Sunday, September 21, 2014

EthioSwedish Task Force Decorated woyane Ambassader with Rotten Fish &eggs

በስዊድን የኢትዮጵያ አምባሳደር ወ/ሮ ወይንሸትና ተላላኪዎቿ ላይ የገማ አሳ የተቀባ እንቁላል ተወረወረባቸው (ፎቶዎች እና ቪድዮ ይዘናል)




  • 134

 በስዊዲን የኢትዮጵያ አባሳደር ላይ የገማ አሳና እንቁላል እንዳይወረወርባቸው ሲከላከሉ የሚያሳይ ፎቶ

በስዊዲን የኢትዮጵያ አባሳደር ላይ የገማ አሳና እንቁላል እንዳይወረወርባቸው ሲከላከሉ የሚያሳይ ፎቶ
 በስዊዲን የኢትዮጵያ አባሳደር ላይ የገማ አሳ የተቀባ እንቁላል እንዳይወረወርባቸው ሲከላከሉ የሚያሳይ ፎቶ

በስዊዲን የኢትዮጵያ አባሳደር ላይ የገማ አሳና እንቁላል እንዳይወረወርባቸው ሲከላከሉ የሚያሳይ ፎቶ


ናቲ ማን ለዘ-ሐበሻ እንደዘገበው፦
“ለኢትዮጵያ ባለስልጣናት ሕዝብን ሃገር ቤት እየገደሉ ውጭ መጥቶ መዝናናት ካሁን በኋላ ፋሽኑ አልፏል” ይላሉ
በስዊድን ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን። ኢትዮጵያውያኑ ዛሬ በስዊድን የኢትዮጵያ አምባሳደርና በተላላኪዎቿ ላይ የገማ
አሳና እንቁላል ሲወረውሩባቸው ውለዋል። አምባሳደሯም ከነሃገር ባህል ልብሷ ሮጣ ስትገባ እና ተላላኪዎቿም ሲከላከሏት
የሚያሳይ ፎቶዎች እና ቪድዮዎች ተይዘዋል። በስዊዲን የኢትዮጵያ አምባሳደር ወ/ሮ ወይንሸት ታደሰ በኢትዮጵያውያኑ
በደረሰባት ከፍተኛ ተቃውሞና የገማ አሳ በተቀባ እንቁላል ውርወራ በመደናገጥ ስትሮጥ ያመሸች ሲሆን በዲያስፖራ ያለው
ኢትዮጵያዊም በገዢው ፓርቲ ባለስልጣናት እና በተባባሪዎቹ ዙሪያ ትዕግስቱ ያለቀ መሆኑን ያሳየበት ዕለት ነው።


አምባሳደሯ የሚገማ አሳ የተቀባ እንቁላል ውርወራውን ፈርተው ለረዥም ጊዜ የፖሊስ ሃይል እስኪመጣ ተቀምጠው ነበር። ተጨማሪ ፖሊስ ቢመጣም ከውርወራው ሊያስጥሏት አልቻሉም።


ከዚህ በፊት በኖርዌይ፣ በቴክሳስ፣ በሚኒሶታ፣ በዋሽንግተን ዲሲ፣ በሎስ አንጀለስ ካናዳ የወያኔ ባለልጣናት
በኢትዮጵያውያን ሊያደርጉት የነበረው ስብሰባ የተስተጓጎለባቸው ከመሆኑም በላይ በሄዱበት ቦታ ሁሉ ኢትዮጵያዊያኑ
እየተጋፈጧቸው ገዳይ እና አምባገነን መሆናቸውን ሲነግሯቸው በቪድዮ ዘ-ሐበሻ ማሳየቷ ይታወሳል።


በስዊድን የኢትዮጵያ አምባሳደር ወ/ሮ ወይንሸት ላይ የተወረወረው የገማ አሳ እና እንቁላል ውርወራ በቀጣይም
የወያኔ ባለስልጣናት በሄዱበት ቦታ ሁሉ እንደሚቀጥል በየከተማው ያሉ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን እያሳወቁ ነው፡፡


ዛሬ እንቁላል የተቀባ አሳ ከተወረወረባቸው የወያኔ ባለስልጣናት መካከል፡

1ኛ. ወ/ሮ ወይንሸት ታደሰ

2ማ. አቶ ዳንኤል ጠንክር

3ኛ. አቶ ሁሴን አህመድ

4ኛ. አቶ ተረፈ ቡርቃ

4ኛ. ወ/ሮ ሮማን አብዱልቃድር

5ኛ. አቶ ፈንታዬ ሮባ

6ኛ. ወ/ሮ ሮማን ሙሉጌታ ይገኙበታል።


ቪድዮውንም ይመልከቱ፦

በስዊድን የኢትዮጵያ አምባሳደር ወ/ሮ ወይንሸትና ተላላኪዎቿ ላይ የገማ አሳ የተቀባ እንቁላል ተወረወረባቸው (ፎቶዎች እና ቪድዮ ይዘናል)





  • 134

 በስዊዲን የኢትዮጵያ አባሳደር ላይ የገማ አሳና እንቁላል እንዳይወረወርባቸው ሲከላከሉ የሚያሳይ ፎቶ

በስዊዲን የኢትዮጵያ አባሳደር ላይ የገማ አሳና እንቁላል እንዳይወረወርባቸው ሲከላከሉ የሚያሳይ ፎቶ
 በስዊዲን የኢትዮጵያ አባሳደር ላይ የገማ አሳ የተቀባ እንቁላል እንዳይወረወርባቸው ሲከላከሉ የሚያሳይ ፎቶ

