Monday, June 30, 2014

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በየመን ባለሥልጣናት እገታ ላይ መሆኑን በማስመልከት የወጣ መግለጫ

2665272d78511e341383257989
June 30, 2014
አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በየመን ባለሥልጣናት እገታ ላይ መሆኑን በማስመልከት የወጣ መግለጫ
ሰኔ 23 ቀን 2006 ዓ.ም
የግንቦት 7፣ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ሰኔ 16 ቀን 2006 ዓም ለሥራ ጉዳይ በየመኒያ አየር መንገድ አይሮፕላን ተጉዞ በትራንዚት ሰንዓ ከተማ እያለ በየመን መንግሥት ፀጥታ ኃይሎች በሕገወጥ መንገድ ታግቷል። አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የመን የጉዞው መዳረሻ አልነበረም፤ ከየመን ጋርም የሚያገናኘው ምንም ጉዳይ አልነበረውም። የየመን መንግሥት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን አግቶ ለአንድ ሰዓት እንኳን ለማቆየት ምንም ምክንያት የለውም። በዚህም ምክንያት ያለአግባብ የታገተብን የንቅናቄያችንን አመራር በአስቸኳይ እንዲፈታ በተለያዩ መንገዶች ላለፈው አንድ ሣምንት ያደረግነው ጥረት እስካሁን አልተሳካም። እንዲያውም የየመን ባለስልጣናት አምባገኑን ወያኔ ለመርዳት ባለው ፍላጎት ሳቢያ መሪያችንን አሳልፎ ሊሰጠው ይችላል የሚል ከፍተኛ ስጋት አድሮብናል።
አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ፣ በሀገራችን በኢትዮጵያ ውስጥ ፍትህ፣ ነፃነትና ዲሞክራሲ እንዲሰፍን ጊዜውን፣ እውቀቱንና ጉልበቱን ብቻ ሳይሆን ሕይወቱን አሳልፎ ለመስጠት የተዘጋጀ፤ ዝግጁነቱንም በተግባር ያሳየ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ ነው። የየመን መንግሥት ከዘረኛውና ፋሽስታዊው ወያኔ ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ታጋይ መሪያችን ላይ እየፀመ ያለውን ደባ የጉዳዩ ባለቤት የሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲያውቅ የንቅናቄዓችን ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ወስኗል።
ትግላችን መስዋትነት እንደሚያስከፍል እናውቃለን። ከዚህ በፊትም ብዙ ጓዶቻችን መስዋዕትነት ከፍለዋል፤ ወደፊትም ብዙ መስዋዕትነት መከፈሉ የማይቀር ጉዳይ ነው። አሁን በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ የደረሰውና ወደፊትም ሊደርስ የሚችለው ጉዳት ምሬታችን በማብዛት፣ ቁጣችንና ዝግጁነታችን ከማጠንከር በስተቀር ቅንጣት ታክል እንኳን ወደ ኋላ እንድናፈገፍግ እንደማያደርገን ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ ለአባሎቻችንና ለደጋፊዎቻችን ሁሉ መግለጽ እንወዳለን።
መንግሥታት ይመጣሉ፣ ይሄዳሉ። ኢትዮጵያና የመን ግን ጎረቤታሞች ሆነው መቆየታቸው የማይቀር ነው። የየመን መንግሥት የወያኔ እድሜ አጭር መሆኑ የተገነዘበ አይመስልም። በዚህም ምክንያት የየመን መንግሥት የሁለቱን አገሮች ሕዝቦች የቆየ ወዳጅነት የሚያደፈርስ እርምጃ ወስዷል። የየመን መንግሥት የየመንን የወደፊት የረዥም ጊዜ ጥቅም እንዲያሰላና ያገተብንን መሪ በአስቸኳይ እንዲፈታ እንመክራለን። ይህ ሳይሆን ቀርቶ በመሪያችን ላይ ጉዳት ቢደርስ ወይም ለወያኔ አሳልፎ ቢሰጥ የመን ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር የማይሽር ቂም ውስጥ የምትገባ መሆኑን የየመን መንግሥት አውቆ በጥብቅ እንዲያስብበት እናስጠነቅቃለን።
በየመን መንግሥት አልሰማ ባይነት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ለፋሽስቱ የወያኔ አገዛዝ ተላልፎ ቢሰጥ በአካሉና በሕይወቱ ለሚደርሰው ሁሉ የወያኔ ፋሽስቶችን ዋጋ የሚያስከፍል መሆኑ ከአሁኑ እናስጠነቅቃለን። በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ አካል፣ መንፈስና ሕይወት ላይ የሚደርሰው ማንኛውም ጥቃት ለነፃነታቸው ለመሰዋት ዝግጁ የሚሆኑ እልፍ አዕላፍ ታጋዮችን እንደሚፈጥር ጥርጥር የለንም። በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ አካል፣ መንፈስ እና ሕይወት ላይ ለሚደርሰው ጥቃት ሁሉ በማንኛውም መንገድ በማንኛውም ቦታ የምንበቀል መሆኑንና ብዙ የወያኔ ሹማምንት ዋጋ የሚከፍሉበት እንደሚሆን እንዲያውቁት እናስጠነቅቃለን ።
በመስዋዕትነት ድልን እንቀዳጃለን።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!
