Thursday, January 2, 2014

አድዋ የሚኒሊክ ታሪክ ብቻ ነዉ እንዴ?

 ገነት ገመዶ  ከኖርዌ

አንዳንድ ሠዎች ግርም ይሉኛል እንሱ ስለሚያስቡት የዘር(ቋንቋ )አመለካከት እንደራሴ ሆኜ ስቃወማቸዉ በእዉቀት ብቻ ይወስዱታል ለምን በቅንነት እንደማይመለከቱት አይገባኝም በዚህ ሳምንት ቴዲ አፍሮ የፍቅር ጉዞ የተሰኘዉን የሙዚቃ ኮንሰርት በመላዉ ኢትዮጲያ ከበደሌ ስፔሻል ቢራ ጋር በመሆን ለማዘጋጀት ስምምነት መፈራረማቸዉ የሚታወስ ነዉ ይህን ተከትሎ አንዳንድ በተማሩት ልክ ያወቁ የመሰላቸዉ የቴዲ አፍሮ < የፍቅር ጉዞ> ኮንሰርት ማንም ሠዉ እንዳይገባና በደሌ ቢራ እንዳይጠጣ ከፍተኛ ቅስቀሳ እያደረጉ ይገኛሉ::

ሠዎች ባወቁት ልክ የሠዉን አዕምሮ ለመጠምዘዝ ይሞኩራሉ ይህ ስህተት ነዉ ኔልሰን ማንዴላ 27 ዓመት በእስር ቤት ለወገናቸው ሲማቅቁ ከዛም ከእስር ከተፈቱ በሁላ የደቡብ አፍሪካ ህዝብ 100% ይወዳችዋል ማለት ሰህተት ነዉ በሚወዳች ልክ የሚጠላቸዉም ሠዉ አለና: እኔ ያልገባኝ ነገር አድዋ የሚኒሊክ ታሪክ ብቻ ነዉ እንዴ? ቴዲ አፍሮ ጥቁር ሠዉ ብሎ በሙዚቃ ያወደሰዉ በአድዋ ላይ የተሳተፉተን መላዉን የኢትዮጲያ ጀግኖችን እኮ ነዉ ያ ታሪክ እንኩአን ለኢትዮጲያ አይደለም መላዉን አፍሪካ ቀና ብለዉ እንዲሄዱ ያደረገ ታሪክ መሆኑን መዘንጋት የለብንም በሙዚቃዉ እነማን ተወሱ ፩ ፊታውራሪ ሃብተጎርጊስ ዲነግዴን ፪ ባልቻ አባ ነፍሶ ፫ ለንግስት እቴጌ ጣይቱ እና በጦርነቱ ለተሰዉ የኢትዮጲያ ጀግኖች ነዉ ፩ ሚኒሊክን ብቻ እያነሳቹ እንዲህ ነበሩ ማለት ምንም ጥቅም የለዉም::

 እዚህ ጋር ማወቅ የሚገባን የሠዉ ልጂ ሁል ጊዜ ትክክል አለምሆኑን ነዉ እምዬ ሚኒሊክ እንደሠዉነታቸዉ ስህተት ሊሰሩ ይችላሉ ሠዉ ናቸዉና አንድ ሀገርን የሚመራ ሠዉ 80 ሚሊየን የኢትዮጲያን ህዝብ ያስደስታል ብሎ ማሰቡ ሞኝነት ነዉ በዛን ጊዜ እምዬ ሚኒሊክ ሀገርን ሲመሩ የነበረዉ በዕዉቀት ሳይሆን በፀጋ ነዉ እምዬ ሚኒሊክ እንደዚህ ብለዉ ተናገሩ የሃገሬ ሠዉ ዘመቻዉ ተቃርቦዋልና ክተት ብያለዉ የቀረህ እንደሆነ እምዬ ማርያምን አልምርህም አሉ። እምዬ ማርያምን ተብሎ ማነዉ እኔ የማርያም ሥም አይመለከተኝም ብሎ ሙስሊም ኢትዮጲያዉያን ከዘመቻ የቀሩት? አቤት ፀጋ እንዲህ ነዉ ዕንጂ እኔ ክርስቲያን ነኝ አንድ ሙስሊም ወገኔ አላህ ይስጥህ ብሎ ቢመርቁኝ አያገባኝም ብዬ ዝም አልልም አሜን አሜን ብዬ ምርቃቱን በደስታ እቀበላለዉ በቃ ፍቅር ማለት ይሄ ነዉ ፍቅር የሌለዉ እዉቀት ከንቱ ነዉ እናንት የዘር(የቋንቋ ) እዉቀት ያላቹ አይጠቅማችዉም ራቁት የፈጠራችዉን ፈጣሪ መለመን ያለባቹ ዕዉቀት ሳይሆን ፍቅርን ለምኑት ምክኒያቱም በፍቅር ዉስጥ ብዙ መልካም ነገሮች አሉና የዛኔ ዕዉቀትን ብቻ ሳይሆን በፍቀር ዓለምን መግዛት ይቻላልና።
 ፍቅር ያሸንፋል!!!

No comments:

Post a Comment