በስዊዲን የኢትዮጵያ አባሳደር ላይ የገማ አሳና እንቁላል እንዳይወረወርባቸው ሲከላከሉ የሚያሳይ ፎቶ

ናቲ ማን ለዘ-ሐበሻ እንደዘገበው፦ “ለኢትዮጵያ ባለስልጣናት ሕዝብን ሃገር ቤት እየገደሉ ውጭ መጥቶ መዝናናት ካሁን በኋላ ፋሽኑ አልፏል” ይላሉ በስዊድን ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን። ኢትዮጵያውያኑ ዛሬ በስዊድን የኢትዮጵያ አምባሳደርና በተላላኪዎቿ ላይ የገማ አሳና እንቁላል ሲወረውሩባቸው ውለዋል። አምባሳደሯም ከነሃገር ባህል ልብሷ ሮጣ ስትገባ እና ተላላኪዎቿም ሲከላከሏት የሚያሳይ ፎቶዎች እና ቪድዮዎች ተይዘዋል። በስዊዲን የኢትዮጵያ አምባሳደር ወ/ሮ ወይንሸት ታደሰ በኢትዮጵያውያኑ በደረሰባት ከፍተኛ ተቃውሞና የገማ አሳ በተቀባ እንቁላል ውርወራ በመደናገጥ ስትሮጥ ያመሸች ሲሆን በዲያስፖራ ያለው ኢትዮጵያዊም በገዢው ፓርቲ ባለስልጣናት እና በተባባሪዎቹ ዙሪያ ትዕግስቱ ያለቀ መሆኑን ያሳየበት ዕለት ነው።
አምባሳደሯ የሚገማ አሳ የተቀባ እንቁላል ውርወራውን ፈርተው ለረዥም ጊዜ የፖሊስ ሃይል እስኪመጣ ተቀምጠው ነበር። ተጨማሪ ፖሊስ ቢመጣም ከውርወራው ሊያስጥሏት አልቻሉም።
ከዚህ በፊት በኖርዌይ፣ በቴክሳስ፣ በሚኒሶታ፣ በዋሽንግተን ዲሲ፣ በሎስ አንጀለስ ካናዳ የወያኔ ባለልጣናት በኢትዮጵያውያን ሊያደርጉት የነበረው ስብሰባ የተስተጓጎለባቸው ከመሆኑም በላይ በሄዱበት ቦታ ሁሉ ኢትዮጵያዊያኑ እየተጋፈጧቸው ገዳይ እና አምባገነን መሆናቸውን ሲነግሯቸው በቪድዮ ዘ-ሐበሻ ማሳየቷ ይታወሳል።
በስዊድን የኢትዮጵያ አምባሳደር ወ/ሮ ወይንሸት ላይ የተወረወረው የገማ አሳ እና እንቁላል ውርወራ በቀጣይም የወያኔ ባለስልጣናት በሄዱበት ቦታ ሁሉ እንደሚቀጥል በየከተማው ያሉ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን እያሳወቁ ነው፡፡
ዛሬ እንቁላል የተቀባ አሳ ከተወረወረባቸው የወያኔ ባለስልጣናት መካከል፡
1ኛ. ወ/ሮ ወይንሸት ታደሰ
2ማ. አቶ ዳንኤል ጠንክር
3ኛ. አቶ ሁሴን አህመድ
4ኛ. አቶ ተረፈ ቡርቃ
4ኛ. ወ/ሮ ሮማን አብዱልቃድር
5ኛ. አቶ ፈንታዬ ሮባ
6ኛ. ወ/ሮ ሮማን ሙሉጌታ ይገኙበታል።
ቪድዮውንም ይመልከቱ፦


Friday, September 19, 2014

አነጋፋው አርቲስት ሀይማኖት ዓለሙ ከሰሞኑ ባጋጠመው ህመም ዛሬ ከሰዓት ከዚህ ዓለም ተለይቷል፡፡

አሳዛኝ ዜና !!
አርቲስት ሃይማኖት ዓለሙ ከዚህ ዓለም ተለየ፡፡
አነጋፋው አርቲስት ሀይማኖት ዓለሙ ከሰሞኑ ባጋጠመው ህመም ዛሬ ከሰዓት ከዚህ ዓለም ተለይቷል፡፡
ወዳጄ ዘካሪያስ ብርሃኑ ባካፈለኝ መረጃ መሰረት
አርቲስት ሀይማኖት…በትወና /አክቲንግ/ በአሜሪካን አገር በሁለተኛ ዲግሪ
ተምሯል፡፡
በአዲስ አበባ ዪኒቨርሲቲና ራክማኖቭ ኮሌጅ ትወናን
አስተምሯል፡፡
የሲሳይ ንጉሱን ልቦለድ /ግርዶሽ/ ወደ ፊልም በመቀየርአዘጋጅቷል፤ ተውኗል፡፡
የሸክስፒርን ስራዎች በተለይም በጫንያለው
ወልደጊዮርጊስና ቴዎድሮስ ተሰማ የተተረጎመውን
ተጫወቷል፡፡
በተለይም በፀጋዬ ገብረ መድህን ስራዎች በዘመኑ እጅግድንቅ ብቃት ያሳየባቸውን የእናት ዓለም ቀኑ እና ሀሁበስድስት ወር ቴአትሮች ገፀባህሪያት በብሔራዊ ቴአትርተውኗል፡፡
ሀምሌትን አዘጋጀቷል፡፡
ከፍቃዱ ተክለማሪያም በፊት ቴዎድሮስን ሆኖ ተወኗል፡፡
ጊታር በድንቅ ብቃት ይጫወት ነበር፡፡
በሲዲ ያልተለቀቁ የእንግሊዝኛ ዘፈኖች አሉት፡፡ ከምንም በላይ ግጥም በማራኪ አቀራረብ በማንበብ
ይወደድ የነበረው አነጋፋው አርቲስት ሀይማኖት ዓለሙበመድረክ መምራትም ተወዳጅ ነበር፡፡
ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በማስታወቂያው ዘርፍ ተሰማርቶእየሰራ የነበረው ሀይማኖት ባደረበት ህመም ከዚህ ዓለምተለይቷል፡፡

ኤርትራዊው ባል ኢትዮጵያዊት ሚስቱን ገደለ፡፡

Admas News Husband Killed his Wife ...

Stockholm:- Marta Bogale has been living in Stockholm, Sweden for 23 years, her husband, whose name is not mentioned, came to Sweden 6 years ago from Asmara, Eritrea. They knew each other when they used to work on the same company in Stockholm.

After they started dating, they eventually got married and moved together. She is 32 and he is 29. As sources told Admas Radio, after they started to live together, they tried to have a wedding ceremony 2 years ago but the ceremony was postponed on his request for unknown reasons.

Recently, in August 2014, She gave a birth to a baby boy. But 3 weeks after she gave a birth, Police said the husband stabbed her repeatedly to death. The news was a shock to the Ethiopian Community in Stockholm. Her father, who saw her body, fainted but recovered in the hospital the next day. The husband sent to jail and her body was buried in "Heliga Korsets kapell Skogskyrkogarden" cemetery in Stockholm.

