳተላይት ፍቶዎች በማስረጃነት በመጥቀስ ይህን ሰሞን በአዲስ አበባ ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ከአፍሪካ ህብረት ሰዎች እና ከአከባቢው የፖለቲካ አዋቂዎች ጋር የተለያዩ ስብሰባዎችን የሚያካሂዱት ዋናው የዚሁ ጦርነት ስጋትና አከባቢው ላይ ብሄራዊ ጥቅማቸው ላይ ምን ሊከሰት ይችላል የሚለውን በመገምገም ላይ መሆናቸው ታውቋል።

ዲፕሎማቶቹ የአሜሪካ መንግስት የሲአይኤን ሪፖርት ተከትሎ በትራንስፖርት ቢሮአቸው አማካኝነት በሰሜን ኢትዮጵያ የአየር በረራ የሚከለክል ደንብ ማስተላለፉ ይታወቃል፡፤ የዚህ ጉዳይ ዋነኛ ምክንያት ደሞ አከባቢው ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ መሆኑና በጦርነት ቀጠና የተመዘግበ ድንገት ጦርነት ይነሳል የሚል ግምት የተወሰደበት መሆኑ በአከባቢው ከፍተኛ የሆነ ከባድ መሳሪያዎች ታንኮች እና ብረት ለበስ አውዳሚ የጦር መሳሪያዎች የተከማቹ በመሆኑ ጦርነት አይቀሬ ስለሆነ በቋፍ ላይ ባለ የጦርነት ቀጠና ላይ አየር ማብረሩ ስጋት እንደሆነ ይናገራሉ፡፤ስለዚህ እንደ ዲፕሎማቶቹ እምነት ከወያኔያዊው ምርጫ በፊት የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ያስጋል።

በምእራብ ኢትዮጵያ በቤንሻንጉል ጉምዝ ወደ ድንበር ከተማው ኩምሩክ አክባቢ በግምት 50 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ከሚገኘው የወያኔው መከላከያ ሰራዊት ካምፕ አቅራቢያ በሰራዊቱ እና ከደቡብ ሱዳን ሰርገው ገብተዋል በሚባሉ ሃይሎች መካከል የ3 ሰአታት ጦርነት መካሄዱን አንድ የምእራብ እዝ መኮንን በላኩልኝ መረጃ ገልጸዋል።

ወታደሮቹ በክምፑ አከባቢ ቅኝት በሚያደርጉበት ጊዜ ድንገት የመጡ ሰርጎቦች የተባሉ ሃይሎች አከባቢውን በመውረር ከባድ ጉዳት ያደረሱ ሲሆን 26 የመከላከያ ሰራዊት አባላት ሲግደሉ በርካቶች ቆስለዋል። በዚህ የሰአታት ጦርነት እንደ መኮንኑ አባባል ከተዋጊዎቹ ወገን ጥልው የሸሹት ሁለት ሬሳ ብቻ ነው ብለዋል።

Tuesday, August 12, 2014

እውነት አብርሃ ደስታ አሸባሪ ነው? (ክብሮም ብርሃነ-መቐለ)