http://www.ginbot7.org/wp-content/uploads/2014/06/Press-release-Andargachew.pdf

የትግራይ ልጆች ሚስጥሩን እያወጡት ነዉ የመለስን ማንነት Abraha Desta

“በርሀ ሻዕብያ” In My Mind
==================
በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት ነው። ሻዕብያ ኢትዮጵያን ለመወረር ዝግጅቱ ማጠናቀቁ እየታወቀ፣ ራሳችንን ለመከላከል መዘጋጀት እንዳለብን እየተነገረ ዝምታ መረጥን። አምባሳደር አውዓሎም ወልዱ (በኤርትራ የኢትዮጵያ አምባሳደር) የሻዕብያን ዝግጅት ለኢትዮጵያ መንግስት ያስተላልፍ ነበር። ገብሩ አስራት፣ ስየ አብርሃና ሌሎች ለመለስ ዜናዊ ይነግሩት ነበር። መለስ ግን ዝምታ መረጠ። ሳንዘጋጅ ተወረርን። የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ፈርሶ ስለነበር ምልሻዎች፣ ፖሊሶችና የቀድሞ ታጋዮች ሙሉ ዝግጅት ሳያደርጉ ወደ ጦር ግንባር ተላኩ። ሻዕብያ ጨረሳቸው። ባጭር ግዜ ብዙ የኢትዮጵያ ወጣቶች ዳር ድንበራቸው ለማስከበር ቆርጠው ተነሱና የሻዕብያን ኃይል ደመሰሱ። መሬታችንን በደማቸው አስመለሱ። ለሀገራቸው መስውእት ከፈሉ። ክብር ይገባቸዋል።
ሻዕብያን ከደመሰሰ በኋላ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ዓሰብን መቆጣጠር ይችል ነበር። ዓሰብን እንዳይቆጣጠር ተብሎ እዛ አከባቢ የነበረ መከላከያ ሰራዊታችን በመለስ ዜናዊ ትእዛዝ እንዲመለስ ተደረገ። በተመሳሳይ ግዜ ‘በርሀ ሻዕብያ” በሚል ስም የሚታወቅ የኢትዮጵያ ወታደራዊ መኮነን 23ኛ ክፍለጦር ይዞ የሻዕብያን ወታደሮችን ደምስሶ የኢሳያስን መንግስት ለመደምሰስ አስመራ ለመግባት ጥቂት ኪሎሜትሮች ሲቀሩት “ተመለስ፣ የሌላ ሀገር መሬት አንወርም!” የሚል ትእዛዝ ተቀበለ።
በርሀ ሻዕብያ “አልመለስም” አለ። “ያ እብሪተኛው፣ ህፃናትን የጨፈጨፈ ወራሪ ኃይል የገባበት ገብቼ እደመስስና ወዳንተ እመለሳለሁ” (ሻዕብያ ደምሲሰ መልሰይ ናባኻ እየ) አለ። ወደ አሥመራ ሲገሰግስ የነበረ የበርሀ ሻዕብያ ክፍለጦር ፈተና እንዲገጥመው ተደረገ። ሆን ተብሎ በመለስ የተደረገ መሆኑ ነው። የበርሀ ክፍለጦር ሲመለስ ወታደሮቹ ጥቃት ተፈፀመባቸው። አለቁ። (ከነዚህ ሲመለሱ ካለቁ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት አጎቴ ይገኝባቸዋል)።
ይህን ሁሉ መስዋእት ከተከፈለ በኋላ የኢትዮጵያ ሰራዊት አሥመራን እንዳይገባ መከልከሉ ክፉኛ አዘነ። ተስፋ ቆረጠ። በርሀ ሻዕብያም ተመለሰ። ዓሰብም የሻዕብያ ወታደሮች በድጋሜ ተቆጣጠሩት። ብዙ ደም ከፈሰሰ በኋላ፣ ብዙ መስዋእት ከተከፈለ በኋላ ወደ ድርድር ተገባና መስዋእት የተከፈለበትን መሬት ለኤርትራ እንዲወሰን ተደረገ። ከጦርነት በኋላ ድርድር ብሎ ነገር አለንዴ?