Reason for killing is not known yet. (Source Admas Radio ATLANTA)
[Pic. The couples during the good times]

Source: Admas News Atlanta

Thursday, September 18, 2014

My fiance who came from Ethiopia to U.S is pregnant from her ex-boyfriend

http://www.amharictube.com/article_read.php?a=536
Read in English: http://soderetimes.com/?p=6017
እጮኛዬ ከኢትዮጵያ ወደ አሜሪካ ስትመጣ ከቀድሞ ጓደኛዋ አርግዛ መጣች
ምንጭ አድማስ ዜና - ትርጉም በሶደሬ
ከ 17 ወር በፊት ኢትዮጵያ ለአንድ ወር እረፍት ሄጄ ነበር። እና ከአንድ ልጅ ጋር እተዋወቃለሁ። በጣም ሰለወደድኳት እርፍቴን በሁለት ወር አራዝምኩኝ። ከመምጣቴ በፊት የእንጋባ ጥያቄ አቀርብኩላት። እሷም ተስማማች።... See More

Tuesday, September 16, 2014

13-year-old boy | Read More at .... http://goo.gl/S8BAc4 | የ31 ዓመቷ የቤት ሰራተኛ ከ13 ዓመት ታዳጊ አረገዘች በባህሬን የቤት ሰራተኛ የሆነችው የ32 ዓመቷ ፊሊፒናዊት የቤት ሰራተኛ የ13 ዓመት እድሜ ካለው የአሰሪዎቿ ልጅ አርግዛለች፡፡ የቤት ሰራተኛዋ በመጀመሪያ በልጁ እንደተደፈረች ብትናገርም በኋላ ላይ ግን በፍላጎቷ ድርጊቱን መፈጸሟን ተናግራለች፡፡ የ13 ዓመቱ ታዳጊ በቤሩት ‹‹ወጣቱ የልጅ አባት›› ይሆናልም ተብሏል፡፡ የ31 ዓመቷ የቤት ሰራተኛ ከ13 ዓመቱ የአሰሪዎቿ ልጅ ጋር በድብቅ ግንኙነት ፈጥራ እንደነበር አምናለች የተባለ ሲሆን እርግዝናዋንም ለመደበቅ ብዙ ትራ እንደነበረ ተነግሯል፡፡

Maid impregnated by 13-year-old boy

A 32-year-old Indonesian housemaid in Manama gave birth to a baby boy after she was impregnated by her employer’s 13-year-old son, the youngest father in Bahrain.

The maid, who is on trial in the Gulf island nation, had first claimed the boy raped her, but changed her statements after she was pressed by police investigators.

The boy’s lawyer Ibtisam Al Sabbagh, quoted by CNN Arabia satellite TV news channel, said the maid had managed to hide her pregnancy from her employers for several months before she was about to board a flight for her home country.

“But she went into premature labour before her travel. She delivered herself in the bathroom at her employer’s home,” she said.

“She had first claimed she was raped by the boy, who is considered a child, but it emerged later that she had a relationship with him.”