August12/2014
ነሐሴ 1 ቀን 2006 ዓ.ም የአረና ትግራይ ፓርቲ ስራ አስፈፃሚና የመቀሌ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምህር አብርሃ ደስታ በሽብር ተጠርጥሮ በተከሰሰበት ልክ በወሩ ፍ/ቤት እንደሚቀርብ በፌስ ቡክ አይቼ እኔም እንደ ዜጋና እንደ አድናቂው የሚቀርቡለትን የድራማ ክስ ለመስማት ጓጉቼ ፍ/ቤቱ ስደርስ እንደ እኔ አብርሃ ደስታን በአይናቸው ለማየትና የክሱን ድራማ ለማወቅ እንዲሁም ለቆራጡ ወጣት ፖለቲከኛ አብርሃ ደስታ የሞራል ድጋፍ ለመስጠት የተሰባሰቡ የተለያዩ የክልላዊና ሀገራዊ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች፣ አባላት፣ ጋዜጠኞችና ብሎገሮች እንዲሁም የወጣቱ ፖለቲከኛ አድናቂዎች ሽማግሌዎችና ወጣቶች ተደማምረው ያልገመትኩት የሕዝብ ብዛት በቡድን በቡድን ሰብሰብ ብለው የአብርሃ ቆራጥነትና የሀገራችን የፖለቲካ ሁኔታ ሲወያዩ አገኘኋቸው፡፡
የክሱን ሁኔታ ለመመልከት የመጡ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች
1. የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ(አንድነት) ተቀዳሚ ም/ፕሬዚዳንት አቶ ተክሌ በቀለ
2. የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ(አንድነት) ም/ፕሩዚዳንት አቶ በላይ ፍቃዱ
3. የሰማያዊ ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንት አቶ ስለሺ ፈይሳ
4. የመድረክ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጥላሁን እንደሻው
5. የጌድኦ ሕዝብ ዴሞክራስያዊ ፓርቲ ፕሬዝዳንት ኣቶ ኣለሳ መንገሻ እንዲሁም ጋዜጤኞች፣ ብዙ የታወቁ ሰዎችና ወጣት አድናቂዎቹ ተገኝተዋል፡፡
አብርሃ ደስታ ወደ ፍ/ቤት ሲገባ
አብርሃ ወደ ፍ/ቤቱ ግቢ ከመድረሱ በፊት ቁመቱ ትንሽ ረዘም ያለ የፊቱ ቀለም አብርሃን የሚመስል አንድ የትግራይ ተወላጅ ደህንነት (ለራሱ ያልዳነ) ከኋላው ሶስት ጠመንጃ ያነገቡ የፌዴራል ፖሊስ አስከትሎ ሲገባ አብርሃ ደስታን ለማየት ጓጉቶ የነበረ የአዲስ አበባ አድናቂዎቹ ‹‹ መጣ ……. መጣ…….. ›› ማለት ጀመሩ፡፡ ደህንነቱና የፌዴራል ፖሊሶቹ ልክ እንደገቡ ፊታቸውን ከሰል አስመስለው “ገለል በሉ …. ዞር በሉ ……!” እያሉ ትዕዛዝ ስለሰጡ ራቅ ብለን ተሰለፉ ሳንባል ፊታችን ወደ ዋናው መንገድ አድርገን ራሳችን ተሰለፍን
አንድ የፌዴራል ፖሊስ ከፊቱ ሆኖ እየመራው አብርሃ በኢትዮጵያ ሕዝብ፣ በሙስሊሙና በክርስቲያኑ ያለውን የመልካም አስተዳደር እጦት እንዲሁም የፖለቲካ ጣልቃ ገብነትና አፈና ለመግለጽ ቀለም የሚያንጠባጥብ ብዕር መያዝ ብቻ የለመዱ እጆቹ በብረት ሰራሽ ካቴና ክርችም ብሎ እልህ የሚነበብበት ፊቱ ጠቆር ብሎ፣ ሰውነቱ ከሳ ብሎ ሁለት የፌዴራል ፖሊስ አስከትሎ ገባ፡፡ ልክ ሙሽራ ሲመጣ እንደምናደርገው አቀባበል ወደ ፍ/ቤቱ ግቢ እንደገባ ያ ሁሉ ሕዝብ ግቢውን በጭብጨባ ቅውጥ አደረገው ያኔ አብርሃ ደስታ ግራ ገባው፡፡ ያ ሁሉ ሰው በሰልፍ ቆሞ ሙሽራ እንደመጣ ሲያጨበጭብ ይሆናል ብሎ ስላልጠበቀ መሰለኝ ጭብጨባው ለራሱ አልመሰለውም፡፡ አንድ ሁለት እርምጃ እንደሄደ ቀና ብሎ ሲያይ ብዙ የሚያውቃቸው ሰዎች ሲያይና ‹‹ አይዞህ!……. አይዞህ!……. አብርሃ የኛ ጀግና! ከጎንህ ነን! ›› እያሉ እጃቸውን እያወዛወዙ ሰላምታና ሞራል ሲሰጡት ለሱ መሆኑን ሲያውቅ ፊቱን ፈገግ በማድረግ የታሰሩ እጆቹን ከፍ በማድረግና ከወቡ ጎንበስ በማለት በተደረገለት አክብሮትና ሞራል የጨዋ ምላሽ እየሰጠ ወደ ችሎቱ ገባ፡፡
