Monday, August 18, 2014

የወያኔው ኢንሳ በአዲስ መልክ የፌስቡክ ስም አጥፊ ፔጆችን/ገጾችን ሊያደራጅ ነው

August 18/2014
=================ነቢል አህመድ ዘገፈርሳ=====================
facebook
ወያኔ የኢትዮጵያን ሕዝብ አንድነት እና ነጻነት ለመሸራረፍ ብሎም ለመበታተን ከሚጠቀምባቸው ዘዴዎች አንዱ በማህበራዊ ድህረገጹ ያሰማራቸውን ከተቃዋሚ ሃይላት ጋር ተመሳስለው የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅት መስለው የተቃዋሚ ሃይሎችን ሎግ በመጠቀም እንዲሁም ለሽፋንነት በየመሃሉ የተቃዋሚ ድርጅቶችን መግለጫ እንደወሽመጥ በማስገባት በማታለል እና በማጭበርበር ላይ ተመስርተው ሲሰሩ የነበሩ ስም አጥፊ ገጾችን/ ፔጆችን በአዲስ መልክ ለማደራጀት በዚህ ሳምንት እረፍት እንዲወስዱ ያደረጋቸው መሆኑ ታውቋል።
ስም በማጥፋት ለውጥ ፈላጊ ሃይሎች በተለያዩ አክቲቪስቶች ላይ መጠራጠር እንዲያሳድሩ እና ጠቃሚ የተባሉ ጦማርያንን እንዲያጡ እና ትግሉ አቅጣጫውን እንዲስት በስፋት አዲስ የአሰራር ዘይቤ ለመቀየስ የተሳዳቢዎች የተዛልፊዎች እና የስም አጥፊዎች የማህበራዊ አካውንት እና ፔጆች እረፍት ላይ መሆናቸውን እና በተጠናከረ መልኩ ወደ ስራ እንደሚመለሱ በቅርብ የሚያውቋቸው ወዳጆቻቸው ተናግረዋል።
በዚሁም መሰረት በዜጎች መካከል ከባድ ጥርጣሬን ያጭራሉ የተባሉ የፈጠራ ጽሁፎች እና የሞቱ ሰዎች ፎቶዎችን በመጠቀም የተለያዩ የፌክ ወንጀሎችን በመጻፍ እንድሁም ከብልግና እና የሰውን ክብር ከሚያዋርዱ አዳዲስ ብካይ የሃሰት መረጃዎች ጋር ወዘተ ተያይዘው ወደ ማህበራዊ ድህረገጾች እርፍታቸውን ጨርሰው እንደሚመጡ ታውቋል።

Sunday, August 17, 2014

ጀግና እናውቃለን ማጀገንም እንደዛው አብሮነታችን ግን እስከየት ድረስ ነው?

August17/2014
Photo: ጀግና እናውቃለን ማጀገንም እንደዛው አብሮነታችን ግን እስከየት ድረስ ነው?