ነገሮች ሁሉ ተገላበጡና በርሀ ሻዕብያም ተመለሰ። በርሀ ሻዕብያ ላደርገው አስተዋፅዖ ሽልማት ሲገባው የመለስ ዒላማ ሆነ። ከነ ሚስቱ ተገድሎ ተገኘ። ከዛ ‘ሚስቱ ከደለችው” አሉን። ይህን ሁሉ እንደሚፈፀም የሚያውቁ የመከላከያ ሰራዊት አባላት እንዴት ነፃ ይሁኑ?
በርሀ ሻዕብያን አደንቃለሁ። ለሀገር መስዋእት የሚሆኑ ይገደላሉ። ሀገር የሚሸጡ ደግሞ ይሸለማሉ፤ ፎቶአቸውን በየመስርያቤቱ ይለጠፋል። ጀግኖች ተሰዉ፤ ሌቦች ሀገር መሩ፣ ሀገር አጠፉ። እውነተኛው ታሪክ የሚጋለጥበት ግዜ ሩቅ አይሆንም።
ክብር ለሀገርና ህዝብ ደህንነት ለተሰዉ ጀግኖች!

በካድሬ የምትሾፈር ሀገር

ስንገጣጠም በካድሬዎቹ ፊት ላይ ድንጋጤና ንዴት የተቀላቀለበት ስሜት መታየት ጀመረ፡፡ከዚያም ያልተለመዱ እንቅስቃሴዎች ተከተሉ ሁሉም ካሜራውን አውጥቶ ፎቶውን ያንቀጫቅጨው ጀመር፡፡ እኛም ካድሬዎቹ እያደረጉት ያሉት የማስፈራራት ሙከራ መሆኑን አውቀን የደብረ ማርቆስ ከተማ የፓርቲያችን አመራር የሆነውን ወጣት ሳሙኤል አወቀን ጨምረን አጠገባቸው ወደነበረ ወንበር ሄደን ተቀመጥን፡፡ይሄኔ ቤቱ ሞቅ ባለ የጉንተላ ዘፈን ተነቃነቀ፡፡ሁሉም ከመቀመጫው ተነስቶ ወደ እኛ ባነጣጠረ መልኩ ‹‹ያቺን ጎፈሬ ዛሬ ነው ዛሬ›› እያለ ይውረገረግ ጀመር እኛም በነሱ ዘፈንና ፉከራ ስንዝናና ቆይተን ወደ ማረፊያችን ተመልሰን ገባን፡፡
እንደገባን ስልኬ ጠራ ሳሙኤል አወቀ ነበር የደወለው፡፡ካድሬዎቹ ዛሬ ሰማያዊዎች እዚች ሆቴል አያድሯትም እናስወጣቸዋለን እያሉ በሞቅታ ስሜት እየዛቱ መሆኑን ነገረኝ፡፡ጅብ በማያውቁት ሀገር ሄዶ……… እንዲሉ ከካድሬዎቹ ጋር በደንብ እንደምንተዋወቅና ደፍረው እንደማያደርጉት በመንገር ተሰናበትኩት፡፡የሚገርመው ካድሬዎቹ ወደ ክፍላችን አልመጡም ሊመጡም አይችሉም ምክንያቱም እኛ ሰማያዊዎች ነን፡፡እነሱም ይህን ጠንቅቀው ስለሚያውቁ ነው ዕኛ ከገባን በኋላ ይፎክሩ የነበረው፡፡
እናንተም ውረዱ እስከ ፈረፈሩ
እኛም እንወርዳለን እስከ ፈረፈሩ
እዛ ጋር ይለያል ፈሪና ደፋሩ
ብለን ለስለስ ባለ ሙዚቃ ጋደም ብለናል፡፡

Sunday, June 29, 2014

የቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ጥፋቱ ምንድን ነው?