የግቢውን በር ከረገጠበት ጀምሮ ችሎት እስከሚገባ ድረስ ባለማቋረጥ በኃይለኛ ጭብጨባ ታጀበ፡፡ ያኔ ይዞት የመጣው ደህንነት በጣም ስለበሸቀ ‹‹ ስነስርዓት አድርጉ!…. ስነስርዓት አድርጉ!…. ›› ቢልም ሀሳቡ ስነስርዓት የሚያሲዝ ስላልነበረ መሰለኝ ጆሮ የሚሰጠው አልነበረም፡፡ አስከትሎም ምንም እንኳ በግልጽ ለማን መሆኑ ባይታወቅም “ቆይ አሳይሃለሁ!…. ኋላ ይቆጭሃል!…. ” እያለ ማስፈራራት ጀመረ፡፡ ይህን የሚገልጽ አንድ የትግርኛ አባባል አለ፡፡ ምን ይላል መሰላችሁ “ሰበይቱያ ዝለአኸቶስ ደገአፍ ቤተመንግስቲ አይፈርሕን ” በአማርኛም እንደዚህ “ሚስቱ የላከችው ሞት አይፈራም ” ይባላል፡፡ ያ ያልዳነ ድህንነትም ያመነው ነገር ባይኖር ህግ ባለበት ሀገር ደህንነት በመሆኑ ብቻ እንዲህ ብሎ ሰው ማስፈራራት አይችልም ነበር፡፡
“ቆይ አሳይሃለሁ!… ኋላ ይቆጭሃል!….” ማለቱ አንተም በሽብር ከስሼህ አሰቃይሃለሁ ማለቱ ይሆን?
በነገራችን ላይ አብርሃ ወደ ፍርድ ቤት ይቀርባል ተብሎ የተቀጠረው በ8፡00 ሰዓት ነበር፡፡ አብርሃን ለማየት የተሰበሰበ የሕዝብ ቁጥር አላምር ስላላቸው መሰለኝ ምናልባት ተሰላችተው ይሄዱ ይሆናል በሚል ታሳቢ እስከ 10 ሰዓት ከ25 አላቀረቡትም ነበር፡፡ ሕዝቡም ይሄን ተረድቶ እስከ 12 ሰዓትም ቢሆን እንቆያለን ብሎ በመረጋጋቱ እንደማይሆንላቸው አውቆ 10 ሰዓት ከ25 ሲል ነው ያመጡት፡፡ ይህ ግን በአብርሃ ብቻ ሳይሆን በእነ ሀብታሙ አያሌውም እንዲህ ተደርጓል፡፡ የሆነው ሆኖ ከግማሽ ሰዓት የችሎት ቆይታ አብርሃ እንደገና ታጅቦ ከችሎት ወጣ፡፡ ሲወጣም እንደገና ቅልጥ ያለ ጭብጨባና ሞራል ሲሰጠው ፈገግ እያለ አፉ ባይናገርም በታሰሩ እጆቹ አይዟችሁ እያለ እጅ እየነሳ ወጣ፡፡
የአብርሃ ደስታ ክስ በፖሊስ ሲነበብ
አብርሃ ችሎት ከገባ በኋላ አጠገቡ የነበረው በሙያውና በስነምግባሩ የታወቀ እንዲሁም ከብር ይልቅ ለፍትህ ቅድሚያ የሚሰጥ ጠበቃው ተማም አባቡልጉ ብቻ ነበር፡፡ ኋላ ግን ሁለት የአረና አመራርና አንድ የአክስቱ ልጅ ገብተው የክሱን ሁኔታ እንዲከታተሉ ስለተፈቀደላቸው ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ተከታትለዋል፡፡
አጠቃላይ የክሱ ጭብጥ
1. አረና ትግራይ ሽፋን በማድረግ ከግንቦት 7 አመራሮች እየተገናኘና ገንዘብ እየተቀበለ ሽብርን ለመፍጠር ተንቀሳቅሷል፡፡
2. ሽብር ለመፈጸም 60 ሰዎች መልምሏል፡፡
3. በቤቱ ሽብር ለመፈጸም የሚያስችል ዶክመንት በፍተሻ ተገኝቷል የሚሉ ነበሩ፡፡
መቼም ቢሆን አብርሃ ደስታ ይህን የፈጠራ ክስ ፈጽሞት ይሆን? ብሎ የሚጠራጠር ካለ የዘመኑ በጣም የዋህ ወይም የህወሓት/ኢህአዴግ መሰሪ ሴራና ተንኮል የማያውቅ ብቻ ነው፡፡ አብርሃ ህወሓት የሚፈጽማቸውን አፈናዎችና የህግ ጥሰቶች በየቀኑ ለኢትዮጵያ ሕዝብ እያሳወቀ በመሄዱና ሕዝብ በጽናት ታግሎ በሚቀጥለው ምርጫ ከትከሻው አሽቀንጥሮ መጣል እንዳለበት በድህረ ገጾችና በመጽሔቶች እየጻፈ ለብዙ ወጣቶች አርአያ እየሆነ በመሄዱና የትግራይ ሕዝብ የህወሓት ክህደትን አውቆ ለዳግም ሰላማዊ ትግል በሁሉ አቅጣጫ እንዲነሳሳ ማድረጉ ለህወሓት ትልቅ የራስ ምታት ስለሆነበት ነው እንጂ አብርሃ ደስታ የተከሰሰበትን የፈጠራ ክስ እንደማይፈጽምና እንዲህ አይነት ተልካሻ ስራ በሚወዳት ሀገሩና በሚወደው ሕዝብ ላይ ለመስራት የሚያዘው ጭንቅላት እንደሌለው አብርሃን በቅርበት የሚያውቁት ሁሉ ይመሰክሩለታል፡፡
አብርሃ ደስታ ለፍ/ቤቱ ካቀረባቸው አቤቱታዎች
1. በጣም ቀዝቃዛና ጨለማ በሆነ ቤት ብቻውን እየታሰረ እንዳለ
2. ፍ/ቤት እስከቀረበበት ጊዜ 8 የተለያዩ ግለሰቦች ከለሊቱ ከ7 እስከ 8 ሰዓት በየተራ እየመጡ እንደሚደበድቡት
(እንደሚያሰቃዩት)
3. በጭለማ ቤት ሆኖ የማያውቀውንና ያላነበበውን ጽሑፍ (ዶክመንት) እየተደበደበ እንዲፈርም እንደተደረገ