የ አብርሃ_ደስታ ጀግንነት ብርታትና ጥንካሬ በሶሻል ሚዲያ ላይ ብቻ የሚለካ አይደለም መከራውን ሲጋፈጥ እኛስ መሬት ላይ ምን እያደረግን ነው? አብርሃ ሲታሰር የበቀል ርምጃ የተወሰደባቸው ቤተሰቦቹም ጭምር ናቸው፣ ከመቐለ እዚህ ድረስ መከራን በማዕከላዊ እንዲቀበል ሲመጣ ቤተሰብም አብሮ ይጉላላል፣ ብዙም በማያውቁት ከተማ በዚህ የኑሮ ውድነት እኛ እያለን ለምንስ ይቸገራሉ ለምንስ ያስቸግራሉ?… የአንድ ሰው መታሰር የአንድ ሰው መታሰር ለሚመስላችሁና ሌሎች ለምን ለምን አልታሰሩም ለምትሉ ግብዞች ልብ ብላችሁ አድምጡኝ የአንድ ሰው መታሰር የቤተሰብ መታሰር ነው! አይደለም አንድ አብርሃ ብዙ ሺ አብርሃዎች መፈጠር የሚችሉት እነሱ ሲታሰሩ እኛ ከቤተሰቦቻቸው ጎን የምንቆም ከሆንና ብርታት መሆን ከቻልን በፕሮፓጋንዳ እንዲሸማቀቁ የተደረጉትን ቀና ብለው እንዲሄዱ ማድረግ ከቻልን የእነአብርሃ ደስታም ሆነ ሌሎች ቤተሰብ አስተዳዳሪዎችና ጧሪዎች እኛ መርዳት ከቻልንና ይረዱት የነበረው ቤተሰብ በሞራል የሚጠገን ከሆነ በቁስ የማይቸግረው ከሆነ ስለእውነት ለምንከፍለው መስዋዕትነት ኩራት እንጂ ሃዘን አይሰማንም፡፡ በደህንነቶች ክትትል ሰላም ለሚነሳችሁ፣ ሳታውቁትም በማታውቁት ጉዳይ ምንም ባልተፈጠረበት በደንባራነታቸው ላይ conspiracy ጨምረው እናንተን በመማገድ እንጀራቸውን ለመጋገር የሚታትሩ ጆሮ ጠቢዎች (ደህንነት ብዬ ከፍ አላረጋቸውም) ተቋቁማችሁ ላላችሁና ለተረበሻችሁ ማንም ባያውቅላችሁም ቅሉ በንጹህ ኅሊናችሁ፣ ሆድ አደሮቹ አንገታችሁን ሊያስደፉ ደስታችሁን ሊቀሙ ቢጥሩም ስለብርታታችሁ ምስጋና ይግባችሁ፡፡ በፖለቲካ አቋማችሁ የምታምኑት አጥታችሁ የሆዳችሁን በሆዳችሁ አድርጋችሁ በስጋት ላላችሁ አይዞን፡፡ ይህ መልዕክት አብርሃ ደስታን በምሳሌነት ያነሳ ይሁን እንጂ ስለ ዞን ዘጠኞች ማኅሌት_ፋንታሁን፣ በፍቃዱ_ኃይሉ፣ ዘላለም_ክብረት፣ ናትናኤል_ፈለቀ፣ አቤል_ዋበላ፣አጥናፍ_ብርሃነ ጋዜጠኞቹ አስማማው_ኃ_ጊዮርጊስ፣ ተስፋለም_ወ_የስ፣ ኤዶም_ካሳዬ፣ እስክንድር_ነጋ፣ ውብሸት_ታዬ፣ ርዕዮት_ዓለሙ፣ እንዲሁም እነአንዷለም_አራጌ በቀለ_ገርባ ን፣ ኦልባና_ሌሊሳን፣ ሃብታሙ_አያሌው፣ የሺዋስ_አሰፋ ፣ ዳንኤል_ሺበሺ ፣ ኢብራሂም_አብዱልሰላም፣ አደይ_አልጋነሸ_ገብሩ እና ስለ ሌሎችም ነው የእነዚህ ሁሉ ቤተሰቦች ቀና እንዲሉ አለንላችሁ እንበላቸው የኛም ቤተሰቦች የእነሱን ቤተሰቦች እንዲጠይቁ ብናድርግስ የለውጥ ጥማት አንድ ያደረገን ቤተሰቦች ነንና፡፡ እንደነ አብርሃ ጦር ሜዳ ካልገባን እኛ እንደራሳችን ደጀን እንሁናቸው፡፡ It is so!
የ አብርሃ_ደስታ ጀግንነት ብርታትና ጥንካሬ በሶሻል ሚዲያ ላይ ብቻ የሚለካ አይደለም መከራውን ሲጋፈጥ እኛስ መሬት ላይ ምን እያደረግን ነው? አብርሃ ሲታሰር የበቀል ርምጃ የተወሰደባቸው ቤተሰቦቹም ጭምር ናቸው፣ ከመቐለ እዚህ ድረስ መከራን በማዕከላዊ እንዲቀበል ሲመጣ ቤተሰብም አብሮ ይጉላላል፣ ብዙምበማያውቁት ከተማ በዚህ የኑሮ ውድነት እኛ እያለን ለምንስ ይቸገራሉ ለምንስ ያስቸግራሉ?… የአንድ ሰው መታሰር የአንድ ሰው መታሰር ለሚመስላችሁና ሌሎች ለምን ለምን አልታሰሩም ለምትሉ ግብዞች ልብ ብላችሁ አድምጡኝ የአንድ ሰው መታሰር የቤተሰብ መታሰር ነው! አይደለም አንድ አብርሃ ብዙ ሺ አብርሃዎች መፈጠር የሚችሉት እነሱ ሲታሰሩ እኛ ከቤተሰቦቻቸው ጎን የምንቆም ከሆንና ብርታት መሆን ከቻልን በፕሮፓጋንዳ እንዲሸማቀቁ የተደረጉትን ቀና ብለው እንዲሄዱ ማድረግ ከቻልን የእነአብርሃ ደስታም ሆነ ሌሎች ቤተሰብ አስተዳዳሪዎችና ጧሪዎች እኛ መርዳት ከቻልንና ይረዱት የነበረው ቤተሰብ በሞራል የሚጠገን ከሆነ በቁስ የማይቸግረው ከሆነ ስለእውነት ለምንከፍለው መስዋዕትነት ኩራት እንጂ ሃዘን አይሰማንም፡፡ በደህንነቶች ክትትል ሰላም ለሚነሳችሁ፣ ሳታውቁትም በማታውቁት ጉዳይ ምንም ባልተፈጠረበት በደንባራነታቸው ላይ conspiracy ጨምረው እናንተን በመማገድ እንጀራቸውን ለመጋገር የሚታትሩ ጆሮ ጠቢዎች (ደህንነት ብዬ ከፍ አላረጋቸውም) ተቋቁማችሁ ላላችሁና ለተረበሻችሁ ማንም ባያውቅላችሁም ቅሉ በንጹህ ኅሊናችሁ፣ ሆድ አደሮቹ አንገታችሁን ሊያስደፉ ደስታችሁን ሊቀሙ ቢጥሩም ስለብርታታችሁ ምስጋና ይግባችሁ፡፡ በፖለቲካ አቋማችሁ የምታምኑት አጥታችሁ የሆዳችሁን በሆዳችሁ አድርጋችሁ በስጋት ላላችሁ አይዞን፡፡ ይህ መልዕክት አብርሃ ደስታን በምሳሌነት ያነሳ ይሁን እንጂ ስለ ዞን ዘጠኞች ማኅሌት_ፋንታሁን፣ በፍቃዱ_ኃይሉ፣ ዘላለም_ክብረት፣ ናትናኤል_ፈለቀ፣ አቤል_ዋበላ፣አጥናፍ_ብርሃነ ጋዜጠኞቹ አስማማው_ኃ_ጊዮርጊስ፣ ተስፋለም_ወ_የስ፣ ኤዶም_ካሳዬ፣ እስክንድር_ነጋ፣ ውብሸት_ታዬ፣ ርዕዮት_ዓለሙ፣ እንዲሁም እነአንዷለም_አራጌ በቀለ_ገርባ ን፣ ኦልባና_ሌሊሳን፣ ሃብታሙ_አያሌው፣ የሺዋስ_አሰፋ ፣ ዳንኤል_ሺበሺ ፣ ኢብራሂም_አብዱልሰላም፣ አደይ_አልጋነሸ_ገብሩ እና ስለ ሌሎችም ነው የእነዚህ ሁሉ ቤተሰቦች ቀና እንዲሉ አለንላችሁ እንበላቸው የኛም ቤተሰቦች የእነሱን ቤተሰቦች እንዲጠይቁ ብናድርግስ የለውጥ ጥማት አንድ ያደረገን ቤተሰቦች ነንና፡፡ እንደነ አብርሃ ጦር ሜዳ ካልገባን እኛ እንደራሳችን ደጀን እንሁናቸው፡፡ It is so!

