Tuesday, April 21, 2015

አ.አ ቡልጋሪያ ማዞሪያ አካባቢ ሐዘኑን ለመግለጽ አደባባይ የወጣው ሕዝብ በፖሊስ ተበተነ (ዜና ፎቶ)

addis ababa pro 7
addis ababa pro 4
addis ababa pro 3
addis ababa pro 2
addis ababa pro
addia ababa pro 1
“እኔም ዘ-ሐበሻ ነኝ” ያለ አንባቢያችን በፎቶ ግራፍ የላከልን መረጃ እው::
ዛሬ ጠዋት ሚያዝያ 13 2007 5፡30 ላይ በተለምዶ ቡልጋሪያ ማዞሪያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከጨርቆስ ወደ አፍሪካ ህብረት በሚወስደው መንገድ ላይ የጨርቆስ ወጣቶች በመሰባሰብ የISIS ጭካኔያዊ ተግባር እና በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ወገኖቻችን ላይ የሚደርሰውን ግፍ በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ቢሞክሩ በፀጥታ ኃይሎች በተፈጠረ ውክቢያ ሊበተኑ ችለዋል፡፡ ለማንኛውም በማያውቁት ጉዳይ ለተሰው ወገኖቻችን ነብስ ይማር!!

Tuesday, October 14, 2014

(ሰበር ዜና) ለ1ዓመት ከ6 ወር በላይ በእስር ሲሰቃዩ የቆዩት 12 ተማሪዎች እና 1 መምህር የ6 ወር እስራት ተፈረደባቸው

በእስር የቆዩበት ጊዜ ከተፈረደባቸው በመብለጡ ከእስር እንደሚፈቱ ተወስኗል!

ማክሰኞ ጥቅምት 4/2007


(ድምፃችን ይሰማ እንደዘገበው፡) ከ21 ወራት በፊት ከጅግጅጋ፣ ከሲቪል ሰርቪስ፣ ከባህር ዳር፣ ከጅማ፣ ከደሴ፣
ከሐዋሳና ከደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲዎች ታፍነው የታሰሩ 12 ሙስሊም ተማሪዎችና 1 አስተማሪ የስድስት ወር የእስር
ቅጣት ተበየነባቸው! በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ወንጀል ሕግ አንቀጽ 32/1/ሀ፣ አንቀጽ 38/1፣ እንዲሁም አንቀጽ 257/ሀ
ላይ በሰፈሩት አንቀጾች መሰረትነት የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ሃይማኖታዊ ስነስርአትና አለባበስን በሚመለከት ያወጣውን
የስነምግባር ደንብ በመቃወም የተለያዩ አደረጃጀቶችን በመፍጠር ‹‹በመላው አገሪቱ አመጽ በመቀስቀስ በሃይማኖት
ሽፋን በአገሪቱ ያለውን ሰላም ማወክ›› እና ‹‹የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎቹን በኃይል ለማስፈታት በመጣር›› የሚሉ
ክሶች ተመስርተውባቸው ክሳቸው በልደታ ፍርድ ቤት ከ18 ወራት በላይ ሲታይ የዘለቀው ተማሪዎች ዛሬ የመጨረሻ ብይን
በፍርድ ቤቱ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

(ሰበር ዜና) ለ1ዓመት ከ6 ወር በላይ በእስር ሲሰቃዩ የቆዩት 12 ተማሪዎች እና 1 መምህር የ6 ወር እስራት ተፈረደባቸው

መንግስት የበረታበትን የህብረተሰቡን ተቃውሞ ‹‹አስተነፍሳለሁ›› በሚል ዓላማ ከጥር 2005 ጀምሮ ከሚማሩባቸው
የተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች አፍሶ ለእስር የዳረጋቸው እነዚሁ ተማሪዎች ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ መስከረም 27/2007
በፍርድ ቤቱ የጥፋተኝት ውሳኔ የተሰጠባቸው ሲሆን የቅጣት ብይን ለመስጠት ለዛሬ ቀጠሮ ያስቀመጠው ፍርድ ቤትም
የስድስት ወራት እስርና ምክር እንዲሰጣቸው ወስኗል፡፡ በሃያዎቹ እድሜ መጀመሪያ ላይ የሚገኙት 13ቱ ተማሪዎች
በመንግስት ኃይሎች ታፍነው ሲወሰዱ የዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን ለማጠናቀቅ ጥቂት ጊዜያት ብቻ ይቀራቸው ነበር፡፡