emirates247

Sunday, September 14, 2014

ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ 17 የውጭ ዜጎች ክስ ተመሠረተባቸው

• ከ95 ሚሊዮን ብር በላይ የገቢ ንግድ ግብርና ቫት ባለመክፈላቸው ተከሰዋል • ከ716 ሚሊዮን ብር በላይ ምንጩንና ዝውውሩን ደብቀዋል ተብሏል • ከ104 ሚሊዮን ብር በላይ በሕገወጥ መንገድ መገኘቱ ተገልጿል
newsየፀና የንግድ ፈቃድ ሳይኖራቸው የንግድ ሥራ በመሥራት፣ የንግድ ትርፍ ግብር፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ ባለመክፈል፣ በሕገወጥ መንገድ የተገኘን ገንዘብን ሕጋዊ አስመስሎ በማቅረብና ሐሰተኛ ሰነዶችን በማቅረብ ወንጀል የተጠረጠሩ የሲሪላንካ፣ የህንድ፣ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ፣ የጂቡቲ፣ የኒውዚላንድና ኢትዮጵያውያን 17 ግለሰቦች ክስ ተመሠረተባቸው፡፡
የገቢ ግብርና ቫት ባለመክፈል፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ምንጭና ዝውውር በመደበቅና በሕገወጥ መንገድ በመያዝ ተከሰዋል፡፡
የፌዴራል ግለሰቦች ዓቃቤ ሕግ ጳጉሜን 4 ቀን 2006 ዓ.ም. በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተረኛ ችሎት ክስ የመሠረተባቸው፣ ተጠርጣሪዎች ኢትዮጵያውያን አሽረፍ አወል አብዶና በሥራ አስኪያጅነት የሚመሩት አካፔ ኢምፔክስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር፣ የሲሪላንካ ዜጋ የሆኑት ሂትራጅግ ያሳንታ ሱሬንድራናታ፣ ፕላንዋታጅ አሲታ፣ ቦፒ ጊድራ አጅት፣ አሳንታ ኡዳያ፣ ኩሩፑ አራችችግ፣ የህንድ ዜግነት ያላቸው አንኪት ሙኪሽ መሂታ፣ አሾክ ሞሃንላል፣ ኩማር ኤም፣ ቪሻል ኩማርና ሙኒሽ ኩማር፣ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ ዜግነት ያላቸው መሐመድ ሽፋን መሐመድ፣ ኦቶ ወርልድ ኢንተርናሽናል ፍሪዞን ኩባንያና ዱባይ ኦቶ ጋላሪ ኤልኤልሲ፣ የኒውዚላንድ ዜጋ ሱሀስ ፓራሳድና የጅቡቲ ዜግነት ያላት ሲና መሐመድ መሐሙድ ይባላሉ፡፡
ተጠርጣሪዎቹ በተለይ ዱባይ ኦቶ ጋለሪ ኤል.ኤል.ሲና ኦቶ ወርልድ ኢንተርናሽናል ፍሪዞን ኩባንያዎች፣ ኢትዮጵያ ውስጥ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የሚገኘውን አካፔ ኢምፔክስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር እንደ ሽፋን በመጠቀም የወንጀል ድርጊት መፈጸማቸውን ክሱ ያብራራል፡፡
የሲሪላንካ ዜግነት ያላቸው ሂትራጅግ ያሳንታ ሱሬንድራናታ ሂትያራጅጅ (ሱሬንድራ)ና ፕላን ዋታጅ አሲታ ሳራናታ ፔሬር (አሲታ) ድርጅቶችን በሚመለከት ሁለት የሲሪላንካ ዜጐች በኢትዮጵያ የዱባይ ጋለሪ መሪና ረዳት መሪ በሚል ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውንም ክሱ ያስረዳል፡፡ ዱባይ ኦቶ ጋለሪና ኦቶ ወርልድ ኢንተርናሽናል ኩባንያዎች፣ በኢትዮጵያዊው አሽረፍ አወልና የጅቡቲ ዜግነት ባላት ሲና መሐመድ ባለቤትነት የተቋቋመውን አካፔ ኢምፔክስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበርን በሽፋንነት በመጠቀም፣ ሐሰተኛ የሥራ ውል መፈራረማቸውም በክሱ ተጠቅሷል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ ምንም ዓይነት የፀና የሥራ ፈቃድ ሳይኖራቸው፣ ለኢትዮጵያውያን ብቻ የተከለለና ለውጭ ዜጎች ባልተፈቀደ የንግድ ሥራ ዘርፍ በመሰማራት፣ የባጃጅ ምርትና መለዋወጫ በቀጥታ ከዱባይ ወደ አገር ውስጥ ሲያስገቡ እንደነበር ክሱ ያስረዳል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ ጂቡቲ ውስጥ ከሚገኝ የንግድ ድርጅት ኤስዲሲ በርበራ ፍሪዞን ኩባንያን በመጠቀም በጂቡቲ በኩል ወደ ኢትዮጵያ በማስገባት፣ በኢትዮጵያ በሚገኙ ክልሎች፣ ዞኖችና የወረዳ ከተሞች በመዘዋወር የገበያ ጥናትና ሌሎች ተያያዥ የንግድ ሥራዎችን በመሥራት ለዱባይ ኦቶ ጋለሪ ኤልኤልሲ ሪፖርት ሲያደርጉ መገኘታቸውን ክሱ ያብራራል፡፡
ሌሎቹ ተጠርጣሪዎች ኢትዮጵያ ውስጥ በተቋቋመው አካፔ ኢምፔክስ ተቀጣሪ ሠራተኞች በመምሰል፣ ሐሰተኛ የሥራ ቅጥር ውል በመፈራረምና በድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ ኢትዮጵያዊው አቶ አሽረፍ አወልና በድርጅቱ ተጠያቂነት በሌላ የሥራ መደብ ፈቃድ በማውጣት ሲጠቀሙ እንደነበርም ክሱ ይገልጻል፡፡
ህንዳዊው አሾክ ሞሃንላል ሻርማና ኒውዚላንዳዊው ሱሀስ ፓራሳድ በቱሪስት ቪዛ ወደ አገር ውስጥ ገብተው፣ ያለምንም የሥራ ፈቃድ የባጃጅ መለዋወጫ ሽያጭ ንግድ ሥራ ውስጥ በመሰማራት በክልሎች በሚገኙ የዞንና የወረዳ ከተሞች በመዘዋወርና የገበያ ጥናት በማድረግ፣ ለዋና ድርጅታቸው ሪፖርት ሲልኩ መገኘታቸውን ክሱ ያስረዳል፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ ያቋቋሙትን አካፔ ኢምፔክስ በሽፋንነት በመጠቀም ለኢትዮጵያውያን ባለሀብቶች ብቻ የተከለለና ለውጭ ዜጎች በማይፈቀድ የአስመጭነት፣ የጅምላና የችርቻሮ ንግድ ሥራ ውስጥ ተሰማርተው መገኘታቸውንና ምንም ዓይነት የሥራ ፈቃድና የፀና የንግድ ፈቃድ ሳይኖራቸው ሽፋን በመስጠት፣ በቱሪስት ቪዛ ብቻ የባጃጅ ንግድ ሥራ እንዲሰማሩ መደረጋቸውን ክሱ ያብራራል፡፡
አካፔ ኢምፔክ፣ ዱባይ ኦቶ ጋለሪ ኤልኤልሲና ኦቶ ወርልድ ኢንተርናሽናል ፍሪዞን ኩባንያዎች ከቂርቆስ ክፍለ ከተማ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥሮችን የወሰዱ ቢሆንም፣ የፀና የንግድ ፈቃድ ሳይኖራቸው ለውጭ ባለሀብት የማይፈቀድ ሥራ ላይ በመሰማራት ካገኙት ገቢ ግብር አለመክፈላቸውን ክሱ ያብራራል፡፡ በመሆኑም ሐሰተኛ ሰነድ በማቅረብ ከ11 ሚሊዮን ብር በላይ የገቢ ንግድ ግብርና ተጨማሪ እሴት ታክስ አለመክፈላቸውን ክሱ ይጠቁማል፡፡ ከ416 ሚሊዮን ብር በላይ የሚሆን ገንዘብ ምንጩንና ዝውውሩን መደበቃቸው ተጠቅሷል፡፡ እንዲሁም ከ104 ሚሊዮን ብር በላይ በኢትዮጵያዊው አሽረፍ አወልና በድርጅቱ አካፔ ኢምፔክስ ስም በተለያዩ ባንኮች በማስቀመጥ፣ በሕገወጥ መንገድ የተገኘን ገንዘብ ሕጋዊ አስመስለው ማቅረባቸውን ክሱ ይዘረዝራል፡፡
ህንዳዊው ቪሻል ኩማር ላክሃኒ ደግሞ የባጃጅ መገጣጠሚያና ማምረቻ ንግድ የሥራ ዘርፍ፣ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኤጀንሲ የኢንቨስትመንት ፈቃድና የንግድ ፈቃድ በማውጣት፣ እንዲሁም ኤሽያ አፍሮ አውቶሞቢልስ በሚል ከንግድ ሚኒስቴር በተሰጠው የንግድ ስያሜ ቪሻል ኩማር ላክሀኒ የሚል ድርጅት ማቋቋሙን ክሱ ይጠቁማል፡፡ ነገር ግን የመገጣጠሚያ ፋብሪካውን ሳያቋቁምና ምንም ዓይነት የአስመጪነት፣ የአከፋፋይነትና የችርቻሮ የፀና የንግድ ፈቃድ ሳይኖረው፣ ባጃጅ ከውጭ አገር በማስመጣት ሳይገጣጠም በጅምላና በችርቻሮ ሲሸጥ እንደነበር በክሱ ተካቷል፡፡ ተጠርጣሪው ከ84 ሚሊዮን ብር በላይ የገቢ ግብርና ተጨማሪ እሴት ታክስ ካለመክፈሉም በላይ፣ በሕገወጥ ንግድና ግብር ሲሠራ ያገኘውን ከ330 ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ ገንዘብ፣ ከወንጀል ተጠያቂነት ለማምለጥ በማሰብ የገንዘቡን ምንጭና ዝውውር መደበቁን ክሱ ያብራራል፡፡
የጂቡቲ ዜግነት ያላት ተጠርጣሪ ሲና መሐመድ መሐሙድ በተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ በዱባይ የኢትዮጵያ ቆንሲላ ጽሐፈት ቤት ቀርባ፣ ‹‹የቤት እመቤት›› የሚል ሐሰተኛ መረጃ በመስጠት መታወቂያ በማግኘት ስትገለገልበት በመክረሟና ሐሰተኛ የሆነ ኦፊሴላዊ ሰነድ በማጭበርበር ማግኘት ወንጀል መከሰሷን የዓቃቤ ሕግ ክስ በዝርዝር ያሳያል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ በአጠቃላይ ከ95 ሚሊዮን ብር በላይ የገቢ ንግድ ግብርና ቫት ባለመክፈል፣ ከ716 ሚሊዮን ብር በላይ ምንጩንና ዝውውሩን በመደበቅ፣ እንዲሁም ከ104 ሚሊዮን ብር በላይ በሕገወጥ መንገድ በመያዝ ክስ ተመሥርቶባቸዋል፡፡
የተጠርጣሪዎቹ ጠበቆች ለደንበኞቻቸው የዋስትና መብት እንዲጠበቅላቸው በጽሑፍ ለፍርድ ቤቱ በማቅረባቸው፣ ዓቃቤ ሕግ ለጥያቄው በጽሑፍ ምላሽ እንዲሰጥ ለመስከረም 6 ቀን 2007 ዓ.ም. ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡

