Sunday, September 21, 2014

EthioSwedish Task Force Decorated woyane Ambassader with Rotten Fish &eggs

በስዊድን የኢትዮጵያ አምባሳደር ወ/ሮ ወይንሸትና ተላላኪዎቿ ላይ የገማ አሳ የተቀባ እንቁላል ተወረወረባቸው (ፎቶዎች እና ቪድዮ ይዘናል)




  • 134

 በስዊዲን የኢትዮጵያ አባሳደር ላይ የገማ አሳና እንቁላል እንዳይወረወርባቸው ሲከላከሉ የሚያሳይ ፎቶ

በስዊዲን የኢትዮጵያ አባሳደር ላይ የገማ አሳና እንቁላል እንዳይወረወርባቸው ሲከላከሉ የሚያሳይ ፎቶ
 በስዊዲን የኢትዮጵያ አባሳደር ላይ የገማ አሳ የተቀባ እንቁላል እንዳይወረወርባቸው ሲከላከሉ የሚያሳይ ፎቶ

በስዊዲን የኢትዮጵያ አባሳደር ላይ የገማ አሳና እንቁላል እንዳይወረወርባቸው ሲከላከሉ የሚያሳይ ፎቶ


ናቲ ማን ለዘ-ሐበሻ እንደዘገበው፦
“ለኢትዮጵያ ባለስልጣናት ሕዝብን ሃገር ቤት እየገደሉ ውጭ መጥቶ መዝናናት ካሁን በኋላ ፋሽኑ አልፏል” ይላሉ
በስዊድን ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን። ኢትዮጵያውያኑ ዛሬ በስዊድን የኢትዮጵያ አምባሳደርና በተላላኪዎቿ ላይ የገማ
አሳና እንቁላል ሲወረውሩባቸው ውለዋል። አምባሳደሯም ከነሃገር ባህል ልብሷ ሮጣ ስትገባ እና ተላላኪዎቿም ሲከላከሏት
የሚያሳይ ፎቶዎች እና ቪድዮዎች ተይዘዋል። በስዊዲን የኢትዮጵያ አምባሳደር ወ/ሮ ወይንሸት ታደሰ በኢትዮጵያውያኑ
በደረሰባት ከፍተኛ ተቃውሞና የገማ አሳ በተቀባ እንቁላል ውርወራ በመደናገጥ ስትሮጥ ያመሸች ሲሆን በዲያስፖራ ያለው
ኢትዮጵያዊም በገዢው ፓርቲ ባለስልጣናት እና በተባባሪዎቹ ዙሪያ ትዕግስቱ ያለቀ መሆኑን ያሳየበት ዕለት ነው።


አምባሳደሯ የሚገማ አሳ የተቀባ እንቁላል ውርወራውን ፈርተው ለረዥም ጊዜ የፖሊስ ሃይል እስኪመጣ ተቀምጠው ነበር። ተጨማሪ ፖሊስ ቢመጣም ከውርወራው ሊያስጥሏት አልቻሉም።


ከዚህ በፊት በኖርዌይ፣ በቴክሳስ፣ በሚኒሶታ፣ በዋሽንግተን ዲሲ፣ በሎስ አንጀለስ ካናዳ የወያኔ ባለልጣናት
በኢትዮጵያውያን ሊያደርጉት የነበረው ስብሰባ የተስተጓጎለባቸው ከመሆኑም በላይ በሄዱበት ቦታ ሁሉ ኢትዮጵያዊያኑ
እየተጋፈጧቸው ገዳይ እና አምባገነን መሆናቸውን ሲነግሯቸው በቪድዮ ዘ-ሐበሻ ማሳየቷ ይታወሳል።


በስዊድን የኢትዮጵያ አምባሳደር ወ/ሮ ወይንሸት ላይ የተወረወረው የገማ አሳ እና እንቁላል ውርወራ በቀጣይም
የወያኔ ባለስልጣናት በሄዱበት ቦታ ሁሉ እንደሚቀጥል በየከተማው ያሉ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን እያሳወቁ ነው፡፡


ዛሬ እንቁላል የተቀባ አሳ ከተወረወረባቸው የወያኔ ባለስልጣናት መካከል፡

1ኛ. ወ/ሮ ወይንሸት ታደሰ

2ማ. አቶ ዳንኤል ጠንክር

3ኛ. አቶ ሁሴን አህመድ

4ኛ. አቶ ተረፈ ቡርቃ

4ኛ. ወ/ሮ ሮማን አብዱልቃድር

5ኛ. አቶ ፈንታዬ ሮባ

6ኛ. ወ/ሮ ሮማን ሙሉጌታ ይገኙበታል።


ቪድዮውንም ይመልከቱ፦

No comments:

Post a Comment