4. የቆየ የጨጓራ ህመም ስላለው እንጀራ ብዙም እንደማይማይበላና ሆኖም ግን አሁን ያለ ፍላጎቱ እያመመው እንዲበላ ስለተገደደ በከፍተኛ የጨጓራ ህመም እየተሰቃየ እንዳለ፣ በማዕከላዊ (ታስሮ ባለበት ቦታ) በሚደረግለትን የህክምና ዕርዳታ ሊያገግም እንዳልቻለ እነዚህና ሌሎች እየደረሱበት ያሉ ስቃዮች ምንም እንኳን ሰሚ ባያገኝም በአቤቱታ መልክ አቅርቧል፡፡
የተከበራችሁ አንባቢዎች እውነት አብርሃና መሰሎቹ ሽብርን ለመፈጸም በተጨባጭ መረጃና ማስረጃ ተይዞ ከሆነ እመኑ እየተባሉ ያ ሁሉ መደብደብ፣ መሰቃየትና ሳያነቡ ጽሑፍ እንዲፈርሙ መደረጉ ለምን አስፈለገ? የተገኘ እውነተኛ መረጃ ለሕዝብ ግልጽ አይደረግም? ፍርዱን ሕሊና ላለው ሰው ይሁን፡፡
በጠበቃው ተማም አባቡልጉ የቀረበ ክርክር
አንድ ሰው በወንጀል ተጠርጥሮ ሲየዝ በቂ የሆነ መረጃና ማስረጃ መኖር አለበት (ሕገ መንግስት እያጣቀሰ) አለበለዚያ ሰውን አስረህ ፖሊስ መረጃና ማስረጃ ላሰባስብ ጊዜ ይሰጠኝ ስላለ ብቻ ከበቂ በላይ ጊዜ እየተሰጠ ሰው ማሰቃየት ከህግ በላይ መሆን ነው፡፡ ወይም ሰው በእምነቱ እንዳይጓዝ ለመገደብ የሚደረግ ህገ መንግስቱን የጣሰ አካሄድ ነው፡፡ ስለዚህ አሁንም ፖሊስ ከዚህ ቀደም በቂ ጊዜ ተሰጥቶት እያለ ትርጉም ያለው መረጃና ማስረጃ ሊያቀርብ ስላልቻለ አሁንም እንደገና ጊዜ ይሰጠኝ ብሎ መጠየቁ ደንበኛዬ ከስራው ለማስተጓጎልና ለማሰቃየት ካልሆነ ሌላ ዓላማ ስለሌለው ደንበኛዬ የዋስ መብቱ እንዲከበርለትና በዋስ ተፈትቶ ክሱን በውጭ ሆኖ እንዲከታተል ይወሰንልኝ ብሎ ህገ መንግስቱን ተንተርሶ ተከራክሮዋል፡፡ ግን ምን ዋጋ አለው ከሳሹና ፈራጁ አንድ በሆነበት ሀገር ፍትህ እንዴት ይገኛል? ድሮም እኮ ፍትህ ቢኖር በፈጠራ ክስ ሰው አይከሰስም ነበር፡፡ እንዲህ ስለሆነ እንደገና ከ28 ቀናት በኋላ ነሐሴ 29 ፍርድ ቤት ይቀርባል ተባለ፡፡
በዛን ቀን የታዘብኩት ነገር
ህወሓት/ኢህአዴግ በቋንቋ፣ በብሔርና በጎጥ ከፋፍሎ ሲገዛን የራሱና ለራሱ ብቻ የሚሆን ምክንያት አለው፡፡ ነገር ግን ያን ቀን የታዘብኩት ነገር ካለ በህወሓት/ኢህአዴግ ሴራ ኢትዮጵያዊነታችን አሁንም ጨርሶ እንደማይናድ ነው፡፡ ምክንያቱም ህወሓት/ኢህአዴግ አብርሃን መቐለ ይዘው አዲስ አበባ ፍ/ቤት ሲያቀርቡት የፍርድ ሂደቱን የሚከታተል ብዙ ሰው ስለማይኖር የአብርሃ ሞራል ይጎዳል ብለው ይሆንናል፡፡ ነገር ግን የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችን እኩል አይቶ በእኩል የሚቆረቆር፣ ከግላዊ ጥቅምና ክብር የሕዝብ ጥቅምና ክብር የሚያስቀድም እንዲሁም የሀገርና የሕዝብ መብትና አንድነት ይከበር ብሎ በፅናት በአደባባይ የሚከራከር ኢትዮጵየዊ ከየትኛውም ብሔር ወይም ክልል ይምጣ፣ የፈለገውን ቋንቋ ይናገር በኢትዮጵያውያን ዘንድ የተለየ ክብርና ሞገስ እንዳለውና ሁሌም ኢትዮጵያውያን ከጎኑ እንደሆኑ በደንብ ተረድቻለሁ፡፡ አሳሪዎቹም ጭንቅላት ካላቸው ሳይረዱት አይቀርም፡፡ እንዴት ብትሉኝ አብርሃ የትግራይ ተወላጅ ኢትዮጵያዊ ቢሆንም ህወሓት/ኢህአዴግ እርስ በእርሳችን በጥላቻ አይን ከመተያየት አልፈን እንዳንተባበር የሚያደርጋቸውን የተለያዩ ሴራዎችን ሰብሮ የአብርሃ ጉዳይ የሁላችን ጉዳይ ስለሆነ ያሳስበናል ብሎ ብሔር፣ ቋንቋ እንዲሁም የህወሓት/ኢህአዴግ የመከፋፈል ሴራ ሳይገድባቸው የትግራይ፣ የአማራ፣ የኦሮሞና የደቡብ ተወላጆች ኢትዮጵያውያን በአንድነት የግል ስራቸውን ትተው የወጣት ፖለቲከኛና መምህር አብርሃ ደስታ የፍርድ ሂደት ሲከታተሉ መዋላቸውና ከፍተኛ ሞራል መስጠታቸውን ሳይ ኢትዮጵያዊነታችን በህወሓት/ኢህአዴግ ሴራ ጨርሶ እንደማይሸረሸር አረጋግጫለሁ፡፡ በኢትዮጵያዊነቴም ኩራት ይሰማኛል፡፡ አሁንም ገዢዎች በሚያደርጉት ሴራ እኛ ኢትዮጵያዊያን መለያየትና መቀያየም የለብንም፡፡ ለጋራ ዓላማና ጥቅም በጋራ መንቀሳቀስ አለብን፡፡ ስንተባበር ክንዳችን ይጠነክራል ሞራላችን ከፍ ይላል፡፡
ቸር እንሰንብት!
አንድ ቀን የፍትህና የነፃነት ባለቤቶች እንደምንሆን አልጠራጠርም!
ምንጭ – ፍኖተ ነጻነት
ፎቶ ቅንብር በኩሪ ሃገሬ