መስፍን ወልደ-ማርያም
ሰኔ 2006 ዓ.ም
ቴዎድሮስ ካሣሁንን በአካል አላውቀውም፤  በዘፈንና በጭፈራ በእውነት ተደሳች መሆን ካቃተኝ ቆይቷል፤ ከ ኅዳር 1967 ጀምሮ ነው የቆረቆረኝ፤ ይህ ሰው እንደሰውና እንደ ኢትዮጲያዊ በየጊዜው የሚደርስበትን ወደ ግፍ የሚጠጋ በደል ስመለከት ያው የለመድነው ምቀኝነት ነው እያልሁ ሳልፈው ቆየሁ፤ ግን በደሉ አላቆም አለ፤ ማንም ሊደርስለት አለመቻሉ ይበልጥ ያሳዝናል፣ በእሱ ላይ ተከታታይ  የደረሰበት በደል የሕግ ያለህ የሚያሰኝ ነው፤ በቴዎድሮስ ካሣሁን ላይ በተቀነባበረ መንገድ የሚፈፀመው ማሰቃየት ማንንም ሰው የሚያሳስብ ነው፤ ምክንያቱ ምንድን ነው? በግልጽ የታወቀ ነገር የለም።
በቴዎድሮስ ላይ ከባድ ተንኮል ሲፈጸምበት የሰማሁት በመጀመሪያ ዛሬ በስደት ላይ ባለው « አዲስ ነገር» የሚባል ጋዜጣ ላይ ነበር፤ ጋዜጣው ቴዎድሮስ በሙያው ያገኘውን መልካም ስም በሰፊው ጥላሸት ቀብቶት ነበር፤ በጣም ሰፊ የሆነ ሀተታ በቴዎድሮስ ዘፈኖች ላይ በማቅረባቸው ምን ያህል አንገብጋቢ የአገር ጉዳይ አግኝተውበት ይሆን ብዬ አነበብሁት፣ ምንም ለአገር  የሚጠቅም ጉዳይ አላገኘሁበትም፤ በዘፈኖቹ ላይ በተደረገው ሂስም ከጋዜጠኞቹ መሀከል የሙዚቃ ሙያ ባለቤት እንዳለ ብጠይቅም ጋዜጣው ባለሙያ እንደሌለውና ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈለገ ባለሙያ ማማከራቸውን ነገሩኝ፣  ስሙ  እንዲጠቀስ የማይፈልግ ባለሙያ፣ ባለሙያ አይባልም፣ እንኳን በሙያው በራሱም አይተማመንም ማለት ነው፤ በዚህ በራሱ በማይተማመን ሰው ምስክርነት ላይ በተመሰረተ ረጅም ነቀፌታ ቴዎድሮስን ደበደቡት፤
ሁለተኛው የቴዎድሮስ ጣጣ በመኪና ሰው ገጭቷል ተብሎ መከሰሱ ነው፤ በሌሊት፣ በጨለማ ነው፤ ቴዎድሮስ እንደሚለው  «እኔ ወደአገሬ የገባሁት ሰውዬው ሞተ በተባለበት ቀን ማግስት እንደሆነ ቪዛዬ ያረጋግጣል፣»  (ነጋድራስ መስከረም 30/2001 ዓ.ም. ) በኋላም ከዳግማዊ ምኒልክ ሆስፒታል የተገኘው መረጃ ይህንኑ የሚያረጋግጥ እንደነበረ ተነግሮአል፤  በዚሁ በነጋድራስ ጋዜጣ ላይ የሚከተሉት መረጃዎች ተጠቅሰዋል ፦