እንደገና ይድረስ ለሠራቱ

August17/2014
“የትግሬ” ነፃ አውጪ ነኝ ብሎ ራሱን የሠየመው የዘረኞችና የዘራፊዎች ቡድን አገሪቷን እያጎሳቆለ ያለው ከሠራዊቱ ጀርባ ተንጠላጥሎ መሆኑ ይታወቃል። ይህ የዘረኞችና የዘራፊዎች ቡድን የተሸከመውን ሠራዊት ሳይቀር በጉስቁልናና በድንቁርና እንዲኖር ፈርዶበታል። ህወሃት ሠራዊቱ እንዲማር፤ ዘመኑ ከሚፈቅደው የቴክኖሎጂ እውቀት ጋር ራሱን እንዲያዋህድ እና በራሱ የሚተማመን የዘመነ ሠራዊት እንዲሆን ፍላጎት የለውም።አሜሪካን በአገሯ በሚገኙ የጦር ትምህርት ተቋማት ውስጥ ወታዶሮችን ለማሰልጠን ፍላጎት ብታሳይም ሳሞራ የኑስና መለስ ዜናዊ እምቢ ማለታቸውን አብዛኛው የሠራዊቱ አባላት የሰሙት አይመስልም። አሜሪካን በሁለት ዓመት ውስጥ ብቻ 42 ወታደሮችን አገሯ ወስዳ ለማስለጠን በጠየቀች ግዜ ሳሞራ የፈቀደው 13 ወታደሮች ብቻ ሂደው እንዲማሩ ነው። እነዚህም ከህወሃቶች መካከል ፊደል የቆጠሩ ተፈልገው በመገኘታቸው መሆኑም ታውቋል። በሠራዊቱ ውስጥ የሚገኙ ሌሎች የትምህርት ዝግጅት ቢኖራቸውም የትምህርት እድሉን ተከልክለዋል።
ህወሃት ከራሱ ውጪ ያሉት ሌሎች ላይ ምንም ዕምነት እንደሌለው በተለያየ አጋጣሚ ተናግሮታል። የትምህርት ዕድሉን ለምን መጠቀም እንዳልፈለጉ ሲጠየቅ ሳሞራ የኑስ “ሌሎችን አናምናቸውም አሜሪካን ሂደው ይቀራሉ” ብሎ መልስ መስጠቱም ተመዝግቦ ይገኛል። 11ኛ ክፍልን ያልዘለለው የህወሃቱ ኢታማዦር ሹም ሳሞራ የኑስ ሠራዊቱን ታማኝና የማይታመኑ በሚል ይከፍላቸዋል። የህወሃት አባል የሆነ ወታደር ታማኝ ፤ ሌሎች የሠራዊቱ አባላት የማይታመኑ።
አሁንም የሠራዊቱ አባላት ስሙ !
እናንተ ምንም ያክል ጥሩ ዜጋ ለመሆን ብትጥሩ በህወሃቶች ዘንድ የምትታመኑ አይደላችሁም። ህወሃቶች ከእነርሱ ውጪ ባሉ ሌሎች ላይ ጥርሳቸውን እንደነከሱ እስከ ዛሬ አሉ። በሌሎች ዜጎች ላይ የመዘዙት የበቀል ሰይፍም ወደ ሰገባው የሚመለስ አልሆነም። በሁለት ዓመት ውስጥ 42 ወታደሮችን አሜሪካን ወደ አገሯ ወስዳ ለማስልጠን ብትጠይቅም 13ቱን ብቻ ተቀብለው 29ኙን አንፈልግም ማለታቸው የተመዘዘው የበቀል ሰይፋቸው አንዱ አንጓ መሆኑን የትምህርት ዕድሉን የተነፈገው የሠራዊቱ አባል ልብ ሊለው ይገባል። እነ ሳሞራ የኑስ ከእነርሱ ውጪ ያሉ ሌሎች ዜጎች በድንቁርናና በችጋር እየተሰቃዩ ይኖሩ ዘንድ ፈርደውበታል። በእንዲህ ሁኔታ እንዲኖር የተፈረደበት ሠራዊት፤ ውጪ አገር ሂዶ እንዳይማር የተከለከለ ሠራዊት፤ ዘር ሃረጉ እና ድርጅታዊ ታማኝነቱ እየታየ ለሹመት የሚበቃው የሠራዊት አባል ይህን ውስኔ ለወሰነበት ለመለስ ዜናዊ ፋውንዴሽን ከሚያገኛት ከወር ደመወዙ ላይ ቆርጦ እንዲከፍል ይደረጋል። እንዲህ ዓይነት በደል በየትኛውም አገር ታይቶ አይታወቅም።
በችጋር እንድትኖሩ ከምታገኟት ከወር ደመወዝችሁ ላይ ይወሰዳል፤ ተምራችሁ ራሳችሁን እንዳትቀይሩ በነፃ የሚገኘውን የትምህርት ዕድል እንኳ እንዳትጠቀሙ ተከልክላችኋል። በዚህ ሁኔታ እንድትኖሩ ከተፈረደባችሁ በኋላ የገዛ ወገኖቻችሁን ደም በከንቱ እንድታፈሱ ትደረጋላችሁ። የቀደመው ትውልድ በደሙ ያቆመው ድንበር ፈርሶ እና ዜጎች ተፈናቅለው መሬቱ ለባዕድ ሲሰጥ አናንተ ቁማችሁ ትመለከታላችሁ። ያ የሚፈሰው ደም የራሳችሁ ደም፤ ተፈናቅሎ ሜዳ ላይ የሚወድቀው የገዛ ወገናችሁ መሆኑን ለማሰብ እንኳ ነፃነት ያጣችሁ ትመስላላችሁ። የህፃን ደም በአዲስ አበባ ጎዳና ላይ ሲፈስ ለምን ስትሉ አልተሰማም፤ ጋምቤላዎች ለዘለዓለም ከኖሩበት መሬት ተፈናቅለው መሬታቸውን ሌሎች ሲቀራመቱት ይሄ አይሆንም ለማለት የያዛችሁት ነፍጥ የሸንበቆ ምርኩዝ ሁኖባችኋል። በኦጋዴን ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል ሲፈፀም ተባባሪ ትሆናላችሁ። ህወሃቶች በዚያች አገር ለሚፈፅሙት ማንኛውም ወንጀል እናንተ የእነርሱ በትር ሁናችሁ ታገለግላላችሁ። ከዚያች አገር ከሚገኘው ሃብት ግን ተካፋይ አትሆኑም። እነርሱ ሚሊየነር ሁነው የሚያደርጉትን ሲያጡ፤ አናንተ የሠራዊቱ አባላት ግን በችጋር ከነ-ቤተሰቦቻችሁ ትሰቃያላችሁ። ይሄ ሁኔታ ማብቃት የኖርበታል።
የአገሪቷ መከላከያ ኃይል ራዕይ ተብሎ የተነገረህ እንዲህ ይላል “. . . ለህገ-መንግስቱ እና ለህዝቡ ፍፁም ታማኝ የሆነ . . . የሃገራችን ህዝቦች ተምሳሊት የሆነ . . . የእውቀት መፍለቂያ የሆነ ሠራዊት መገንባት “