ኢንጅነር ይልቃል የአውሮፓ ህብረት እርምጃ እንዲወስድ አሳሰቡ

August 12/2014
ዛሬ ነሃሴ 6/2006 ዓ.ም በኢትዮጵያ ተወካይ ያላቸው 20 የአውሮፓ ህብረት አባል አገራት ተወካዮች በተገኙበት አዲስ አበባ በሚገኘው የአውሮፓ ህብረት ቢሮ ስለ ኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ እንዲያስረዱ የተጋበዙት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት የአውሮፓ ህብረት ኢትዮጵያ ወደባሰ ችግር ሳትገባ እርምጃ ሊወስዱ እንደሚገባ አሳሰቡ፡፡

የአውሮፓ ሉዑካን ኃላፊ የሆኑት ሚስስ ባርባራ በመሩት ስብሰባ ላይ የተገኙት ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት በአሁኑ ወቅት ገዥው ፓርቲ ስለሚያደርገው አፈና፣ ሰብአዊ መብት ረገጣ፣ በሚዲያው ላይ ስለሚወሰደው እርምጃ፣ ስለታሰሩትፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞችና ጦማሪያን አስረድተዋል፡፡ ኢንጅነር ይልቃል ስለ ኢህአዴግ ሁኔታ በተጠየቁበት ወቅትም ‹‹ኢህአዴግ በራሱ ችግር፣ በርዕዮት ዓለም መደናበር፣ በአመራር ብቃት ማነስ ምክንያት ምርጫውን ክፍት በማድረግ ዴሞክራሲን መፍቀድ ዋጋ እንዲሚያስከፍለው ያውቃል፡፡ በሌላ ኩል ምርጫን ማጭበርበርም ጣጣ እንደሚያመጣበት ተረድቷል፡፡ በመሆኑም ምርጫ ማጭበርበርም ሆነ ምርጫውን ክፍት ማድረግ ችግር እንደሚፈጥርበት ስለሚያውቅ ከወዲሁ አፈናን መርጧል›› ሲሉ አስረድተዋል፡፡

በተጨማሪም ኢንጅነር ይልቃል ‹‹በቀጠናው ባላችሁ ጥቅም ምክንያት ኢህአዴግን እየደገፋችሁ፣ ህግና ባህላዊ መሰረት የነበረበት አገር ወዳልሆነ አቅጣጫ እያመራች ነው›› ብለዋል፡፡ ኢንጅነሩ አክለውም ‹‹ኢህአዴግን ስለምትደግፉ፣ ወጣት ኢትዮጵያውያን ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞችና ጦማሪያን ሲታሰሩና ህዝብ አማራጭ እንዲያጣ ሲደረግ ዝም በማለታችው የኢትዮጵያ ህዝብ የኢህአዴግ እንጅ የኢትዮጵያ ወዳጅ አድርጎ አያያችሁም፡፡›› በሚል በህብረቱ አባላት ተወካዮች ላይ ወቀሳ አቅርበዋል፡፡ የህብረቱ አባላት ‹‹ምን እናድርግ?›› በሚል ላቀረቡላቸው ጥያቄ ‹‹ምን ማድረግ እንዳለባችሁ እናንተም ታውቁታላችሁ፡፡ ሙጋቤ ላይ ከወሰዳችሁት እርምጃ መካከል ትንሹን እንኳ ኢህአዴግ ላይ ብታደርጉት ትልቅ ለውጥ ማምጣት ትችሉ ነበር፡፡ ኢትዮጵያ የህብረቱ መቀመጫ በመሆኗ፣ በአፍሪካ ቀንድም ወሳኝ አፈርና ለቀይ ባህርም ያላት ቅርበት ለዓለም ደህንነት ከዚምባብዌ በላይ ጠቃሚ አገር ነች፡፡ ኢትዮጵያ ቀውስ ውስጥ በመግባቷ የእናንተም ብሄራዊ ጥቅም ጭምር ነው ችግር ውስጥ የሚገባው፡፡ በመሆኑም ለኢትዮጵያውያንም ለራሳችሁም ሲባል ኢትዮጵያ የባሰ ችግር ውስጥ ከመግባቷ በፊት አንድ እርምጃ መውሰድ አለባችሁ፡፡›› በሚል እርምጃ እንዲወስዱ አሳስበዋል፡፡