በእነ እስማኤል ኑርሑሴን መዝገብ የተከሰሱትና ብይን የተሰጠባቸው ተማሪዎች እስማኤል ኑር ሁሴን፣ ሰይድ
ኢብራሂም፣ ሙሐመድ ሰይድ፣ ፈትሂያ ሙሐመድ፣ ኑርዬ ቃሲም፣ ያሲን ፈያሞ፣ መሃመድ አሚን፣ ዩሱፍ ከድር፣ ጣሂር
መሃመድ፣ መሃመድ ሰይድ፣ አብደላ መሃመድ፣ አብዲ ሙሐመድ እና ኢብራሂም ዩሱፍ ናቸው። ከተከሳሾቹ መካከል ብቸኛዋ
ሴት የህክምና ተማሪዋ ፈትህያም የክሱ ሰለባ ሆና በቃሊቲ እስር ያሳለፈች ሲሆን ከቤተሰቦቿ ጋር እንዳትገናኝም
በወህኒው ሀላፊዎች እቀባ ተጥሎባት ይገኛል፡፡


በግንቦት 2005 ክስ የተመሰረተባቸው እነዚሁ ተማሪዎች በተለያዩ ሰበብ አስባቦች ምክንያት ችሎቱ እየተጓተተ
በመቆየቱና የፍትህ ስርአቱ የዜጎችን መብት ማስከበር በማይችልበት ደረጃ በመኮላሸቱ ጥፋተኛ ሆነው ቢገኙ እንኳ
ክሳቸው ከሚያስፈርድባቸው በላይ በእስር እየቆዩ መሆኑን የህግ ባለሙያዎች ሲያሳስቡ ቆይተዋል፡፡ በዚህም ምክንያት
ፍርድ ቤቱ ዛሬ የስድስት ወር ቅጣት ሲበይን ተማሪዎቹ በእስር ከ21 ወራት በላይ (ከተወሰነባቸው ቅጣት 3 እጥፍ
በላይ) በቆዩበት ሁኔታ ላይ ነበር፡፡


እነዚህ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው በእምነታቸው ምክንያት ብቻ ከሌሎች ተማሪዎች ተነጥለው በድብደባ እና
በተንዛዛ የፍርድ ቤት አሰራር መንገላታታቸው ሳያንስ የጥፋተኝነት ውሳኔ መተላለፉ አስደንጋጭም አሳዛኝም ነው፡፡
በተለይም ተማሪዎቹ ከትምህርት ገበታቸው ተፈናቅለው ሊመረቁ የሚችሉበት ጊዜ ያለፈ እና የቀሪዎቹም የተራዘመ ሲሆን
አሁንም ቀጣይ የትምህርት እድላቸው ምን እንደሚሆን በውል አልታወቀም፡፡ በተማሪዎቹ ላይና በህዝቡ ላይ ለተዘነበለው
ፍትህ የህግ ስርአቱ ተዋንያንና አጠቃላይ አስፈጻሚው አካል ተጠያቂ ሊሆኑ እንደሚገባ እሙን ቢሆንም የፍትህ ስርአቱ
የመንግስት የፖለቲካ ማስፈጸሚያ ሸንጎ መሆኑ ሁሉንም ዜጋ ሊያሳስበው ይገባል፡፡


ህዝበ ሙስሊሙ እነዚህ ጀግና ተማሪዎች ይህን ሁሉ መስዋእትነት የከፈሉለትን ትግል ከዳር ለማድረስ ያለውን
ቁርጠኝነት እየገለጸ ከዚህ ሁሉ ስቃይ በኋላም ቢሆን ተማሪዎቹ እንዲፈቱ ውሳኔ መሰጠቱ ለቤተሰቦቻቸው እና በዱዓና
በጭንቀት ከጎናቸው ለቆመው ሁሉ መልካም ዜና መሆኑ አልቀረምና ለተማሪዎቹ እና ለቤተሰቦቻቸው ‹‹እንኳን ደስ
አላችሁ!›› እያለ ይገኛል!



ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!

ድምፃችን ይሰማ!

አላሁ አክበር!

Monday, October 13, 2014

Breaking News: ቴዲ አፍሮ ታስሮ ፍርድ ቤት ቀረበ

ዝነኛው ድምፃዊ ቴዲ አፍሮ በፌደራል ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን በቀረበበት ክስ ምክንያት ዛሬ ታስሮ ፍርድ ቤት ቀረበ፡፡ ድምፃዊው የቀረበበት ክስ ከስምንት ዓመት በፊት ከቀረጥ ነፃ ወደ ሃገር ውስጥ የገባችን ቢኤምደብሊው መኪና ገዝቶ ተገቢውን የቀረጥ ክፍያ ሳያጠናቅቅ ወደ ስሙ አዛውሯል የሚል መሆኑን የኢትዮጲካሊንክ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡
ድምፃዊው በዚሁ ክስ መሰረት ዛሬ ረፋድ በአራዳ ምድብ አንደኛ ወንጀል ችሎት ቀርቦ ክሱ ከታየ በኋላ ቀርቦ የዕለቱ ዳኛ 30 ሺህ ብር በማስያዝ በዋስ እንዲፈታ ትዕዛዝ ሰጥተዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜም የዋስ ሂደቱን ለመጨረስና ድምፃዊውን ለማስፈታት የቢሮ ሥራዎች እየተሰሩ እንደሆነ ታውቋል፡፡
ለቴዲ አፍሮ መከሰስ ምክንያት የሆነችው ይህች መኪና ከዚህ ቀደም በተቀጣበት የሰው ገጭቶ ህይወት ማጥፋት ወንጀል የተከሰሰባት ነበረች፡:http://www.zehabesha.com/amharic/wp-content/uploads/2014/08/teddy-afro.jpg

Tuesday, October 7, 2014

Ethiopian Maid pours hot water on handicapped child | Read More at ....http://goo.gl/Ov7kOW | በሳውዲ አረቢያ ኢትዮጵያዊቷ የቤት ሰራተኛ የአካል ጉዳተኛ የሆነቸውን የአሰሪዎቿን ልጅ በፈላ ውሀ አቃጠለች የቤት ሰራተኛዋ ኢትዮጵያዊት የአካል ጉዳተኛ በሆነችው የአሰሪዎቿ ልጅ ላይ የፈላ ውሃ በማፍሰስ ጉዳት አድርሳባታለች ተብሏል፡፡ ድርጊቱ ሲፈጸም ያየው የአካል ጉዳተኛዋ የ10 ዓመት እድሜ ያለው ወንድም በአቅራቢያው ወደ ሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ በመሄድ ጉዳዩን ለፖሊስ ካስረዳ በኋላ ኢትዮጵያዊቷ ወደ እስር ቤት ህጻኗም ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል፡፡ ... See More

Maid pours hot water on handicapped child

An Ethiopian housemaid waited for her Saudi employers to go out and poured boiling water on their little handicapped daughter, a newspaper reported on Monday.

The girl’s 10-year-old brother, who was at home in the northeastern town of Hafr Al Batin, rushed to the nearby police station and reported the maid, Sabq said.

Police arrested the maid while the child was taken to hospital suffering from burns in various parts of her body.

The paper said police questioned the maid on her motives for burning that little girl, whose age was not specified.

Source:emirates247

Sunday, September 21, 2014

EthioSwedish Task Force Decorated woyane Ambassader with Rotten Fish &eggs

በስዊድን የኢትዮጵያ አምባሳደር ወ/ሮ ወይንሸትና ተላላኪዎቿ ላይ የገማ አሳ የተቀባ እንቁላል ተወረወረባቸው (ፎቶዎች እና ቪድዮ ይዘናል)




  • 134

 በስዊዲን የኢትዮጵያ አባሳደር ላይ የገማ አሳና እንቁላል እንዳይወረወርባቸው ሲከላከሉ የሚያሳይ ፎቶ

በስዊዲን የኢትዮጵያ አባሳደር ላይ የገማ አሳና እንቁላል እንዳይወረወርባቸው ሲከላከሉ የሚያሳይ ፎቶ
 በስዊዲን የኢትዮጵያ አባሳደር ላይ የገማ አሳ የተቀባ እንቁላል እንዳይወረወርባቸው ሲከላከሉ የሚያሳይ ፎቶ