ምንም እንኳ ጥሩ ራዕይ ተቀርፆ የተቀመጠ ቢሆንም አንተ የሠራዊቱ አባል ግን የዚህ ራዕይ ተካፋይ አይደለህም።አንተ የምትካፈልው መከራውን እንጂ መልካሙን ራዕይ አይደለም። ለህገ-መንግስቱ እና ለህዝቡ ፍፁም ታማኝ የሆነ ሠራዊት መገንባት የሚለውን ራዕይ መልሰህ መልሰህ እንድታስብ እንመክርሃለን። በእኛ በኩል ግን ህወሃት በአገሪቷ ጫንቃ ላይ ከተቆናጠጠ ዘመን ጀምሮ ህዝቡን ሲያዋርድ ኖረ እንጂ ለህዝብ ታማኝ ሲሆን አልታየም። ህገ-መንግስት ብሎ ራሱ እዚያ ጫካ ሁኖ የፃፈውን ራሱ ሲያፈርሰው ኖረ እንጂ ሲያከብረው አላየንም። ህወሃት ለህገ-ማንግስቱ እና ለህዝቡ ታማኝ ሁኖም አያውቅም። ወደ ፊትም ራሱን ከህዝብ እና ከህግ-በታች አድርጎ እንዳይኖር እሰከ ዛሬ ሲፈፅመው የኖረው ወንጀል የሚያስችለው አይሆንም። ህወሃቶች ከነ እድፋቸው ወደ ማይቀረው መቃብራቸው መሄድን የመረጡ ስለሆነ ሠራዊቱ ራሱን ከእነዚህ ነውረኞች ለይቶ ለህገ-መንግስቱና ለህዝቡ ፍፁም ታማኝ መሆኑን ማስመስከር ይጠበቅበታል።
ሌላው ከህወሃት ውጪ ያላችሁ የሠራዊቱ አባላት ልታስቡበት የሚገባው ዓቢይ ነገር ደግሞ ‘የሃገራችን ህዝቦች ተምሳሊት የሆነ ሠራዊት መገንባት ‘ የሚለውን ራዕይ ነው። ሃገራችን ከ80 በላይ ብሄሮች የሚኖሩባት መሆኑ ይታወቃል።ለዚህች አገር ምሳሌ ሊሆን የሚችል መከላከያ ኃይል መገንባት እንደ ራዕይ የተቀመጠ ቢሆንም በተግባር የሆነው ግን ሌላ ነው። አሁን ባለው የአገሪቷ መከላከያ ኃይል ውስጥ ያሉ የጦር አዛዦችን ቀና ብለህ አይተህ እውነት መከላከያ ሃይሉ የህዝቦቿ ተምሳሊት የሆነ ሠራዊት መሆኑን ራስህ እንድትመልስ እንጠይቅሃለን። በአገሪቷ የተሾሙ ጄኔራሎች ከአንድ ጎጥ እና መንደር የተሰባሰቡ መሆናቸው በምን መልኩ የሃገራችን ህዝቦች ተምሳሊት የሆነ ሠራዊት ሊሆን እንደሚችል ህወሃቶችን ደግሞ ደጋግሞ መጠየቅ ተገቢ ይሆናል።
በመጨረሻም ‘የዕውቀት ምንጭ የሆነ ሠራዊት መገንባት’ የሚል ራዕይም በጉልህ ተፅፎ ተቀምጧል። የህወሃት የጦር አበጋዞች ከ7ኛ ክፍል ያልዘለሉ፤ካርታ ይዘው የቆሙበትን ሥፍራ እንኳ ለማሳየት የሚደናበሩ መሆናቸው የታወቀ ነው። እነዚህ ፊደል ቆጥረው ያልዘለቁ ቡድኖች የሚመሩት ተቋም እንደምን ሁኖ የዕውቀት ምንጭ ሊሆን እንደሚችል የሚያውቅ የለም። የህወሃቶች እውቀት የንፁሃን ደም ማፍሰስ፤ የድሃ ሃብት መዝረፍ፤ እኔ ብቻ ባይነት እንጂ ከዝህ የዘለለ ሌላ እውቀት ያላቸው አይደሉም። እነርሱ ባለመማራቸው የጎደለባቸው ነገር አለመኖሩን እያዩት ለትምህርትና ለተለየ ዕውቀት ዋጋ ይሰጣሉ ማለት አይቻልም። ሌሎቹም ተምረው እውቀት እንዲገበዩ ለማድረግ ስብዕናቸው አይፈቅድላቸውም። በዚህም ምክንያት ከውጭ አገራት በነፃ የሚገኘውን የትምህርት ዕድል እንኳ ወታደሩ ተጠቅሞ ራሱን በእውቀት እንዳያዳብር ይከለክላሉ። እንዳይማር የተከለከል የሠራዊት አባል እንደምን ሁኖ የዕውቀት መፍለቂያ ሊሆን እንደሚችል የሠራዊቱ አባላት የሽፍቶቹን ቡድኖች መጠየቅ ይኖርባችኋል።
የሠራዊቱ አባል የህዝብ አካል መሆንህን አትርሳው። ነገ ዞረህ የምትገባውም እዚያው ከወጣህበት ህዝብ መሆኑን እኛ ልናስታውስህ እንወዳለን። አሁን ባለው አካሄድህ የወጣህበትህን ድንኳን፤ በዚያች ድንኳን ውስጥ ሁነህ ያሳደጉህ ወገኖችህን እያሳደድክ መሆንህን አስታውስ። የወጣህበትንም ድንኳን እያፈረስክ ነው። ድንኳንህንም አፍርሰህ ከጨረስከው ነገ ዞሮ ማረፊያ እንደማይኖርህ ደግሞ እኛ ልናስታውሰህ እንፈልጋለን። ጥሪያችንን መስማት ከማንም በላይ ለራስህ ይበጅሃል። የወገኖችህን ጥሪ ሰምተህ በወገኖችህ ላይ የተመዘዘውን የበቀል ሰይፍ ለማቆም ከህዝብ ጎን መሆንን አልመርጥ ካልክ መጨረሻህ አያምርም። እነ ሳሞራ የኑስ ጠላቶችህ እንጂ ወገኖችህ አይደሉም። እነ ሳሞራ የኑስ አንተንና ልጅ ልጆችህን ጭምር በድንቁርና አዘቅት ውስጥ አኑረው ቀጥቅጠው ለመግዛት ያላቸው ፍላጎት ወሰን እንደሌለው ማወቅ ይኖርብሃል። የተሸከምከው መሣሪያ ለፍትህ ለእኩልነት፤ ለነፃነት እና ለእውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ እንቅፋት የሚሆኑትን የሚፋለም ሊሆን ይገባዋል እንጂ እነዚህን ጥያቄዎች ባነሱ ወገኖች ላይ የሚያነጣጥር መሆን አይኖርበትም።
እንግዲህ ምን እናድርግ እያላችሁ የምትጠይቁን አላችሁ። ለዚህ ጥያቄ መልሱ ያለው ከእናተው ደጅ ነው። እኛ ያነሳነውን ጥያቄ ባላችሁበት ሁናችሁ ማንሳት ትችላላችሁ። አብዛኛው ሠራዊት ጥቂት ዘረኞችንና ዘራፊዎችን ተሸክሞ የሚኖሩበት ሁኔታ ለመቀየር ሦስትም አራትም እየሆናችሁ እምቢ ማለት መጀመር አለባችሁ። ህወሃቶችን ተሸክማችሁ፤ የህዝባችሁ ጠላቶች ሁናችሁ፤ አገራችሁንና ህዝባችሁን አዋርዳችሁ የምትኖሩት ኑሮ ኑሮ አይደለምና እምቢ አይሆንም ማለት ጀምሩ። ለዘረኞቹና ለዘራፊዎቹ ህወሃቶች ከመሞት ይልቅ ለፍትህ፤ ለእኩልነት እና ለነፃነት ብላችሁ ብትሠው መሥዋእትነታችሁ ለዘላለም ሲዘከር ይኖራል፤ ስማችሁም ከመቃብር በላይ ይሆናል።ፍፃሜያችሁም የጀግና ፍፃሜ ይሆናል።
ፍፃሜያችሁ የጀግና ፍፃሜ እንዲሆን ለፍትህ፤ ለነፃነት እና ለእኩልነት ዘብ የምትቆሙ ሁኑ እንጂ የአንድን ዘረኛና ዘራፊ ቡድን እድሜ ለማራዘም የምትቆሙ አትሁኑ።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!!