(ሰበር ዜና) ፍትህ ሚ/ር የክስ ቻርጆችን ለሃገር ቤት ጋዜጠኞች ማደል ጀመረ (የሎሚ መጽሔትን የክስ ቻርጅ ይዘናል)

Augest12/2014
(ዘ-ሐበሻ) ቀድሞ በኢትዮጵያ ያሉትን መጽሔቶችን እና ጋዜጦችን እንደሚከስ ያስታወቀው የሕወሓት አስተዳደር ፍትህ ሚ/ር ለጋዜጠኞች የክስ ቻርጆችን ማደል ጀመረ። በዛሬው ዕለት የሎሚ መጽሔት ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ግዛው ታዬ እና ድርጅቱ ዳዲስሞስ ኢንተርቴይመንትና የፕሬስ ሥራዎች ኃ/የተ/የግል ማህበር የክስ ቻርጅ እንደደረሰው ለዘ-ሐበሻ የመጣው መረጃ አመለከተ።
ጋዜጠኛ ግዛው ታዬ
ጋዜጠኛ ግዛው ታዬ
በተመሳሳይ እንደሚከሰሱ የተነገራቸው የአዲስ ጉዳይ ጋዜጠኞች ሃገር ጥለው ለመሰደድ የበቁ መሆኑን ዘ-ሐበሻ በትናንትናው ዕለት መዘገቧ ይታወሳል።
በሎሚ መጽሔት አዘጋጅ ላይ የሕወሓት አስተዳደር ፍትህ ሚ/ር ያቀረበው ክስ “ተከሳሾች በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን ወንጀሉና ወንጀሉ የሚሰጠውን ውጤት በመቀበል መንግስት የሚለወጠው ህገ መንግስታዊ በሆነ መርህ በምርጫ ሆኖ እያለ ኢ-ህገመንግስታዊ በሆነ መንገድ በአመጽ ሥርዓቱን ለመጣል” የሚል ሲሆን ለክስ ያበቁት ጽሁፎችም
1ኛ. በሎሚ መጽሄት ቅጽ 3 ቁጥር 109 “በዓለም በጨቋኝነቷ አቻ የማይገኝላት የሚዲያ ምህዳር በኢትዮጵያ” የሚለው
2ኛ. ሰብ አዊ መብት የሚባል በኢትዮጵያ መንግስት ሙሉ በሙሉ ተረስቷል። የምንገኝበትም ዓለም በመራጮችና የለውጥ ማዕበሎች የሰፈነበት በመሆኑ ኢትዮጵያውያን በቀጣይ ዓመት በሚደረገው የአገራዊ አጠቃላይ ምርጫ በመንተራስ ለበርካታ ዓመታት ከዘለቀ የፍ የጭቆና አገዛዝ ለመላከክ የማይቀረውን የለውጥ ማዕበል ለማምጣት እራሳቸውን ለተጠናከረ ሕዝባዊ ዓመጽ ማደራጀት መጀመራቸው ሊበረታታ የሚገባው ነው” በሚል አረፍተ ነገር፤
3ኛ. በሎሚ ቁጥር 91 ላይ “የአሸባሪነት ፈርጦች” በሚል ር ዕስት ‘ኢህ አዴግም ከማን አንሼ በሚል ስሜት ተቃራኒ ሃሳብ የሚያቀርቡ ጋዜጠኞችን ለስልጣኔ/ወንበሬ) ያስገኛል የሚላቸውን ጠንካራ ተቃዋሚዎችን እያደነ በአሸባሪነት ስም ወህኒ ያወርዳቸው ከጀመረ ሰንብቷል በሚል ጽፏል በሚል
4ኛ.”የኢሕአዴግ የሽብርተኝነት መመዘኛ ምንድን ነው?” “ኢህአዴግ” የሕዝብ ተቀባይነት ያገኘ አይመስለውም ሕዝብ የተቀበለውና አምነዋለው የሚለው ሰው ለኢህ አዴግ ጠላት ነው፤ ሽብርተኛ ተብሎ ይከሰሳል በማለት በሽብር ህግ ተከሰው የተቀጡ ተከሳሾች በህዝብ የሚወደዱና ለገዢ ፓርቲ ተቀናቃኝ በመሆናቸው ብቻ በግፍ የተቀጡ ንጹሃን እንደሆኑ የሚያስመስል ጽሑፍ አቅርቧል በሚል 4 ክሶች ቀርበውበታል።
የክስ ቻርጆቹን ተመልከቷቸው፤ ተጨማሪ መረጃዎች እንደደርሱን እንመለሳለን።
feteh Lomi 1
feteh Lomi 2
feteh Lomi 3

Sunday, August 10, 2014

‹‹አያ ጅቦ ሳታመኻኝ ብላኝ›› በበፍቃዱ ሃይሉ (ከቂሊጦ እስር ቤት)