በስዊዲን የኢትዮጵያ አባሳደር ላይ የገማ አሳና እንቁላል እንዳይወረወርባቸው ሲከላከሉ የሚያሳይ ፎቶ


ናቲ ማን ለዘ-ሐበሻ እንደዘገበው፦
“ለኢትዮጵያ ባለስልጣናት ሕዝብን ሃገር ቤት እየገደሉ ውጭ መጥቶ መዝናናት ካሁን በኋላ ፋሽኑ አልፏል” ይላሉ
በስዊድን ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን። ኢትዮጵያውያኑ ዛሬ በስዊድን የኢትዮጵያ አምባሳደርና በተላላኪዎቿ ላይ የገማ
አሳና እንቁላል ሲወረውሩባቸው ውለዋል። አምባሳደሯም ከነሃገር ባህል ልብሷ ሮጣ ስትገባ እና ተላላኪዎቿም ሲከላከሏት
የሚያሳይ ፎቶዎች እና ቪድዮዎች ተይዘዋል። በስዊዲን የኢትዮጵያ አምባሳደር ወ/ሮ ወይንሸት ታደሰ በኢትዮጵያውያኑ
በደረሰባት ከፍተኛ ተቃውሞና የገማ አሳ በተቀባ እንቁላል ውርወራ በመደናገጥ ስትሮጥ ያመሸች ሲሆን በዲያስፖራ ያለው
ኢትዮጵያዊም በገዢው ፓርቲ ባለስልጣናት እና በተባባሪዎቹ ዙሪያ ትዕግስቱ ያለቀ መሆኑን ያሳየበት ዕለት ነው።


አምባሳደሯ የሚገማ አሳ የተቀባ እንቁላል ውርወራውን ፈርተው ለረዥም ጊዜ የፖሊስ ሃይል እስኪመጣ ተቀምጠው ነበር። ተጨማሪ ፖሊስ ቢመጣም ከውርወራው ሊያስጥሏት አልቻሉም።


ከዚህ በፊት በኖርዌይ፣ በቴክሳስ፣ በሚኒሶታ፣ በዋሽንግተን ዲሲ፣ በሎስ አንጀለስ ካናዳ የወያኔ ባለልጣናት
በኢትዮጵያውያን ሊያደርጉት የነበረው ስብሰባ የተስተጓጎለባቸው ከመሆኑም በላይ በሄዱበት ቦታ ሁሉ ኢትዮጵያዊያኑ
እየተጋፈጧቸው ገዳይ እና አምባገነን መሆናቸውን ሲነግሯቸው በቪድዮ ዘ-ሐበሻ ማሳየቷ ይታወሳል።


በስዊድን የኢትዮጵያ አምባሳደር ወ/ሮ ወይንሸት ላይ የተወረወረው የገማ አሳ እና እንቁላል ውርወራ በቀጣይም
የወያኔ ባለስልጣናት በሄዱበት ቦታ ሁሉ እንደሚቀጥል በየከተማው ያሉ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን እያሳወቁ ነው፡፡


ዛሬ እንቁላል የተቀባ አሳ ከተወረወረባቸው የወያኔ ባለስልጣናት መካከል፡

1ኛ. ወ/ሮ ወይንሸት ታደሰ

2ማ. አቶ ዳንኤል ጠንክር

3ኛ. አቶ ሁሴን አህመድ

4ኛ. አቶ ተረፈ ቡርቃ

4ኛ. ወ/ሮ ሮማን አብዱልቃድር

5ኛ. አቶ ፈንታዬ ሮባ

6ኛ. ወ/ሮ ሮማን ሙሉጌታ ይገኙበታል።


ቪድዮውንም ይመልከቱ፦

በስዊድን የኢትዮጵያ አምባሳደር ወ/ሮ ወይንሸትና ተላላኪዎቿ ላይ የገማ አሳ የተቀባ እንቁላል ተወረወረባቸው (ፎቶዎች እና ቪድዮ ይዘናል)