  1. ቴዎድሮስ ከውጭ የተመለሰው በ22/2/1999 ዓ.ም መሆኑ
  2. ሰውዬው በ 22/1/1999 ሞቶ አስከሬኑ በ22/2/1999 ዓ.ም መመርመሩን የጽሑፍ ማስረጃ፣
  3. ዓቃቤ ሕግና ፖሊስ በሆስፒታሉ የተገለጸው የምርመራ ቀን እንዲለወጥ መጠየቃቸው፣
  4. ከአሥራ ሦስት ቀኖች በኋላ በተደረገ ምርመራ መኪናው ላይ ምንም ደም አለመገኘቱን፣
ይህ ሁሉ ሆኖ በቴዎድሮስ ላይ ተፈርዶበት ወህኒ ወርዶ ጊዜውን ጨርሶ ከወጣ ቆይቶአል።
ከዚያ ወዲህ ደግሞ በተቀነባበረ ሁኔታ ቴዎድሮስ ካሣሁን በዘፈኑ ያገኘውን ዝና ለማጉደፍና በሥራውም የሚያገኘውን ጥቅም ለመቀነስ ተግተው የሚሠሩ ሰዎች መኖራቸውን የሚያመለክቱ ነገሮች አሉ፣ በመጀመሪያ ቴዎድሮስ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የፈጸመው በደል ከአለ ግልጽ ሆኖ ቢወጣና ሁላችንም ብናውቀው ጥሩ ነው፤ አለዚያ ግን እየተደራጁ አንድ ግለሰብን ለማጥቃት የሚደረገው እርምጃ የሚወገዝና ልንቃወመው የሚገባ ጉዳይ ነው፣  አንድን ሰው በእምነቱ፣ በአስተያየቱ፣ ወይም ስኬታማነቱን በመመቅኘት ለመጉዳት ዓለም -አቀፋዊ ሴራ ማካሄድ ክፋት ነው፤ ይህንን ክፋት አምጠው የወለዱትና ለማሳደግ የሚሞክሩት ሰዎች፤ የማሰብ ችግር ያለባቸውና ክፋታቸው ተመልሶ እነሱኑ የሚያጠቃ መሆኑን የመገንዘብ ችሎታ  እንኳን የሌላቸው ናቸው።
ሦስተኛው የቴዎድሮስ ስቃይ የበደሌ ቢራ ፋብሪካ በቴዎድሮስ ዘፈን ለመጠቀም ሲፈልግ፣ የጨለማ ሰዎች ተሰብስበው በቴዎድሮስ ዘፈን የታጀበውን የበደሌ ቢራ እንደማይጠጡ በመዛታቸው ኩባንያው ከቴዎድሮስ ጋር የነበረውን ውል መሰረዙ ነው፤  እንደተገነዘብሁት ቴዎድሮስ ትንሽ በቁንጫ ተሰቃየ እንጂ ክፍያው አልቀረበትም፣ ነገር ግን ቴዎድሮስን አንደሰው፣ እንደኢትዮጵያዊ፣ እንደዘፋኝ የሚያውቁት ሰዎች የሉም፤ ወይም በጨለማዎቹ ሰዎች ተሸንፈዋል፤ ወይም በፍርሃት ቆፈን ደንዝዘዋል! የጨለማ ሰዎቹ ቴዎድሮስ ካለበት አንጠጣውም የተባለው ቢራ ለቴዎድሮስ ወዳጆች እንዴት ጣፈጣቸው?
