ሀገር እያለው ሀገር እንደሌለው በሞት ለሚቀጣው ህዝብስ ተተያቂው ማነው? በድብደባ በእስር ለሚገላታው ወገን አረ
ማንነው ተተያቂው? ለዚህ ሁሉ ተተያቂው ማነው? አረ ወገኖች የሀገር
የወገን ያለ! እያለ ነው፡ ህዝባችን ግን ማን አለን ሀገር መሪ ቢኖረን ወገኖች በሳውዲ ሲሰቃዩ ሲገደሉ ሲቆረጡ መንግስት ለህዝቡ
መብት መቆም አልቻለም::
ላለፉት ሁለት አስርት አመታት በማን አለብኝነት ህዝብን ማሰር ማሰቃየት መግደል ግለሰቦችንና
ቡድኖችን ማንቃሸሽ መሳደብ ስልጣንን ተገን አድርጎ የሀገርና የህዝብን ሀብት
መዝረፍ ለግላቸው ጥቅምና ስልጣን የሀገርንና የህዝብን
ጥቅም አሳልፎ መስጠትና የመሳሰሉትን ወንጀሎች ሲፈፅሙ ቆይተዋል:: ልክ ከዚህ በፊት እንዳየናቸው አምባገነን አፍሪካዊያን መሪዎች
በስልጣን ለመቆየትና የህዝብንና የሀገርን ሀብት ንብረት ለመዝረፍ ሲሉ
የወያኔ መንግስት የፈፅሙዋቸውና ያስፈፅሙዋችው ኢ-ሰብአዊና ኢ-ፍታዊ ድርጊቶች: የዘር ማጥፋት: የግለሰቦችን ነብስ ማጥፋት ወንጀሎች:
ሁሉም የመንግስት ባለስልጣናት በከፍተኛ ሙስና የጠገቡ ባለሀብቶች መሆን: ሀገሪቱዋ እስካሁን በምግብ እራስን ለመቻል ተቀረዑ የተባሉት
እስትራቴጂዎች ምንም ውጤታማ ሳይሆኑ ቀርተው በአስር ሚሊዮኖች ኢትዮጵያውያን
በተደጋጋሚ በከፍተኛ በርሀብ አለንጋ ከመገረፍ አለማዳናቸው: የህዝቡን ጥያቄ በአግባቡ ባለመመለሳቸው የወያኔ መንግስት ወደ ስነልቦናዊ
አእምሮአዊና ፖለቲካዊ ችግር ውስጥ ተዘፍቀዋል::
የወያኔ መንግስት ለስሙ ሀይማኖትና መንግስት ጣልቃ አይገባቡም እያለ ጆሮችንን በየቀኑ
ያደነቁረናል ነገር ግን በኦርቶዶክስና በእስልምና እምነት ድርጅቶች
ውስጥ በቀጥታ እጁን አስገብቶ በመጀመሪያ ለዘመናት ተቻችለውና ተከባብርው
የኖሩትን ከላይ የተጠቀሱትን የሁለቱን እምነቶች ተከታዮችን ጣልቃ
በመግባት እርስ በርሱ እንዲተላለቁ ለማድረግ ብዙ ስራዎች ተሰርተው ነበረ ነገር ግን ህብረተሰቡ ይህ ተግባር የወያኔ አኩይ ስራ እንደነበረ ስለተረዳ በትዝብት ተመልክቶታል:: በሁለተኛ ደረጃ ወያኔ በእምነቶች ውስጥ ጣልቃ መግባቱ ገሀድ የወጣበት በኦርቶዶክስ እምነት ውስጥ
የሚገኙትን ከፍተኛ የስልጣን ቦታዎችን የፈጣሪን የሚመለክባቸው ሳይሆን የወያኔን ጥቅም ለሚያስከብሩ ከአንድ ብሄር ለተሰበሰቡ ግለሰቦች አስረከበ::
የወያኔ መንግስት ህዝባዊ አመፅ የሚያስነሱ ናቸው በማለት በውሸት በተቀነባበረ ክስ በሺዎች የሚቆጠሩ ንጹሀን ዜጎች የተቃዋሚ
የፖለቲካ ድርጅት አባላቶች ደጋፊዎች የሰብአዊ መብት ተከራካሪዎች በሰብአዊ መብትና በማህበረሰብ ልማት ላይ የተሰማሩትን መንግስታዊ
ያልሆኑ ድርጅቶችን የግል ጋዜጣ ባለቤቶችና አምደኞች በየእስር ቤቶቹ
እያጎረ ነው። እነዚህ በየማጎሪያ ቤቶቹ የሚገኙትን እስረኞች ቁጥር በእጅጉ ከመጨመሩም በላይ ታስረው በሚገኙበት ቦታ
የሚፈጸመው እንግልት እና ስቃይ እጅግ በጣም ተባብሷል::
ሆኖም ግን ወያኔ የህዝቡን አመለካከት እና የወቅቱን የፓለቲካ እንቅስቃሴ ለመለወጥ ሲል
በአሸባሪዎች በማሳበብ ብዙ ሽብሮችን እየፈጠረ የፓለቲካውን ሂደት እንዲለውጥ በማድረግ ይሞክራል። ሆኖም ግን በተደጋጋሚ በመደረጉ
በህዝቡ አመኔታን ከማጣቱ የተነሳ ተቀባይነት ሊያገኝ አልቻለም።
አሁን የወያኔ አባላቶችና ደጋፊዎች የሚይዙትን የሚጨብጡትን ያጡበት ሰአት ላይ ይገኛሉ።
ትልቁ ችግራቸው እስካሁን በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ያደረሱትን ወንጀሎች ኢተፈጥሮአዊና ኢሰብአዊ ድርጊቶች የሀገርና የህዝብ ሀብትና ንብረት ዘረፋ ብሎም የግለሰቦችን የብሄርንና የሀገርን
ስምና ታሪክ ማጥፋትና ማበላሸትና የመሳሰሉ የውንብድና ተግባሮቻቸውን እንዴት ማጥፋት እንደሚችሉ የሚቻላቸውን ሁሉ ጥረት እያደረጉ
ነው። ነገር ግን የሄ የመንግስት የሀይል እርምጃ ፉከራ ድንፋታ መደነባበር የህዝባችንን የፍትህ የእኩልነትና የነፃነት ትግል ማቆም
አያስችለውም::
No comments:
Post a Comment