Saturday, August 16, 2014

ከግብረሰዶማውያኑ ጀርባ (አርአያ ተስፋማሪያም)

August16/2014
አርአያ ተስፋማሪያም
ከጥቂት አመት በፊት በኢትዮጵያ በተለይ አዲስ አበባ የሚገኙ ግብረሰዶማውያን ያቀረቡትን ጥያቄ ተከትሎ በሸራተን ሆቴል የሃይማኖት አባቶች ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠት በስፍራው ተገኝተዋል። ፕሮግራሙ ሊጀመር 15 ደቂቃ ሲቀረው በድንገት የደህንነት ሰዎች ይገቡና ጋዜጠኞች እንዲወጡ ያደርጋሉ። ቀጥሎ ለሃይማኖት መሪዎቹ « ይህን መግለጫ መስጠት አትችሉም» ተባሉ። « ማነው ከልካዩ?..» ሲሉ ጠየቁ፤ ጭራሽ ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው። የተቃውሞ መግለጫው በዚህ መልኩ ተደናቀፈ። በመቀጠል ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ተጠየቀ። የሸራተኑን መግለጫ ያደናቀፈው ባለስልጣን ጣልቃ ገብቶ ሰልፉን አስከለከለ። ይህን ሁሉ ያደረጉት የወቅቱ የጤና ጥበቃ ሚ/ር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም መሆናቸውን የቅርብ ምንጮች ያረጋግጣሉ። በቅርቡ አሜሪካ መጥተው የነበሩት ዶ/ር ቴዎድሮስ በአፍሪካ ከጤና ጋር በተያያዘ አንድ ተቋም በሃላፊነት እንዲመሩ ተፈልገዋል። ከያዙት ስልጣን ፓርቲያቸው እንዲለቃቸውና አሜሪካኖቹ ወደሚፈለጉት ቦታ ዶክተሩን ለመውሰድ እቅድ መኖሩን አንዲት ከፍተኛ ሃላፊን በመጥቀስ ምንጮች ገልፀዋል።
ዶ/ር ቴዎድሮስ ስለዚህ ጉዳይ ይነጋገሩ አይነጋገሩ የታወቀ ነገር የለም። ዶክተሩ የተመረጡት « በኢትዮጵያ የጤና ጥበቃ ሚ/ር ሆነው ብዙ ነገር ሰርተዋል፤ ለምሳሌ ኤ.ች.አይ.ቪ/ ኤድስ፣ የወሊድ ቁጥጥር፣ የጤና ተቋማት ግንባታ..» ወዘተ በሚል ይጠቅሳሉ። ነገሩ ወዲህ ነው..የሚሉ ወገኖች ባለስልጣኑ የተፈለጉት « ለግብረሰዶማውያን መብት ዘብ በመቆም አሜሪካ በዚህ ዙሪያ ለምታራምደው አቋም ዶ/ር ቴዎድሮስ በተደጋጋሚ አጋርነታቸውን በማሳየታቸውና በተጨማሪ ስለግብረሰዶማውያን መብት ደግፈው ስለሚፅፉ ነው» ይላሉ። የሚያሳዝነው ዶ/ር ቴዎድሮስ « የማሰር ሱስ የለብንም..» ከማለት አልፈው የታሰሩትን ሙስሊሞች ከጓንታናሞ ጋር ለማያያዝ መሞከራቸውና ቀጥሎ ለማስተባበል መሯሯጣቸው ነው። እውነት ለመብት የቆሙ ቢሆን ኖሮ ከአምላክ ድንጋጌና ተፈጥሮ ላፈነገጡ ሳይሆን ካለሃጢያታቸው በእስር እየተሰቃዩ ለሚገኙ ወገኖች መሆን ነበረበት።
Social Media