August 10/2014

10425046_735506299828810_9070794374192798618_n[ከመቶ ሰባት ቀናት እስር በኋላ በፍቄ ሰለ እስሩ ስለ ምርመራው እና ስለ ወደፊት ተስፋቸው ከቂሊጦ እስር ቤት የሰደዳት መልዕክት ይቺትና። እኔ ጽሁፉን ሳነብ የመጣብኝ ሃሳብ እነዚህ ሰዎች በርካታ ንጹሃንን እስከዛሬ ማንም ሳያያቸው ሲያሰቃዩ የስቃዩ ሰለባዎች ዘጋቢዎች እና ጋዜጠኞች ካልሆኑ የስቃያቸውን መጠን የሚገልጹት በእንባ እና... ''ተወው... ተወው አይነሳ...'' በሚል ምሬት ብቻ ነበር። አሁን ግን በራሳቸው ጊዜ ዘጋቢዎችን ወደ ማዕከላዊ እያስገቡ እነሆ የኢህአዴግ ''አመራር ጥበብ''ን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ሰዕላዊ መግለጫ እየሰጡን ነው።
ኢህአዴግ ሆይ፤ በጥፊ በርግጫ አይገኝም ምርጫ፤ እያልን የበፍቄን ጽሁፍ ሁሉም ሰው ያነበው ዘንድ ይሄው...
‹‹አያ ጅቦ ሳታመኻኝ ብላኝ›› በበፍቃዱ ሃይሉ.
‹‹ታዲያ ጥፋቴ ምንድን ነው ትላለህ?!››፣ ብሎኛል አንዱ መርማሪዬ ስለዞን ዘጠኝ እና እኔም እራሴ እንደጦማሪም እንደአራማጅ ተራማጅም ሠራሁ የምላቸውን ነገሮች ዝርዝር ነግሬው ሳበቃ፡፡ በኋላ ላይ በእስር ቤት ቋንቋ ከ‹‹አባሪዎቼ›› ጋር መገናኘት ከተፈቀደልን በኋላ ስንጠያየቅ ለካስ ሁላችንም ይቺኑ ጥያቄ ተጠይቀናል፡፡ ይኼ ነው እንግዲህ የምርመራችንን ሒደት የሚገልፀው ጥያቄ፡፡ ‹‹ተጠርጥረን›› የተያዝንበትን ጉዳይ የሚያረጋግጥ ሥራ ሠርተን ባለመገኘታችን (ወይም ‹‹ባለመናገራችን››) ታዲያ ጥፋትህ ምንድን ነው? ተባልን፡፡ ምርመራው የኛን ነፃ መሆን አለመሆን ለማጣራት ሳይሆን ጥፋት ለማግኘት ነበር፡፡ ብዙዎች ‹መንግሥት ዞን ዘጠኝን ለምን ሁለት ዓመት እንደታገሠው› ግራ በመጋባት ይጠይቃሉ፤ ባሕሪው አይደለምና፡፡ የኢትዮጵያ ሀሳብን የመግለጽ ነጻነት ምኅዳር በቀላሉ እንደገመቱት ተይዘን፣ ተመርምረንና ‹‹ተገኘባችሁ›› የተባልነው ‹‹ የግንቦት 7 [እና ኦነግም ጭምር] አባልነት [ብሎም ግብ አስፈጻሚነት] ›› በሽታ ለተከሳሽነት አብቅቶናል፡፡ ቀጣዩ የክርክር ሂደት ነው፡፡
ከዚያ በፊት ግን ዞን ዘጠኝን በሩቅም በቅርብም የሚያውቁ በግራ መጋባት መልስ እንደሚሹ በማሰብ ይቺን አጭር ማስታወሻ ለመጻፍ ተገድጃለሁ፡፡ የእስራችን ሂደት ምን ይመስላል? የምርመራችንስ? እውን የግንቦት ሰባት አባል ነን? [ታዲያ] ለምን ታሰርን? በቅርቡ እንፈታ ይሆን?
ደቂቅም ይሁን ሊቅ ስለኢትዮጵያ ፖለቲካዊ እውነታ የሚጽፍ ማንኛውም ሰው [ኢትዮጵያ ውስጥ ሳለ] አንድ ቀን እታሰር ይሆን እያለ መስጋቱ አይቀርም ፡፡ ለዚህም ይመስለኛል ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም በአንድ መጽሐፋቸው ላይ ሰው ነገረኝ ብለው የኢትዮጵያ ሕዝብን በሦስት የመደቡት፡- የታሰረ፣ ታስሮ የተፈታ እና ወደፊት የሚታሰር በማለት፡፡ እርግጥ ዞን ዘጠኝ ‹‹ሐሳቡን መግለጽ ፈርቶ ዝም ያለ ሁሉ እስረኛ ነው›› ብሎ መደምደም ሦስቱም ምድብ አንደኛው ውስጥ ያጠቃልለዋል ‹‹የታሰረ›› በሚል፡፡ ዞን ዘጠኞች ጦማራችንን በከፈተን በሁለት ሳምንት ሲታገድብን እና ሌላ ስንከፍት ግና መጨረሻ ላይ ታጋቾቹ እኛ እንደምንሆን እናውቅ ነበር፡፡ ያንን የሚያረጋግጥ ተደጋጋሚ የደህንነቶች ክትትል እና ምልክቶች ስለደረሱን መታሰራችን ማስደንገጡ ባይቀርም ያልተጠበቀ ግን አልነበረም፡፡
እስሩ በክትትሉ የተገኘነውን ስድስት የዞን ዘጠኝ አባላት እና ሦስት ጋዜጠኛ ጓደኞቻችንን መሆኑን በተለይ የጋዜጠኞቹ [ቢያንስ ለእኛ] ያልተጠበቀ ነበር ማለት ይቻላል፡፡ የኋላ ኋላ ስንመለከተው ግን በእኛ አስታኮ እነሱንም ማሰሩ የታሰበበት ዘመቻ እንደሆነ መገመት አይከብድም፡፡ እኛን በቁጥጥር ስር የማዋሉ ሒደትም ቢሆን በቅጡ የታሰበበት ነበር ሁላችንም (ከአስማማው በቀር) ከቀኑ በ11፡00 ገደማ በያለንበት ስንያዝ አስማማው በማግሥቱ ታስሯል፡፡ ሌሎቻችን ቤታችን በሚፈተሸበት ሰዓት ሕጉ የሚፈቅድበት ሰዓት(12፡00) አልፎ ነበር፡፡ በቁጥጥር ስር ካዋሉን በኋላ የሕገ-ወጥ አያያዝ ሰለባ የመሆናችን ሂደት የሚጀምረው ከዚህ ነው፡፡