Monday, September 8, 2014

ኢህአዴግ በአንድ አመት ውስጥ ለተለያዩ ዝግጅቶች ከ900 ሚሊዮን ብር በላይ ማውጣቱ ተሰማ

Today, September 08, 2014, 
ጳጉሜን ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአለፈው አንድ አመት ውስጥ ኢህአዴግ መራሹ መንግስት ለፓርቲው የፖለቲካ ስራ የሚጠቅም ከመንግስት ባጀት ከ900 ሚሊዮን ብር ያላነሰ ገንዘብ ማውጣቱን ምንጮች ገለጹ።

ለብሄር ብሄረሰቦች ቀን፣ ለባንዲራ ቀን፣ ለመከላከያ ቀን፣ ለተለያዩ የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች የፖለቲካ ስልጠና፣ ከ100 ሺ በላይ ለሚሆኑ የኢህአዴግ አባላት ስልጠና፣ ለፖሊስ ሰራዊት የተሰጠው ስልጠና፣ እንዲሁም በተለያዩ ታሃድሶ የሚል ስያሜ በተሰጣቸው ስልጠናዎችና ስብሰባዎች ከመንግስት ባጀት እስከ 900 ብር ወጪ መደረጉን እስካሁን የተሰባሰቡት የወጪ ደረሰኞች እንደሚያሳዩ ምንጮች ገልጸዋል።

አንዳንድ ወጪዎችን ክልሎች ቢያወጡዋቸውም ፣ ወጪው ከመንግስት ባጀት የሚሸፈን መሆኑን የጠቀሱት ምንጮች፣ አሃዙ ተጠቃሎ ሲታወቅ ወጪው ከዚህም በላይ ሊሆን እንደሚችል ገልጸዋል።

ገዚው ፓርቲ ለራሱ የፖለቲካ ስራ በተለያዩ ሰበቦች ገንዘብ ከመንግስት ካዝና ማውጣት መቀጠሉ፣ ታክስ ከፋዩ ህዝብ በተዘዋዋሪ መንገድ ሳይፈልግ ፓርቲውን እዲደግፍ እያደረገው መሆኑንና የአገሪቱ አጠቃላይ ኦዲተሮችም ይህን ወጪ እንደመንግስት ወጪ በመያዝ ፓርቲውን ተጠያቂ ለማድረግ እንዳልቻሉ ምንጮች አክለው ተናግረዋል።

በተለይ የብሄር ብሄረሰቦች ፣ የባንዲራ እና የመከላከያ ቀን በሚባሉት ዝግጅቶች የአንድ አካባቢ ሰዎች ተሰባስበው እነሱ በመሰረቱት የዝግጅት ኩባንያ ዝግጅት በማዘጋጀት ከፍተኛ ገቢ እንደሚያገኙ የጠቆሙት ምንጮች፣ እነዚህ ሰዎች ከመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በፈጠሩት ሽርክና የተለያዩ ሃሳቦችን
እያመጡና እና እያስጸደቁ ከፍተኛ የሆነ ገንዘብ በመመዝበር ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ግንባሩ ከዚህ ቀደም ለኤች አይ ቪ ቫይረስና ለሌሎችም በሽታዎች መከላከያ የሚመጡ ፈንዶችን ሲጠቀም መቆየቱን ያስታወሱት ምንጮች፣ በተለይ ግሎባል ፈንድ የተባለው አለማቀፍ ለጋሽ ድርጅት ለኢትዮጵያ ይሰጥ የነበረውን እርዳታ መቀነሱን ተከትሎ፣ ኢህአዴግ ሙሉ በሙሉ የመንግስትን ባጀት በመጠቀም
የፖለቲካ ስራ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል። አንዳንድ ዝግጅቶች በመንግስት ስም እውቅና ቢሰጣቸውም ዋና ተልእኮዋቸው የኢህአዴግን አብዮታ ዲሞክራሲ