“ማረሚያ ቤቶች ‹‹ማረሚያ›› ወይስ ማሰቃያ? – የሕዝብ ወኪሎችን ማሰቃየት የወከሉትን ህዝብ ማሰቃየት ነው” – ድምፃችን ይሰማ

ቅዳሜ ነሃሴ 10/2006
ሰሞኑን ከወደ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የሚሰማው ወሬ እንኳን ውስጡ ላለበት ውጪ ሆኖ ለሚሰማውም እጅግ ያስደነግጣል! አምባገነኖች በጭቁን ዜጎቻቸው ሰቆቃና መከራ ሲደሰቱ፣ ህዝባቸውን እንደታዳኝ እንስሳ ሲመለከቱ ማየት በእርግጥም ያሳዝናል! ያለአንዳች ጥፋት የህዝብ ወኪል ሆነው ድምጹን በማሰማታቸው ብቻ በሐሰት የሽብር ክስ ወህኒ ተወርውረው ሦስተኛ ዓመታቸውን የጀመሩት የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት በማእከላዊ የስቃይ ማእከል የጀመረ ስቃያቸው አሁንም ያለቀ አይመስልም። ሰሞኑን ወህኒ ቤት ውስጥ የተፈጠረው ክስተት አይደለም ለእስረኞች ለጠባቂ ፖሊሶች ሳይቀር አጅግ አሳዛኝ ነበር!!
c እና ሙስሊምች አህባሽን እና መጅሊስን በመቃወም ያደረጉት ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ (ቪዲዮ)
ሰሞኑን በእውቆቹ ዳዒዎች ኡስታዝ በድሩ ሁሴን፣ ኡስታዝ ያሲን ኑሩ እና ኡስታዝ አህመዲን ጀበል አዘጋጅነት የተዘጋጁ መፅሀፎች የህትመት ብርሀን በማየታቸው እጅግ የተበሳጨውና ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከብሔራዊ ‹‹ደህንነት›› ወቀሳ የደረሰበት ወህኒ ቤቱ አስተዳደር ኮሚቴዎችን ለማጥቃት ሰበብ ሲፈልግ ቆይቷል፡፡ ለዚያም ነበር ዳዒ በድሩ ሁሴንን ‹‹ግቢ ውስጥ በህገ ወጥ መንገድ መፅሀፍ ለማስገባት ሞክርሀል›› በሚል ሰበብ ማንገላታት የጀመረው፡፡ ለኡስታዙ ስንቅ የሚያደርሱለትን የባለቤቱን እናት ለግማሽ ቀን አግተው እርሱንም በሰንሰለት እጁን ጠፍረው ጨለማ ቤት ወረወሩት፡፡ ምንም እንኳን በወህኒ ቤቱ ህግ የዲሲፕሊን ተቀጪ እስረኞች ቤተሰብ እንዳይገናኙ ከመከልከል ውጭ ምግብ እንዳይገባላቸው ተከልክሎ የማያውቅ ቢሆንም ኡስታዝ በድሩን ግን ውዱዕ ማድረግ እንኳ በማይችልበት ጨለማ ክፍል እጆቹ በሰንሰለት ታስረው ከቤተሰብ ምግብም ሳይገባለት ለቀናት በረሃብ እንዲቀጣ አድርገዋል፡፡
ጨለማ ክፍል የገባው ኡስታዝ በድሩ ብቻ አይደለም፡፡ ኡስታዝ አሕመድ ሙስጠፋም ወንድም አብዱረዛቅ አክመል ላይ ወህኒ ቤቱ የሚፈጽመውን በደል ተቃውሞ ‹‹ለምን እንዲህ ይደረጋል?›› በማለቱ ብቻ እርሱም በጨለማው ቤት ከኡስታዝ በድሩ ጋር በረሃብ እንዲቀጣ አድርገዋል፡፡ የቤተሰብ ምግብ እና ቅያሬ ልብስ እንዳያገኝ ተደርጎና በግፍ እንዲሰቃይ ተፈርዶበት በዚያ መከረኛ ጨለማ ቤት ተወርውሯል።
ማረሚያ ቤቱ እየፈጸመ ያለው በደል ለፍርድ ቤት በአቤቱታ መልኩ የቀረበ ሲሆን ፍርድ ቤቱም ሰውን እንዲህ አይነት ቅጣት መቅጣት ፋሽስታዊ ተግባር በመሆኑ በአስቸኳይ እንዲቆም በቃል ትዕዛዝ አስተላልፏል፡፡ የወህኒ ቤቱ አስተዳደር ግን ‹‹እኛ ከህጎች ሁሉ የበላይ ነን! እስቲ ፍ/ቤቱ ምን እንደሚያደርግ እናያለን!›› በሚል ትእቢተኝነት በድርጊቱ ገፍቶበታል፡፡ አቤቱታው ድጋሚ ቀርቦ ፍ/ቤቱ ተመሳሳይ ትዕዛዝ አስተላልፏል፡፡ በሁኔታው የተቆጡት የመሃል ዳኛ ‹‹ፍ/ቤቱ ጥርስ የሌለው አንበሳ አይደለም›› ብለው እስከመዛትም ደርሰዋል፡፡ ግና የተፈጠረ ነገር ቢኖር ማረሚያ ቤቱ ‹‹አይደለም ምግብ ገና ምኑን አይታችሁ! ቁም ስቅላችሁን ነው የምናሳያችሁ! ፍ/ቤቱም፣ ጦር ሰራዊቱም ወህኒ ቤቱም በእኛው እጅ ነው! ይህን እስክታምኑ ድረስ የእስር ቆይታችሁን የሲኦል ህይወት ነው የምናደርገው›› ሲል መዛቱ ብቻ ነበር!
ከፍርድ ቤቱ የተላከውን የጽሁፍ ትእዛዝ ማረሚያ ቤቱ አሁንም አልተቀበለም፡፡ ዳኞቹም ተስፋ የቆረጡ በሚመስል ሁኔታ ‹‹አቤቱታውን በፅሁፍ አምጡ›› ብለው ለማረሚያ ቤቱ አንድ፣ ለራሳቸው ደግሞ አንድ ቅጂ ወስደው ማረሚያ ቤቱ ይህን ድርጊት ለምን እንደሚፈፅም እንዲያስረዳ ለሰኞ ነሐሴ 12/12/06 ቀጥረዋል።
‹‹እንዲህ አይነቱ ግፍና መከራ ከህዝባችን ላይ መች ይሆን የሚቆመው?›› ብለን ራሳችንን ስንጠይቅ ገና ብዙ ትግል እንደሚቀረን እንረዳለን፡፡ ወኪሎቻችን ከማእከላዊ ጀምሮ ብዙ ስቃይ አልፈው ከእነ ሙሉ ወኔያቸው ዛሬ ላይ ደርሰዋል፡፡ እኛም እንደህዝብ በአካል ወህኒ ቤት ባንገባም ነጻነት በራቀው አየር ስንኖር ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ ይህን ግፍ የሚሰሩና የሚያሰሩ ሁሉ ወደፊት ይህ ግፋቸው ዋጋ እንደሚያስከፍላቸው ሊያውቁት ይገባል፡፡ ህዝበ ሙስሊሙ መብቱ ተጥሶ እጁን አጣጥፎ የሚቀመጥበት ዘመን ካለፈ መቆየቱን ላለፉት ዓመታት በተግባር እንዳረጋገጠ ሁሉ በቀጣይም ወኔውን አግዝፎ በአላህ ፈቃድ በሰላማዊ ትግሉ ድል እስኪጎናጸፍ ድረስ ይቀጥላል፤ ድልም ከአላህ እንጂ ከሌላ አይደለምና!
የሕዝብ ወኪሎችን ማሰቃየት የወከሉትን ህዝብ ማሰቃየት ነው!
ትግላችን በአላህ ፈቃድ እስከድል ደጃፎች ይቀጥላል!
ድምፃችን ይሰማ!

