አቶ ሬድዋን ሁሴን በቨርጂኒያ ውርደት ገጠመው፤ ኢትዮጵያውያኑ ልክ ልኩን ነገሩት (ቪዲዮ)
ስንታየሁ ከሚኒሶታአቶ ሬድዋን ሁሴን ለሆዱ ያደረ በአራዳ ቋንቋ ‘ችስታ የወያኔ ተላላኪ’ መሆኑን ያሳየው ዛሬ ነው። በአርሊንግተን ቨርጂኒያ። አሜሪካን ውስጥ “ችስታ” ወይም ገንዘብ መቋጠር ከፈለክ የተራረፉ ልብሶችን የምትገዛበት ሱቅ ማርሻልስ ነው። የኬቨን ኪለር፣ ባናና፣ ቦስ፣ ናይኪ፣ አዲዳስ፣ ቶሚ፣ ኤክስፕረስ እና ወዘተ ታዋቂ የልብስና ጫማ አምራች ድርጅቶች በመደብሮቻቸው በሰዎች ልክ (ሳይዝ) የሰሯቸው እቃዎች ወደ ማለቂያ (ፋሽናቸው ሲያልፍ) የሚልኩት ወደ ማርሻልስ ስቶር ነው። ባጭሩ ማርሻልስን በሃገርኛ “ምናለሽ ተራ” ልትሉት ትችላላችሁ።
እንደለመደ አፉን አይከፍት ነገር ያለው አሜሪካ ሆነበት፤ እንዳይደነፋ ኢቲቪና መቀሱ የሉም። ውርደቱን ከኤክስፕረስ በታላቅ ቅናሽ የገዛውን ሰማያዊ ልብስ እንደለበሰ ተከናንቦ ተመለሰ። ወይ ሬድዋን፤ አዜብ ጆርጅ ታውን፣ ቴዎድሮስ ጄፕሬስ ሲገበያዩ አንተ ቺስታና ሆድ አደር ስለሆንክ በማርሻል ውርደትህን አከናነቡህ አይደል? ገና ምን አይተህ? ኢትዮጵያውያኑ የሳሞራ የኑስን ልብስ እንዲመስል ያደረጉልህ ቆዳህ ገና ወደ የት እንደሚሄድ አብረን እናየዋለን።
ሬድዋንን የተጋፈጡትን ብርቱ ኢትዮጵያውያንን እያደነቁ፤ የወያኔ ተላላኪዎችን የማወረዱ ሥራ እንዲቀጥል አደራ እላለሁ። ቪድዮውን እነሆ።
No comments:
Post a Comment