አራተኛው የቴዎድሮስ ስቃይ የመጣው ሦስተኛውን ጥቃት ለመቋቋምና ለማረም ምንም ዓይነት የማረሚያ እርምጃ ስላልተወሰደ ነው፤ የበደሌ ቢራ ኩባንያ እንዳደረገው ሁሉ የኮካኮላ ኩባንያም ቴዎድሮስ ካሣሁንን ለአሻሻጭነት መረጠ፤  የጨለማዎቹም  ሰዎች እንደገና ተነሡ፤  ቴዎድሮስን ካልሻራችሁ ኮካ ኮላ አንጠጣም  ብለው የቴዎድሮስ ውል እንዲፈርስ አደረጉ፤  አሁንም ቁንጫው ትንሽ ምቾቱን ከመቀነሱ በስተቀር ቴዎድሮስ ገንዘቡን አላጣም፤ አሁንም የቴዎድሮስ ወዳጆች ነን የሚሉ ኮካ ኮላ እየጣፈጣቸው ይጠጣሉ፤ ትንሽ ቆራጦች የጨለማ ሰዎች  በአደባባይ ምላሱን እየሳለ እልል ከሚለውና ከሚጨፍረው ነፍሰ-ቢስ ስብስብ ምን ያህል እንደሚበልጡና ውጤታማ እንደሚሆኑ ያሳያል።
የቴዎድሮስ ካሣሁን ጉዳይ የአንድ ግለሰብ የሰብዓዊ መብት ጉዳይ ነው፤ የጨለማ ሰዎቹ ግን ወደግለሰብነት ደረጃ ገና ያልደረሱ ናቸው፤ ስለዚህም ቴዎድሮስን እንደሰው እንዳያዩት እዚያ ገና አልደረሱም፤ እንደኢትዮጲያዊ እንዳያዩት መናፍቃን ናቸው፤ እንደዘፋኝ እንዳያዩት ጆሮአቸው አይሰማም።
በአዲስ ነገር ተጀምሮ እስካሁን አልበርድ ያለው ቴዎድሮስን ነጥሎ የማጥቃት ዘመቻ ምክንያቱ ምንድን ነው? በጥሞና ሊታይና ሊመረመር የሚገባው በአዲስ ነገር ጋዜጣና በጨለማዎቹ ሰዎች መሀከል ያለ የሚመስለው ድርጅታዊ ግንኙነት ነው፤  የአንድ ግለሰብን ሰብዓዊ መብቶች እየደጋገሙ በመርገጥ አጋጣሚ እየፈለጉ ማጥቃት የሚጎዳው ተረጋጩን ብቻ ሳይሆን ረጋጮቹንና የጋን ወንድሞችንም ነው፤ አንድ ቀን ግፍ ወደተነሣበት ይመለሳል።
mesfinwoldemariam

ኢትዮጵያዊው-ኖርዌጂያን ኦኬሎ ኦካይ ኦቻላ ”ሞት ሊበየንበት ይችላል” -በሽብርተኝነት ክስ ሞት ተፈርዶባቸው ሞታቸውን የሚጠባበቁ 127 ሰዎች ኣሉ

በኖርዌይ ሃገር ውስጥ በኖርዌጂያንኛ የሚታተመው ዳግብላደት የተባለው ጋዜጣና ድረ-ገጽ ”ኢትዮጵያዊው-ኖርዌጂያን” ኦኬሎ ኦካይ ኦቻላ በሚቀጥለው ሳምንት ሞት ሊበየንበት ይችላል” ሲል ኣውጥቶኣል።
”ባለፈው ሳምንት ለማወቅ እንደተቻለው ዕድሜው 52  የሆነና  ኦኬሎ ኦካይ ኦቻ  የተባለ ኖርዌጂያን ኢትዮጵያ ውስጥ በሽብርተኝነት ተከሶ በእስር ላይ ይገኛል።” tiltalt for terror በማለት የጀመረው የኖርዌዩ ዳግብላደት ሲቀጥልም…”የኢትዮጵያ መንግስት ቃለ ኣቀባይ እንደሚለው ገንዘብ ኣሰባስቦና ኣጥቂ ቡድን መልምሎ ኣደጋ ለማድረስ ሲሞክር ያዝነው በማለት መከሰሱን ያትትና በበኩላቸው የኖርዌዩ የሰብኣዊ መብት ጥበቃም ሆኑ የዓለም ኣቀፉ ሰብኣዊ መብት ተሟጋቾች ድርጊቱን በጥብቅ ያወገዙት ሲሆን፣ ኣያይዘውም ለዚሁ ድረ-ገጽ ታሳሪው ግለሰብ ያለበት ሁኔታ ከወትሮው የከፋ እንደሆነም ስጋታቸውን እንደገለጹለት ያወሳል።