Friday, August 15, 2014

በሰማያዊ ፓርቲ የአርባ ምንጭ አስተባባሪዎች የተጀመረው እስር ተጠናቅሮ ቀጥሏል

August 16/2014
ሰማያዊ ፓርቲ እንደዘገበው፦
blue party
ከአሁን ቀደም አራት የሰማያዊ ፓርቲ የአርባ ምንጭ አስተባባሪዎች በሽብርተኝነት ስም መታሰራቸው ይታወቃል፡፡ እነዚህን እስረኞች ያሉበትን ሁኔታና የዞኑን አደረጃጀት ለመጎብኘት ከአዲስ አበባ (ከማዕከል) የድርጅት ጉዳይ ኃላፊው አቶ ብርሃኑ ተክለያሬድና የድርጅት ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ አባል የሆነው ዮናስ ከድር ለጉብኝት በሄዱበት ወቅት ሲያስተባብሩ የነበሩት አባላት ከማዕከል የሄዱት የፓርቲው አመራሮች ሲመለሱ ለእስር መዳረጋቸውን ከአካባቢው የደረሰን መረጃ ይጠቁማል፡፡
በመሆኑም አቶ ከሳሁን አየለ የተባለው የሰማያዊ ፓርቲ አርባምንጭ አስተባባሪ ከአዲስ አበባ የመጡትን የፓርቲው አመራሮች ጋር በመሆን የዞኑን አደረጃጀትና በእስር ላይ ያሉትን የፓርቲው አስተባባሪዎች አስጎብኝቷል በሚል መታሰራቸው ታውቋል፡፡ በተመሳሳይ ሻምበል ካሳ የታሰሩትን ጠይቀሃል በሚል ለእስር መዳረጋቸውንና ነፃነት የተባለው የፓርቲው አስተባባሪ ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር እንዳይሰራና በታሰሩት ላይ እንዲመሰክር በማስፈራሪያ መለቀቁ ታውቋል፡፡
በዞኑ የሚገኙ የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች እስራትና መከባ እየደረሰባቸው ሲሆን በአሁኑ ወቅትም ሉሉ መሰለ፣ በፈቃዱ አበበ፣ ካሳሁን አየለ፣ ሻምበል ካሰና ኢ/ር ጌታሁን የተባሉት የፓርቲው አስተባባሪዎችና አባላት በእስር ላይ እንደሚገኙ ለመረዳት ተችሏል።

ለዝክረ መለስ በሚል የአዲስ አበባ መስተዳድር ሰራተኞች ስራቸውን አቋርጠው ውይይቱን እንዲሳተፉ ታዘዙ

august15/014
Esat
የዝክረ መለስ 2ኛ የሙት ዓመት አከባበርን ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ በነበረው የፓናል ውይይት የመንግስትን ስራተኛው ለግማሽ ቀን ስራ ሳይሰራ መዋሉን ዘጋያችን ገልጿል። 

በተለያዩ ቦታዎች የተዘጋጁትን የፓናል ውይይቶች የመስተዳድሩ የአመራር አባል አቶ ፋቃዱ ወ/አረጋይ፣ የአዲስ አበባ ሴቶችና ወጣቶች ቢሮ ኃላፊና የምክትል ቢሮ ኃላፊ በተናጠል መርተዋል። 


የወጣቶች መድረክ በሃገር ፍቅር አዳራሽ፣ የሴቶች መድረክ በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት የባህል አዳራሽ እንዲሁም የልዩ ልዩ አካላት መድረክ በስድስት ኪሎ በሚገኘው የባህል ማዕከል የፓናል ውይይት ተካሂዷል።


በሶስቱም ውይይቶች ለተሳታፊዎች የሃሳብና የጥያቄ ማቅረቢያ ሰዓት በተጊቢው መንገድ ያላተሰጠ ሲሆን ሁሉም የመድረኩ ተናጋሪዎች አቶ መለስ ዜናዊን በማወደስ ላይ ትኩረት አድርገው ነበር።


በመድረኩ ላይ አቶ መለስ ዜናዊ አዋቂ መሪ፣ የሰብዓዊ መብት ታጋይ፤ የአፍሪካ መሪ ፤ የመልካም አስተዳደር ችግርን የፈታ መሪ፤ የአለም መሪ፤ አለማቀፋዊ ደረጃ ያለው ጭንቅላት ባለቤት ፣ ተዝቆ የማያልክ የእውቀት ምንጭ እንደነበር ተወስቷል።
የመለስ ሌጋሲን ብቻ እየመነዘሩ መሄድ እንደሚገባ የተነገረ ሲሆን መለስ በመሪነት ዘመኑ በተለያየ ጊዜ ያደረጋቸውን ቃለ መጠይቆች ማንበብ እንደሚገባ ለሰራተኛው ተነግሯል።