Friday, August 8, 2014

Breaking News: Redwan Hussein confronted By Ethiopians at M





አቶ ሬድዋን ሁሴን በቨርጂኒያ ውርደት ገጠመው፤ ኢትዮጵያውያኑ ልክ ልኩን ነገሩት (ቪዲዮ)

ስንታየሁ ከሚኒሶታ

አቶ ሬድዋን ሁሴን ለሆዱ ያደረ በአራዳ ቋንቋ ‘ችስታ የወያኔ ተላላኪ’ መሆኑን ያሳየው ዛሬ ነው። በአርሊንግተን ቨርጂኒያ። አሜሪካን ውስጥ “ችስታ” ወይም ገንዘብ መቋጠር ከፈለክ የተራረፉ ልብሶችን የምትገዛበት ሱቅ ማርሻልስ ነው። የኬቨን ኪለር፣ ባናና፣ ቦስ፣ ናይኪ፣ አዲዳስ፣ ቶሚ፣ ኤክስፕረስ እና ወዘተ ታዋቂ የልብስና ጫማ አምራች ድርጅቶች በመደብሮቻቸው በሰዎች ልክ (ሳይዝ) የሰሯቸው እቃዎች ወደ ማለቂያ (ፋሽናቸው ሲያልፍ) የሚልኩት ወደ ማርሻልስ ስቶር ነው። ባጭሩ ማርሻልስን በሃገርኛ “ምናለሽ ተራ” ልትሉት ትችላላችሁ።
redwon Hussein አዜብ መስፍን አሜሪካ ስትመጣ ጆርጅ ታውን ወርዳ በጣም ውድ የሆኑ ሱቆች ገብታ በ$10 ሺህዎች የሚቆጠሩ ዶላሮችን ታፈሳለች – የሰረቀችው ስላላት። ቴዎድሮስ አድሃኖም ከደሃው ሕዝብ ከሰረቀው ገንዘብ ቀነስ አድርጎ ኒውዮርክ ላይ ጄ ፕሬስ ቡቲክ ገብቶ በሺዎች ዶላሮች ለልብሶቹ አፍሶ ይወጣል። ታይም ስኩዌር ሄዶ ፎቶ ይነሳል። ተላላኪው ሬድዋን ሁሴን ግን ‘ቺፕ’ ብለው አሜሪካውያን በሚጠሩት ማርሻል የተራረፈ ልብስ ገዝቶ ይወጣል:: ዛሬ የሆነውም ያ ነው። ሰውዬው አሜሪካ መጥቶ አዲስ አበባ ላሉት ባለስልጣኖች ከአሜሪካ የገዛሁት ልብስ ብሎ ለማሳየት ከአሜሪካው ምናለሽ ተራ ሱቅ ልብስ ሊገዛ ገብቶ ተዋርዶ ተመለሰ። ኢትዮጵያውያኑ ተጋፈጡት። ሌባ መሆኑን፤ ገዳይና የገዳይ አገልጋይ መሆኑንም የፊቱ ቆዳ የሳሞራ የኑስን ልብስ እስኪመስል ድረስ ነገሩት።
እንደለመደ አፉን አይከፍት ነገር ያለው አሜሪካ ሆነበት፤ እንዳይደነፋ ኢቲቪና መቀሱ የሉም። ውርደቱን ከኤክስፕረስ በታላቅ ቅናሽ የገዛውን ሰማያዊ ልብስ እንደለበሰ ተከናንቦ ተመለሰ። ወይ ሬድዋን፤ አዜብ ጆርጅ ታውን፣ ቴዎድሮስ ጄፕሬስ ሲገበያዩ አንተ ቺስታና ሆድ አደር ስለሆንክ በማርሻል ውርደትህን አከናነቡህ አይደል? ገና ምን አይተህ? ኢትዮጵያውያኑ የሳሞራ የኑስን ልብስ እንዲመስል ያደረጉልህ ቆዳህ ገና ወደ የት እንደሚሄድ አብረን እናየዋለን።
ሬድዋንን የተጋፈጡትን ብርቱ ኢትዮጵያውያንን እያደነቁ፤ የወያኔ ተላላኪዎችን የማወረዱ ሥራ እንዲቀጥል አደራ እላለሁ። ቪድዮውን እነሆ።

|