ፖሊሲ ማንጸባረቅ መሆኑን ምንጮች አያይዘው ተናግረዋል።

Sunday, September 7, 2014

የለውጡ አካል መሆኛው ግዜው አሁን ነው

September 7/2014

እኔም አንዳርጋቸው ነኝ የሚል ድምፅ ከአጥናፍ እስከ አጥናፍ እያሰተጋባ ነው። ይሄን ድምፅ የሚያቆመው አንዳችም ምድራዊ ኃይል አልተገኘም። ኢትዮጵያዊ ባለበት ሥፍራ ሁሉ ይሄ ድምፅ ከፍ ብሎ እየተሰማ ነው። ይህንንም ተከትሎ “ላንቺ ነው ኢትዮጵያ፤ ላንቺ ነው ኢትዮጵያ” የሚለው መዝሙር በኢትዮጵያ ተራሮች እናት ላይ እየተዘመረ ነው። ፍትህ ተዋርዳለች፤እኩልነት ጠፍቷል፤ ነፃነት የለም ያሉ ምርጥ ኢትዮጵያዊያን ሳያቅማሙ አያቶቻቸው በተመላለሱበት ተራሮች ላይ ተሠማርተዋል። ሞትንም ንቀው ጋሻ አንስተዋል፤ ሰይፋቸውንም መዘዋል። ለፍትህ፤ ለዕኩልነት እና ለነፃነት የተመዘዘው ሰይፍ ከእንግዲህ ወደ ሰገባው እንደማይመለስ ህወሃቶች እንዲያውቁት እንፈልጋለን።
በኢትዮጵያችን ፍትህ ከጠፋ ብዙ ዘመን ሁኖታል። ከሁሉም ዘመን የህወሃቶች ዘመን ግን የተለየ ነው። ህወሃቶች ህግን ዜጎችን የማጥቂያ መሣሪያ አድርገው መጠቀማቸው ከሌሎች እንዲለዩ ያደርጋቸዋል። እነዚህ ቡድኖች ሥፍር ቁጥር የሌላቸው ቂም መወጣጪያ ህጎችን አውጥተዋል። እንዲህ በማድርጋቸውም ሠላም እናገኛለን ብለው ያስባሉ። የህወሃቶች አስተሳሰብ ደካማና እርባና ቢስ መሆኑን ከሚያሳዩ ተግባሮቻቸው መካከል አንዱ ይሄው በፍትህ ሳይሆን በህግ ብዛት ሠላም እናገኛለን ብለው ተስፋ ማድረጋቸው ነው። የህግ ብዛት ሠላምን አያስገኝም፤ ፍትህንም ማስፈን አይችልም። እንዲያውም ህግ በበዛ ቁጥር ፍትህ እየጎደለች እንደምትሄድ የህወሃቶች ድርጊት ደህና ምስክር ነው። እነርሱ ዜጎችን ለመበቀያ ብለው የሚያወጧቸው ጥቃቅን ህጎች እነርሱ “ህገ መንግስት” ብለው የሚጠሩትን የሚንዱ እና ፍትህን ዋጋ የሚያሳጡ ሁነው እያየናቸው ነው። የፀረ ሽብር ህጉ በህገ መንግስቱ የተቀመጠውን የዜጎችን የመናገር የመደራጀትና በሰላማዊ መንገድ የመንግስትን እኩይ ተግባራት የመቃወምን መብት የገፈፈ ነው። የፀረ ሙስና ህጉም ቢሆን እንዲሁ ነው። በፀረ ሙስና ህጉ የሚጠየቁ በህወሃት የተጠሉ ብቻ ስለመሆናቸው በሙስና የተጨማለቁት የህወሃት ሹማምንት ህያው ምስክሮች ናቸው። በህወሃቶች ህግ ሁሉም ዜጎች እኩል አይደሉም። ህወሃቶች ከሌሎች ይበልጣሉ። የህወሃቶች ምኞት እነርሱ ከህግ በላይ፤ ሌላው ህዝብ ከህግ በታች ሁነው ህወሃትን ተሸክመው እንዲኖሩ ነው። እንዲህ ዓይነቱን ኢ-ፍትሃዊነት መታገል ግዜው የሚጠይቀው ታሪካዊ ግዴታ ነው። መሪያችን አንዳርጋቸው ፅጌ የተነሳውም ህወሃቶች መሣቂያ መሳለቂያ ያደረጓትን ፍትህ ወደ ሚገባት ክብር ለመመለስ ነው። በአገራችን የህግ የበላይነት ሠፍኖ ጥቂቱ ብዙሃኑን ሳይጫን፤ ማንም ማንንም ሳይሸከም ሁሉም በህግ እና በፍትህ እኩል ሁኖ የሚኖሩባት ሠላም የበዛላት ሥፍራ እንድትሆን የመሪያችን የአንዳርጋቸው ምኞት ነው። ይሄን ምኞት ሚሊየኖች አንግበው ተነስተዋል።
ህወሃቶች አገራችንን አደጋ ላይ ከጣሉባቸው አንኳር ድርጊቶቻቸው መካከል አንዱ በዜጎች መካከል እየፈጠሩ ያሉት ግልፅ ልዩነት ነው። ህወሃቶች ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር እኩል ነን የሚል እምነት የላቸውም። የህወሃቶች ዕምነት እነርሱ ከሌላው ኢትዮጵያዊ ከፍ እንደሚሉና በዚያች አገር ውስጥ የተለየ መብት እንዳላቸው ነው። ለመገድልም፤ ለመዝረፍም፤ዜጎችን ለማሳቃየት እና ከአገር ለማባረርም መብቱ የእኛ ነው የሚል ጅላጅል እምነት አላቸው። ይህ የሞኝ እምነታቸው በዜጎች መካከል ቂመ በቀል ሊያተርፍ የሚችል አድሎዎ እንዲፈጥሩ አድርጓቸዋል። አድሎአቸውንም ይበልጥ የከፋ የሚያደርገው ህወሃቶች ሁሉን አድራጊ እኛ ነን ብለው ሲያበቁ የህወሃት የበላይነት የለም ብላችሁ እምኑ ብለው ዜጎችን መጫናቸው ነው። ይህ ድርጊታቸው ብዙ ዜጎችን አስቆጥቷል። ህወሃቶች ግን የዜጎችን ቁጣ የሚያይ ዓይን፤ የሚያስተውል ሂሊና ርቋቸዋል። በኢትዮጵያችን በህወሃቶች አማካኝነት እየተፈጠረ ያለው ግልፅ አድልዖ ለአገራችን ህልውና ከፍተኛ አደጋ ነው። በህዝብ መካከል አድልዖ መፈፀም እና ቂምና በቀልን መትከል የህወሃቶች የመኖሪያ ድንኳናቸው ሁኗል። መከፋፈልና አድልዖ ባለበት አገር ውስጥ ሠላም ይኖራል ማለት አይቻልም። አድልዎ የታላላቅ ግጭቶችና ለውጦች ጥሩ ምክንያት መሆኑን መርሳት አይገባንም።መሪያችን አንዳርጋቸውም ሆነ ግንቦት ሰባት ንቅናቄ የተነሳው እንዲህ በዜጎች መካከል የሚፈፀመውን አድልዖ ለማስቆምና ዜጎች በገዛ አገራቸው በእኩልነት የሚኖሩበትን ሁኔታ ለመፍጠር ነው። ይህ የእኩልነት ጥያቄ የግንቦት ሰባት ንቅናቄ ብቻ ሳይሆን የሁሉም ዜጎች ጥያቄ ሁኖ ከኢትዮጵያ እስከ ውጪ አገራት ድረስ እያሰተጋባ ነው።