  • 134

 በስዊዲን የኢትዮጵያ አባሳደር ላይ የገማ አሳና እንቁላል እንዳይወረወርባቸው ሲከላከሉ የሚያሳይ ፎቶ

በስዊዲን የኢትዮጵያ አባሳደር ላይ የገማ አሳና እንቁላል እንዳይወረወርባቸው ሲከላከሉ የሚያሳይ ፎቶ
 በስዊዲን የኢትዮጵያ አባሳደር ላይ የገማ አሳ የተቀባ እንቁላል እንዳይወረወርባቸው ሲከላከሉ የሚያሳይ ፎቶ

በስዊዲን የኢትዮጵያ አባሳደር ላይ የገማ አሳና እንቁላል እንዳይወረወርባቸው ሲከላከሉ የሚያሳይ ፎቶ

ናቲ ማን ለዘ-ሐበሻ እንደዘገበው፦ “ለኢትዮጵያ ባለስልጣናት ሕዝብን ሃገር ቤት እየገደሉ ውጭ መጥቶ መዝናናት ካሁን በኋላ ፋሽኑ አልፏል” ይላሉ በስዊድን ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን። ኢትዮጵያውያኑ ዛሬ በስዊድን የኢትዮጵያ አምባሳደርና በተላላኪዎቿ ላይ የገማ አሳና እንቁላል ሲወረውሩባቸው ውለዋል። አምባሳደሯም ከነሃገር ባህል ልብሷ ሮጣ ስትገባ እና ተላላኪዎቿም ሲከላከሏት የሚያሳይ ፎቶዎች እና ቪድዮዎች ተይዘዋል። በስዊዲን የኢትዮጵያ አምባሳደር ወ/ሮ ወይንሸት ታደሰ በኢትዮጵያውያኑ በደረሰባት ከፍተኛ ተቃውሞና የገማ አሳ በተቀባ እንቁላል ውርወራ በመደናገጥ ስትሮጥ ያመሸች ሲሆን በዲያስፖራ ያለው ኢትዮጵያዊም በገዢው ፓርቲ ባለስልጣናት እና በተባባሪዎቹ ዙሪያ ትዕግስቱ ያለቀ መሆኑን ያሳየበት ዕለት ነው።
አምባሳደሯ የሚገማ አሳ የተቀባ እንቁላል ውርወራውን ፈርተው ለረዥም ጊዜ የፖሊስ ሃይል እስኪመጣ ተቀምጠው ነበር። ተጨማሪ ፖሊስ ቢመጣም ከውርወራው ሊያስጥሏት አልቻሉም።
ከዚህ በፊት በኖርዌይ፣ በቴክሳስ፣ በሚኒሶታ፣ በዋሽንግተን ዲሲ፣ በሎስ አንጀለስ ካናዳ የወያኔ ባለልጣናት በኢትዮጵያውያን ሊያደርጉት የነበረው ስብሰባ የተስተጓጎለባቸው ከመሆኑም በላይ በሄዱበት ቦታ ሁሉ ኢትዮጵያዊያኑ እየተጋፈጧቸው ገዳይ እና አምባገነን መሆናቸውን ሲነግሯቸው በቪድዮ ዘ-ሐበሻ ማሳየቷ ይታወሳል።
በስዊድን የኢትዮጵያ አምባሳደር ወ/ሮ ወይንሸት ላይ የተወረወረው የገማ አሳ እና እንቁላል ውርወራ በቀጣይም የወያኔ ባለስልጣናት በሄዱበት ቦታ ሁሉ እንደሚቀጥል በየከተማው ያሉ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን እያሳወቁ ነው፡፡
ዛሬ እንቁላል የተቀባ አሳ ከተወረወረባቸው የወያኔ ባለስልጣናት መካከል፡
1ኛ. ወ/ሮ ወይንሸት ታደሰ
2ማ. አቶ ዳንኤል ጠንክር
3ኛ. አቶ ሁሴን አህመድ
4ኛ. አቶ ተረፈ ቡርቃ
4ኛ. ወ/ሮ ሮማን አብዱልቃድር
5ኛ. አቶ ፈንታዬ ሮባ
6ኛ. ወ/ሮ ሮማን ሙሉጌታ ይገኙበታል።
ቪድዮውንም ይመልከቱ፦