 ኢትዮጵያንም ሆነ የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት፣ በኣሁኑ ወቅት በማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ውስጥ የሚገኙትን  ኦኬሎ ኦካይ ኦቻ ”በሚገባ ያውቃሉ” ያሉዋቸውን የሰብኣዊ መብት ተሟጋችና ኖርዌጂያን ፈሊክስ ሆርነ ን  ኣነጋግሮ ድረ-ገጹ ያገኘው መልስ ”ኖርዌጂያኑን ኦኬሎ በሚቀጥለው ሳምንት የሚሰየመው ችሎት ሞት ሊበይንበት ይችላል” በማለት የገለጹ ሲሆን ኣክለውም፣
”በሃገሪቷ ውስጥ በሽብር ወንጀል የሚከሰሱት ዜጎች የሚገጥማቸው የሞት ፍርድ ነው። ነገር ግን እነዚህ ሞት የሚፈረድባቸው ዜጎች ምንም ማስረጃ ያልቀረበባቸው ናቸው። በሽብር ክስ ስለተከሰሱ ብቻ ዕድላቸው ይሄው ነው። በሞት ቀጠና የሚገኙትን ዜጎች የሚዘግበው ዓለም ኣቀፉ ድርጅት በኢትዮጵያ በእስር ቤት ውስጥ በሞት ቀጠና (ሴል) የሚሰቀሉበትን ወይም የሚገደሉበትን ጊዜ የሚጠባበቁ 127  ዜጎች  ይገኛሉ ሲል ፈሊክስ ሆርነ ለድረ- ገጹ ገልጸዋል።
 ሌላው ኣምነስቲ ኢንተርናሽናል ውስጥ የሚሰሩት ጌራልድ ካዶርድ ”የኢትዮጵያ መንግስት ኦኬሎን እንደከሰሰው በሽብር ወንጀል ጦር ሲመለምልና ሲያደራጅ ኣግኝቶት ከሆነ፣ የሞት ቅጣት ይበይኑበታል የሚለው ስጋቴ ነው።የፍርድ ሂደቱን እንደምናየው የሞት ቅጣቱ በፍርድ ቤቱ ይለወጣል የሚል ዋስትና የለንም።” ኣያይዘውም ባለፈው ዓመት 8 ጋምቤላ ውስጥ ያሉ የተቃዋሚ ድርጅት ኣባላቶች በሽብርተኝነት ከሰዋቸውና የሞት ፍርድ በይነውባቸው ሞታቸውን በመጠባበቅ ላይ ናቸው።”
 ጭፍጨፋ
ኦቻላ ከሽብርተኛ ጋር ግንኙነት እንዳለው ኣላውቅም። ነገር ግን በጋምቤላ ውስጥ መንግስትን የሚቃወም ጠንካራ ተቃዋሚ ድርጅት የለም። መንግስትን ለመቃወም የሚነሱትንም ሽብርተኛ የሚል ስም በክልሉ መንግስት ይለጠፍባቸዋል።
 ኦቻላ የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት የነበረ ጊዜ፣ massakre 13. desember 2003. የ 1000 በላይ  የኣባወራዎች መኖሪያ ቤቶች በገዥው ስርዓት ወታደሮች ሲቃጠልና ከ400 የኣኙዋክ ንጹሃን ተወላጆች በጥይትና በስለት ሲታረዱ በስፍራው  ነበር። ይሄንንም ተከትሎ ወደ ደቡብ ሱዳን ስልጣኑን በመተው መሰደዱንና ከዚያም ከቤተሰቡ ጋር  በኖርዌይ ”ትሮንዳሄም” በተባለ ቦታ  በስደተኝነት በመግባትና ፈቃድ ጠይቆ በ2009 ዓ.ም የኖርዌጂያን ዜግነት ተሰጥቶት ነበር።
  ቢሆንም  ከ 2012 ጀምሮ በጋምቤላ ውስጥ በሚከናወነው ሁኔታዎች ይረበሽ ነበር። በዚህም የተነሳ ወደዚያው ኣቅንቶኣል።ማድረግ ግን ኣልነበረበትም።በኣንድ ወቅት በክረምት ወራት የሱዳን የመረጃና ደህንነት ሰራተኞች በሱዳን ጁባ ውስጥ ያለን ኣንድ ሆቴል በድንገት ከበቡት። ከዚያም በውስጡ የነበሩትን የሱን ጓደኞች  ኣስረዋቸው ወደ ኢትዮጵያ  ልከዋቸዋል በማለት ድረ- ገጹ ኣትቶኣል።