ሌላው ህወሃቶች አገሪቷን እያዋረዱ ካሉበት ነገሮች መካከል አንዱ የነፃነት ጥያቄ ነው። እኛ ከመጣን በኋላ በኢትዮጵያ ነፃነት ሰፈነ እያሉ ያላዝናሉ። ህወሃቶች ከነፃነት ጋር ተያይዞ ሊመጣ የሚችለውን ኃላፊነት ለመረዳትና ለመሸከም ከፍተኛ የሆነ የአስተሳሰብ ድክመት አለባቸው። ከነፃነት ጋር የሚመጣውን ኃላፊነት ለመሸከም ብቻ ሳይሆን የነፃነትንም ትርጉም ለመረዳት ከፍተኛ የሆነ የእውቀት ማነስ ችግር ያለባቸው መሆኑም ይታወቃል። ራሳቸውን ከታሰሩበት የድንቁርና ሰንሰለት ማስፈታት ሳይችሉ ከሰሞኑ የከፍተኛ ተቋም ተማሪዎችን ሰብስብው የእኛን አብዮታዊ ዲሞክራሲ ካልስተማርናችሁ ትምህርታችሁን አትቀጥሉም ሲሉ ማሰብ ማቆማቸውን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳየን አንድ እውነት ሁኖ አግኝተነዋል። ማሰብ የሚችሉ ቢሆኑማ ኑሮ ነፃነት ማለት ‘የእናንተን አብዮታዊ ዲሞክራሲ መስማት አልፈልግም ማለትን’ እንደሚጨምር ያውቁ ነበር። ነፃነትን የማያውቁት ነፃ አውጪዎች ነን ባዮቹ ህወሃቶች ግን ተማሪው መስማት የማይፈልገውን አብዮታዊ ዲሞክራሲ አስገድደው እየጋቱት ይገኛሉ። ለሚቀጥለውም አርባና ሃምሳ ዓመት ስልጣኑን ለማንም አሳልፈን የምንሰጥ አይደለንም ሲሉ በድፍረት ተናግረዋል። የዚህ ሁሉ ድፍረት ምንጭ ህወሃቶችን የተፀናወታቸው እኔ ብቻ ከሚል ከንቱ አስተሳሰብ የመነጨው ስግብግብነታቸው መሆኑን መገነዘብ ያስፈልጋል።
እንግዲህ ፍትህ መቀለጃ ሁናለች፤ እኩልነት ተጓድሏል፤ ነፃነት ጠፍቷል የሚሉ ዜጎች ከሁሉም አቅጣጫዎች ድምፃቸውን እያሰሙ ነው። የህዝቡ ብሶትም ፅዋውን ሞልቶ እየፈሰሰ ነው፤ ቁጭቱም ከመቸውም ግዜ በላይ ግሏል። ከሰሞኑ በሃያ ስድስት ታላላቅ ከተሞች የተደረጉት ውይይቶችም ያሳዩን አንድ እውነት ህዝቡ ይበልጥ መቆጣቱን ነው። ቁጣውም የተገለፀበት መንገድም ሌላው አስደማሚ ጉዳይ ነው።“እኛም አንዳርጋቸው ነን” ሲሉ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው አሰምተዋል። ከእንግዲህ ፍርሃት ሆይ መወጊያህ ወዴት አለ የሚሉ ኢትዮጵያዊያን ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ላንቺ ነው ኢትዮጵያ፤ ላንቺ ነው ኢትዮጵያ እያሉ ዘምረዋል። ይሄ ለፍትህ፤ ለእኩልነትና ለነፃነት ለሚታገሉ ታጋዮች ተስፋ ሰጪ ምልክት ነው።
ህወሃቶች በሠላማዊ መንገድ ለሚደረገው ትግል መንገዱን ሲያደናቅፉ እሰከ ዛሬ ዘልቀዋል። አሁን ጭራሹን ገና ሃምሳ የመከራ ዘመን እየተመኙልን ነው። ይሄ ምኞታቸው ቅዥት ሁኖ እንደሚቀር እኛ ልናስታውሳቸው እንፈልጋለን። በዚያች አገር ለውጥ መምጣት አለበት። ለውጡ በዛፍ ላይ የተንጠለጠለ የጎመራ ፓፓያ አይደለም በራሱ ወደ ምድር የሚወርድ፤እኛ ራሳችን ልናወርደው የሚገባን እንጂ። ተፈላጊውን ለውጥ ለማምጣት እያንዳንዱ ዜጋ በቻለው መሣሪያና ባለው አቅም ሁሉ ለልውጡ ሳያቅማማ መታገል ይኖርበታል። ህወሃቶች ነፃነታችንን አይሰጡንም፤ ፍትህም ከእነርሱ እጅ የምትገኝ አይደለችም፤ እኩልነትንም የሚያውቁ አይደሉም እነዚህ ወርቃማ እሴቶች በትግል የሚገኙ ናቸው። እነዚህን ክቡር ስጦታዎች አስነጥቆ ዝም ያለ ወደ መታረጃው ሥፍራ የሚነዳ ከብትን ይመስላል። ብዙ ኢትዮጵያዊያን እንዲህ መሆንን የሚምርጡ አይደሉም። በየከተሞቹ በተደረገው ውይይት ከተገነዘብናቸው እውነቶች መካከል አንዱ ዜጎች ለፍትህ፤ለእኩልነት እና ለነፃነት አስፈላጊውን መሥዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆናቸውን ነው።
በህወሃት ዘመነ መንግስት የመከራ እንባችሁን በመዳፋችሁ የምታፍሱ፤ ህወሃት በአገሪቷ ላይ እያደረሰ ያለው የጥፋት ድርጊት የሚያነገበግባችሁ እና ምን እናድርግ መሪ አጣን የምትሉ ስሙን! መሪ ካጣችሁ እንዲህ አድርጉ “ራሳችሁ ተነሱና መሪ ሁኑ!”። ከምታምኗቸው ጥቂት ወዳጆቻችሁ ጋር ሁናችሁ ተደራጁ፤ አንዳችሁ አንዳችሁን አድምጡ፤ ጥሩ ተመሪ መሆን ከቻላችሁ ጥሩ መሪ ወጥቷችኋል ማለት ነው። የአገራችን ፈርጀ ብዙ ችግር በጥቂት ዜጎች ብቻ የሚቀረፍ አይደለም።የሁሉንም ቁርጠኛ ዜጎች ትግል የሚጠይቅ ነውና በየመንደራችሁ ተደራጅታችሁ የጎበዝ አለቃ መርጣችሁ ዘረኞችን፤ ዘራፊዎችንና አድሎዋዊ ሥርዓት የዘረጉባችሁን ታገሏቸው። እንዲህ ካደረጋችሁ ከእኛ ጋር ለመገናኘት መንገዱ ቀላል ይሆናል።
የግንቦት ሰባት ንቅናቄ ጥያቄ አጭርና ግልፅ ነው። ፍትህ፤ ነፃነትና እኩልነት በኢትዮጵያችን ይሰፈን ነው። የህወሃትን ዘረኝነትና አምባገነንነት የሚፀየፍ ሁሉ የንቅናቄያችን ደጋፊ ነው። እነዚህን ነገሮች በኢትዮጵያ ለማስፈን በሚችለው ሁሉ ርምጃ መውሰድ የጀመረ የንቅናቄያችን አካል ነው። እኛም ከጎኑ አለን። እንዲህ በማድረግ የማይቀረውን ለውጥ አናመጣለን። ለውጡ ይመጣል አንድም የተፈጥሮ ህግ ስለሆነ፤ አንድም ደግሞ እኛ ሳናቅማማ የፈለግነውን ለውጥ ለማምጣት ስለተነሳን።
ህወሃቶች መስልጠን የማይችሉ፤ ከአዲስ አስተሳሰብ ጋር ራሳቸውን ማዋሃድ የማይሆንላቸው ፍፁም ግትሮች መሆናቸውን በተዳዳጋሚ አይተናል። ይሄን ግትርነታቸውን እንደ ጀግንነት ይቆጥሩታል። በአገራችን ደህና አባባል አለች እንዲህ የምትል “ሞኝ አሸነፈ ምን ብሎ? እምቢ ብሎ” ይባላል። ህወሃቶችን በዚህ አባባል መግለፅ ሞኝ ያስመስላቸዋል እነርሱ ግን ሞኞች አይደሉም ጨካኞች እንጂ። የጭካኔያቸው ምንጭ ደግሞ በራሳቸው የማይተማመኑ ደካሞች መሆናቸው ነው። እነርሱ ከዛሬ ሠላሳ ዓመት በፊት በመስታወት ውስጥ ያዩትን የራሳቸውን ምሥል ዛሬም መልሰው ያንኑ ምሥል እያዩት ነው። ከሠላሳ ዓመት በኋላም ሊቀየሩ አልቻሉም። ከዚያ ካረጀው ምሥላቸው ላይ ዓይናቸውን ነቅለው ግዜው እና ሁኔታው የፈጠረውን በአካባቢያቸው ያለውን አዲስ ምሥል ለማየት አቅቷቸውል። ስለዚህ ህወሃቶችን ማስወገድ ግድ ነውና ሁሉም በያለበት ለሚመጣው ለውጥ ራሱን ያዘጋጅ፤ የለውጡም አካል ይሁን እንላለን።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !

Saturday, September 6, 2014

በኮ/ል አለበል አማረ የሚመራው የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ “ከግንቦት 7 ጋር አልተዋሃድኩም” አለ

(ፎቶ ከፋይል)
(ፎቶ ከፋይል)
በኢሳት ራድዮና ቲቪ ነሐሴ 28 ቀን 2014 ዓ.ም ከስልጣናቸው እንደተነሱ የተዘገበላቸው ኮ/ል አለበል አማረ የሚመራው የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ “እየተካሄደ ነው የሚባለው ውህደት ብዙ ችግር ያለበትና ከእውነትም የራቀ ነው” ሲል መግለጫ አወጣ።
(ፎቶ ከፋይል - የአማራ ዲሞክራቲክ ኃይል ጦር ኃይሎች መካከል የተወሰኑት)
(ፎቶ ከፋይል – የአማራ ዲሞክራቲክ ኃይል ጦር ኃይሎች መካከል የተወሰኑት)

በኮ/ል አለበል አበራ እንደሚመራው ንቅናቄው መግለጫ “የተወሰኑ የድርጅታችን ታጋዮች አሁንም በኤርትራ መንግስት እገታ ኤርትራ ይገኛሉ፤ እነዚሁን ታጋዮች የድርጅቱ አካል በማስመሰልና በማስገደድ ኢንተርቪው እንዲሰጡ በማድረግ የሕገ-ወጡ ተግባር ከማድረግ እንዲቆጠቡና የሂደቱንም አፈጻጸም የተቀዋወሙሙ የድርጅታችን የተወሰኑ ሶስት አመራሮችና ሁለት አመራሮችና ሁለት ካድሬዎች በኤርትራ መንግስት እስር ላይ መሆናቸውን የታወቀ በመሆኑ ይኸው አላስፈላጊ ሁኔታ እንዲስተካከል ለኤርትራ መንግስትና ለተባባሪዎቻቸው በጥብቅ ደጋግመን እናሳስባለን” ይላል። ኢሳት “የአማራ ዲሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ መሪውን ከሃላፊነት ማንሳቱን አስታወቀ” በሚል የሌላኛውን ወገን የአማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ጠቅሶ በዘገበው ዘገባ ላይ “ኮ/ል አለበል አማረ የድርጅቱ መስራችና ሊቀመንበር ሆነው ሲያገለግሉ መቆየታቸውን፣ ውጭ አገር ከሄዱም በሁዋላ ድርጀቱን በማጠናከር ከፍተኛ ሚና መጫወታቸውን” ካወሳ በሁዋላ፣ ድርጅቱ መስዋትነት እየከፈለበት ያለው የነጻነት ትግል በቶሎ ግቡን እንዲመታ መሬት ላይ ወርዶ መታገሉ የበለጠ ውጤታማ ያደርገዋል ተብሎ ስላሚታመን በተደጋጋሚ እንዲመጡ ቢነገራቸው ሊመጡ ባለመቻላቸውና አሁን ባለንበት ጊዜ ድርጅቱን ውጭ ሃገር ተቀምጦ መምራት ስለማይቻል ከድርጅቱ ሊ/መንበርነት ወርደው በአባልነት እንዲቀጥሉ በሙሉ ድምጽ ወስነናል ብለዋል።” ሲል መዘገቡን፤ የኮ/ል አለበል ወገን ይህን ዘገባ ተቃውሟል።
ሙሉ መግለጫውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