MARCH 27, 2014 LEAVE A COMMENT
ዛሬ ጠዋት ለህወሓት/ኢህአዴግ የሚያስደስት ለኢትዮጵያውያን ደግሞ መልካም ያልሆነ ዜና ሰማሁ፡፡ አማርኛ እና ኦሮምኛ ተናጋሪ ካድሬዎች ባህር ዳር ላይ በስርዓቱ የተለመዱ አጸያፊ ስድቦችን ተለዋወጡ፡፡ ተደባደቡ፡፡ ይህ እንግዲህ ለኢህአዴግ የዘራውን የጠባብ ብሄርተኝነት እንደማጨድ ይቆጠራል፡፡
የመላው ኢትዮጵያ ጨዋታዎች፣ የብሄር ብሄረሰቦች….ምናምን ተብሎ ከካድሬ ውጭ ማንም ሊገኝ አይችልም፡፡ በዚህ ጨዋታም የተገኙት ሆድ አደር የህወሓት/ኢህአዴግ ካድሬዎች ብቻ ናቸው፡፡ ከወራት በፊት ህወሓት እንደፈለገ የሚጎትተው የብአዴኑ አለምነው መኮንን ወክየዋለሁ የሚለውን ህዝብ አብጠልጥሏል፡፡ እርግጠኛ ነኝ ይህ ህዝብ ‹‹መርዝ›› መሆኑን ለማሳየት ሲባል እራሳቸው እሳቱን ለኩሰውታል፡፡ ደግሞም በአሁኑ ወቅት ህዝብ በሌላ ምሬት ላይ ነው፡፡ ተቃዋሚዎች በስፋት መንቀሳቀስ ጀምረዋል፡፡
ይህን ሁሉ አጀንዳ ሁሌም መሳሪያው ወደሆነው ጎጠኝነት አዞረው፡፡ ህወሓት/ኢህአዴግ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያንን ሲያደማ ተንፈስ ያለ ይመስለዋል፡፡ ደስም ይለዋል፡፡ ይህ ልክፍቱ ነው! ይህ የባህርዳሩ ግጭት ሆን ተብሎ ታስቦበት የተደረገ የህወሓት/ኢህአዴግ የፕሮጀክት አካል ነው፡፡ ምርጫና ሌላ አስፈሪ ነገር ሲከሰትበት ይህን ካርድ ማውጣቱ የተለመደ ነው፡፡ አዎ! ህወሓት አትርፏል፡፡ ሆድ አደር ካድሬዎች ይህን ፕሮጀክት ወደ ዩኒቨርሲቲዎች ሊያስፋፉት ይችላሉ፡፡ ታዲያ እነ አለምነውና አባዱላ ምን ስራ አላቸው? እነ አባይ ጸሀዬስ ምን አላማ አላቸው?
Getachew Shiferaw
posted by Aseged Tamene
No comments:
Post a Comment