ስንገጣጠም
በካድሬዎቹ ፊት ላይ ድንጋጤና ንዴት የተቀላቀለበት ስሜት መታየት ጀመረ፡፡ከዚያም ያልተለመዱ እንቅስቃሴዎች ተከተሉ
ሁሉም ካሜራውን አውጥቶ ፎቶውን ያንቀጫቅጨው ጀመር፡፡ እኛም ካድሬዎቹ እያደረጉት ያሉት የማስፈራራት ሙከራ መሆኑን
አውቀን የደብረ ማርቆስ ከተማ የፓርቲያችን አመራር የሆነውን ወጣት ሳሙኤል አወቀን ጨምረን አጠገባቸው ወደነበረ
ወንበር ሄደን ተቀመጥን፡፡ይሄኔ ቤቱ ሞቅ ባለ የጉንተላ ዘፈን ተነቃነቀ፡፡ሁሉም ከመቀመጫው ተነስቶ ወደ እኛ
ባነጣጠረ መልኩ ‹‹ያቺን ጎፈሬ ዛሬ ነው ዛሬ›› እያለ ይውረገረግ ጀመር እኛም በነሱ ዘፈንና ፉከራ ስንዝናና
ቆይተን ወደ ማረፊያችን ተመልሰን ገባን፡፡
እንደገባን ስልኬ ጠራ ሳሙኤል አወቀ ነበር የደወለው፡፡ካድሬዎቹ ዛሬ ሰማያዊዎች እዚች ሆቴል አያድሯትም እናስወጣቸዋለን እያሉ በሞቅታ ስሜት እየዛቱ መሆኑን ነገረኝ፡፡ጅብ በማያውቁት ሀገር ሄዶ……… እንዲሉ ከካድሬዎቹ ጋር በደንብ እንደምንተዋወቅና ደፍረው እንደማያደርጉት በመንገር ተሰናበትኩት፡፡የሚገርመው ካድሬዎቹ ወደ ክፍላችን አልመጡም ሊመጡም አይችሉም ምክንያቱም እኛ ሰማያዊዎች ነን፡፡እነሱም ይህን ጠንቅቀው ስለሚያውቁ ነው ዕኛ ከገባን በኋላ ይፎክሩ የነበረው፡፡
እናንተም ውረዱ እስከ ፈረፈሩ
እኛም እንወርዳለን እስከ ፈረፈሩ
እዛ ጋር ይለያል ፈሪና ደፋሩ
ብለን ለስለስ ባለ ሙዚቃ ጋደም ብለናል፡፡

No comments:
Post a Comment