ቶርቸር 
በኣሁኑ ሰዓት ኦኬሎ በእስር ቤት ውስጥ ባልተረጋገጠ መረጃ ውስጥ ይገኛል። ይህ ኖርዌጂያን በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ማወቅ ኣይቻልም።በኢትዮጵያ ውስጥ በሽብርተኝነት በእስር ቤት ውስጥ ሆኖ  የእናትነት እንክብካቤን ማግኘት ህልም ነው።እስረኞች ለቶርቸርና ስቃይ የተጋለጡ  መሆናቸውን ፈሊክስ ሆርነ  ለድረ-ገጹ ኣስረድተዋል።
የኦኬሎን የፍርድ ሁኔታ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኘው ሪፖርተር የተሰኘው  ጋዜጣ ችሎቱ  ጁላይ 1 ይውላል ብሎ ቢገልጽም፣ የእኛ Dagbaldet በሲዊድን ያለውን የኢትዮጵያ ኣምባሳደር ለማግኘት ሞክረን ያልተሳካልን ሲሆን፤ ዓለም ኣቀፉን የሰብ ኣዊ መብት ተሟጋች ድርጅትንም ሆነ በኣዲስ ኣበባ ካለውም የኖርዌይ ኤምባሲ ትክክለኛ የችሎት ጊዜውን ማረጋገጥ ኣልተቻለም።
የኖርዌይ የውጭ ጉዳይም ለኣንድ ኣዲስ ኖርዌጂያን በኣደጋ ውስጥ በሚሆንበት ጊዜ፣ ወይም ኣደጋ በገጠመው ወቅት እንዴት መከላከል  እንዳለበት ከድረ- ገጹ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ መስጠት ኣልፈለጉም።ድረ- ገጹ   ምላሽ በማጣቱም ይመስላል በኮንጎ ውስጥ ኖርዌጂያዊው Joshua French  በሞት ሲቀጣና፣  Shahid Azim  በኣስገድዶ መድፈር ወንጀል ፖኪስታን ውስጥ ተይዞ ሞት ሲፈረድበትም ኣላስጣሉትም በሚል ኣጣቅሰው ያለፉት። ቢሆንም ይላሉ የውጭ ጉዳይ ቃል ኣቀባይ ፍሮደ ኣንደርሰን፥ እስከኣሁን ከተከሳሹ ስለ ፍርድ ውሳኔውንም  ሆነ  ስለ ችሎቱ ቀን የምናውቀው የለም በማለት ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ ያለው የኖርዌይ ኣምባሳደር  ኦኬሎ ኦካይ ኦቻላን በተመለከተ ተደጋጋሚ  ጥያቄዎችን ለኢትዮጵያ መንግስት ኣቅርቦኣል። ኦኬሎ ያለበትን ሁኔታ፣ የፍርድ ሂደቱን ለመከታተልና በእስር ቤት ለመጎብኘት፣ ቢሆንም  ከኢትዮጵያ መንግስት ምንም  ምላሽ  ኣልተገኘም። የኖርዌይ የውጭ ጉዳይ ቢሮ ሁኔታውን በኣደገኛነት እንደሚያዩትም ሳይገልጹ ኣላለፉም።
ባለፈው ሳምንት  የኦኬሎ ባለቤት ኦባ ኦድዋ ኦመት kona Obo Adwo Omot fram i Dagbladet  ”… ባለቤቴ ሽብርተኛ ሳይሆን የፖለቲካ እስረኛ ነው” በማለት ገልጻ ነበር። ይህችው የ ኣራት ልጆች እናት የሆነችው ባለቤቱ ባለፈው ሳምንት እንደገለጸችው፣ ”…በኣሁኑ ሰዓት በዚህ ጠባብ ክፍል ከኣራት ልጆቼ ጋር እገኛለሁ። ምንም የማውቀው ነገር የለም። ባለቤቴም የሚያውቀው ነገር የለም። የኖርዌይ መንግስት የተቻለውን ሁሉ ኣድርጎ ባለቤቴን ከእስር እንዲያስወጡልኝ እማጸናለሁ በማለት ነበር የገለጸችው።