
ለነሱ (ለማ/ቅዱሳን) የተሰጠው ስም ለእኔም ይገባኛል”(ክቡር አቶ ግርማ ሰይፉ፤ የፓርላማ አባል)ክቡር ሆይአኔ የአንድ እምነት አንድ ሀገር አራማጅ ነኝ መንግሥትበማኅበረ ቅዱሳን ላይ
ዘመቻ ጀመረ በሚል እሰጥ አገባእንደበዛ አውቃለሁ፡፡ በሌለኝ መረጃ የእኔን ስም እየጠቀሱሰዎች
ፖስት እንደሚያደርጉ ከሰዎች ብሰማም የእኔ ፌስቡክ ይህን አልገለፀልኝም፡፡ ለማንኛውም
መንግሥትበእምነት ላይ ዘመቻ ሲጀምር በኦርቶዶክስ ላይ በማኅበረ ቅዱሳን መስመር እንደነበር
ትዝ ይለኛል፡፡ሟቹ ጠቅላይ ሚኒሰትር አቶ መለስ ይህን አሰመልክተው ለሰጡት አሰተያየት
የሰጠሁትን ምላሽበድጋሚ ላጋራችሁ፡፡ ይህ ነው የእኔ አቋም፡፡ ይህ ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር ከገጠመ
እሰየው ነው፡፡ ለነሱየተሰጠው ስም ለእኔም ይገባኛል፡፡ የሰጠሁት ምላሽ እንደወረደ ይህን ይመስል
ነበር፡፡ብዙ ጉዳዮች እንደተርጓሚው እንደሚሆን መገመት ይቻላል። ነገር ግን “አንድ እምነት
አንድ ሀገር”ማለት ግን ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እንደተረጎሙት ሳይሆን፤
አንድ ሰው ሊኖረውየሚገባው አንድ እምነት ብቻ ነው (ሰኞ፤ ዕሮብና አርብ ሙስሊም ማክሰኞ፤
ሀሙስና ቅዳሜክርስቲያን፤ ወዘተ መሆን አይቻልም)። ይህ ደግሞ አምላካዊ ቃል ነው።
(እኔ ቀናተኛ አምላክ ነኝ ሲል)ይህ አምላካዊ ቃል ደግም የሚሰራው ለሚያምኑበት ነው፡፡
ቃልቻ ቤት እየሄዳችሁ ቤተ ክርስቲያንአትምጡ ማለት ነው፡፡ ሊኖረን የሚገባው አንድ እምነት ነው፡፡
በእርግጠኝነት ሙስሊም ሆኖምክርስቲያን መሆን አይቻልም። ስለዚህ ይህ ለአንድ እምነት የመገዛት
ፍልስፍና የሁሉም የእምነት ዘርፎችመለያ ነው፡፡ ጥንቆላ ብቻ ነው ይህንን የሚፈቅደው።
ይህ ደግም በሁሉም እምነቶች የተወገዘ የመጥፎመንፈስ ሥራ ነው፡፡ ስለዚህ እኔ ያለኝ አንድ እምነት ብቻ ነው፡፡
መፍክሬም ይኸው ነው፡፡
ከአንድ እምነት ጋር ተያይዛ የመጣችው የአንድ ሀገር ጉዳይ ነው፡፡ ይህ በእርግጥ አከራካሪ ነው፡፡
ከአንድ እምነት ጋር ተያይዛ የመጣችው የአንድ ሀገር ጉዳይ ነው፡፡ ይህ በእርግጥ አከራካሪ ነው፡፡
አንድአንድ ሀገሮች ጥምር ዜግነትን የሚፈቅዱ አሉ። ይህም ሆኖ እኔ በግሌ ኢትዮጵያ ከምትባል
ሀገርበሰተቀር ሌላ ሀገር የለኝም- እንዲኖረኝም አልፈልግም። ይህን አቋሜን ስገልፅ ግን እኔ
ኢትዮጵያዊ ነኝስል “ሌሎች ኢትዮጵያዊ አይደላችሁም አለ” ተብሎ ልከሰስ አይገባም፡፡
አንድ የእስልምና እምነትተከታይ ኢትዮጵያዊ ሊሆን እንደሚችል ብዥታ ኖሮብኝ
አያውቅም ወይም የሌላ ክርስትና እምነትተከታዮች ኢትዮጵያዊ እንደሆኑ አልጠራጠርም፡፡
ኢ-አማኒያንም ቢሆኑ፡፡
አንድ ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር አለችኝ ብዬ ነው ለዚህች ሀገር እድገት
አንድ ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር አለችኝ ብዬ ነው ለዚህች ሀገር እድገት
(ሁሉ አቀፍ እድገት ማለቴ ነው)የሚከፈል መሰዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ የሆኑኩት፡፡
ሌላ አማራጭ የለኝም - አማራጭ ያለው ግንካልተመቸው ወደዛኛው ሊሄድ ይችላል፡፡
ሁለት ጉርጓድ ያላት አይጥ እንደሚባለው፡፡ እኔ ግን ሀገሬአንድ እና አንድ ነች፡፡ ኢትዮጵያ፡፡
ይህ ማለት ግን በምንም መመዘኛ ይህች ሀገር የኔ ብቻ ነች ማለትአይቻልም፡፡ አይሆንምም፡፡
እኔ የአንድ እምነት እና አንድ ሀገር ባለቤት ነኝ፡፡
ምንጭ፦ የፌስቡክ ገጻቸው።
posted by Aseged Tamene
No comments:
Post a Comment