መለስ "ድህነትን ያስወገደ ፤የሃገርና የትውልድ ችግር የቀረፈ ፤የመልካም አስተዳደር ችግርን ገና ተማሪ እያለ ጀምሮ የሚያውቅ ፤የውጪ ጉዳይ ፖሊሲው በሰላምና በድህነት ላይ ብቻ እንዲመሰረት ያደረገ ፤የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ያስከበረ ፤በአፍሪካ መሪዎችና በዓለም መሪዎች ስብሰባ ላይ ተጽእኖ ሲፈጥር የነበረ ፤በእውቀትና በንባብ ላይ የተመሰረተ ትንታኔ የሚሰጥ ፣የህዳሴ ግድብን መሰረት የጣለ ታሪካዊ መሪ" መሆኑን በማወቅ ፣ ማንኛውም ዜጋ የእሱን ሌጋሲ ማስቀጠል እንዳለበት በመድረኩ ላይ ተወስቷል። የመለስ ሌጋሲ የአፍሪካም ሌጋሲ እንደሆነም ተገልጿል። 


በማዘጋጃ ቤት በነበረው የሴቶች መድረክ ከተሳታፊ ሴቶች ምንም ጥያቄ ሳይነሳ ውይይቱ ያለቀ ሲሆን ፣ መድረክ ላይ ስታወያይ የነበረችሁ የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች ወጣቶችና ህፃናት ቢሮ ኃላፊ በመድረኩ ላይ ማይክራፎኑን ተቀብላ ማልቀሷን ዘጋቢያችን ገልጻለች።


በሀገር ፍቅር በነበረው መድረክ ደግሞ ስለመለስ ብዙ ገለጻዎች ከተሰጡ በሁዋላ፣ ተሳታፊው አስተያየት እንዲሰጥበት እድል ሲቀርብ ፣ አንድ ተሳታፊ " ስለ መለስ ብዙ ተብሏል ፣ ነገር ግን በአዲስ አበባ ብዙ ቁጥር ያላቸው ዜጎች ዳቦ መብላት አልቻሉም፤የኑሮ ውድነቱ ሰማይ ነክቷል፣ እናንተ ድህነት ጠፍቷል ትላላችሁ.." እያለ መናገር ሲጀምር፣ መድረክ ላይ ያሉ ሰዎች አስቁመውታል። 


ጠያቂው ያነሳውን ጥያቄ ለመደገፍና ንግግሩ እንዲቋረጥ መደረጉን ለመቃወም በሚመስል መልኩ አዳራሹ በጭብጫ የተናጋ ሲሆን ፣ የመድረኩ መሪዎች " እንዲህ አይነት ጥያቄዎች በሌላ የመልካም አስተዳደር መድረኮች የሚመለሱ በመሆናቸውና የዛሬው ውይይት በዝክረ መለስ ላይ ብቻ ማተኮር እንደለበት በማሳሰባቸው ከድጋፍ ማብራሪያ ውጪ ሌላ የተቃውሞ ሃሳብ ሳይነሳ መቅረቱን በውይይቱ የተሳተፈው ዘጋቢያችን ገልጿል።


አወያዩ አቶ ፋቃዱ ወ/ገብርኤል " አንድ በሽተኛ የሬዲዮ እና ቴሌቪዥ ጣቢያ አለ፣ ኢትዮጵያን በመንግስታዊ ድርጅቶች እንድትጥለቀለቅ አድርጌ በእርዳታ ሃገሪቱን እመራታለሁ ብሎ የሚያስብ ብለው የተናገሩ ሲሆን፣ የጣቢያውን ስም ከመግለጽ ተቆጥበዋል። ንግግራቸውን በመቀጠልም " መንግስት ስለልማት ይለፈልፋል! መብራት ግን ይጠፋል፤መንግስት ስለልማት ይለፈልፋል! ውሃ ግን ይጠፋል፤ መንግስት ስለልማት ይለፈልፋል! ትራንስፖርት ግን ይጠፋል" በማለት ህዝቡ እንደሚናገር ገልጸው፣ ይህ አስተሳሰብ እንደማይጠቅም፣ የያዝነውን ልማት በአግባቡ ይዘን ለሌላውን ጠንክረን መስራት ብቻ ነው የሚያዋጣን ብለዋል።


በ3ቱም መድረኮች ተሳታፊ የነበሩት በአዲስ አበባ መስተዳድር ስር የሚገኙ ከወረዳና ክ/ከተማ በላይ ያሉ የሁሉም ቢሮዎችና ተቋማት ሰራተኞች ናቸው፡፡


ኢሳት ዝክረ መለስ በአል አከባበር ዝርዝር መመሪያው የደረሰው ሲሆን፣ ከመመሪያው ለመረዳት እንደሚቻለው መለስና ልማታዊ ዲሞክራሲያዊ መንግስት፣ መለስና የህዳሴው ግድብ፣ መለስና የድህነት ጥላቻ፣ መለስና ብህሃነትን በብቃት ማስተናገድ፣ መለስና የረቀቀ የዲፕሎማሲ ትግል በሚሉ ርእሶች ዙሪያ በመላው አገሪቱ ውይይቶች ይካሄዳሉ፡፤ ከዚህ በተጨማሪ መለስ በራሱ ንግግር በተመረጡ ጉዳዮች ላይ ያደረጋቸው ንግግሮች በሚዲያ እንዲቀርቡ እንዲደረግ በመመሪያው ላይ ተቀምጧል።
በሌላ ዜና ደግሞ በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ በጠ/ሚ/ር ኃይለማርያም ደሳለኝ የሚመራ 2ኛው ሃገራዊ የመልካም አስተዳደር ውይይት እየተካሄደ ነው። የከፍተኛ ት/ት ተቋማት አመራሮች፤የክልል መስተዳድሮች፣ የቢሮ ኃላፊዎችና ሚኒስትሮች ስብሰባ እያካሄዱ መሆኑ ታውቋል።


አቶ አዲሱ ለገሰ ኢህአዴግ በገጠመው የአመራር ችግር የተነሳ የትራንስፎርሜሸንኑን እቅድ ለማሳካት አለመቻሉን መግለጻቸው ይታወቃል።ኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች እያደረጉት በሚገኘው ስብሰባ የአመራር ችግሩ ዋናው የመመያያ አጀንዳ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።